አንድ ሁለት ልጅ የወለድን ንብረት ለማፍራት ተፍ ተፍ የምንል ፅድድድድድት ያልን ትውልዶች!! እነዛን ሰገጤ ተላልቀው ያለቁ የ 60 ዎቹን እና የ 70 ዎቹን ወጣቶች “እንትን በኛ ግዜ ቀረ ፍሪኮች” የምንጠላ እና የምንፀየፍ ነቄ ትውልዶች!!

Habtish Dôø Yilma
ረጅም ፅሁፍ!
We are an old school
freaks በ 1970 ዎቹ ተወልደን
በ 1990 ዎቹ የፈነዳን ፅድድድድት
ያልን!!
ጋንዲ እና ዘውዲቱ ሆስፒታል
የተወለድን
ጥቁር አንበሳ ፣ ቦሌ ፣ አዲስ ከተማ
፣ አሳይ ፣ ምስካየዙናል ፣ አቃቂ
ሚሽን ፣ ካቴድራል ፣ ሴንጆ ፣
ናዝሬት ስኩል ፣ ደብረዘይት
ሃይስኩል ፣ ናዝሬት ሴንጆ እና በ
መላው ኢትዮጵያ በ1980ዎቹ
ትምህርት የጀመርን
ጠዋት ጠዋት ትምህርት
ከመጀመራችን በፊት የኢትዮጵያ
ብሄራዊ መዝሙር የዘመርን
መንገድ ላይ ሆነን መዝሩን
ከሰማን እንደ ጨው አምድ
ባለንበት የቆምን
የተማሪ ዩኒፎርም በ ሁሉም ት/
ቤቶች ያስጀመርን
በ ስጋጃ ቦርሳ ፣ በሪንግ ቡክ ፣
በDino ቦርሳ ደብተር ይዘን
የተማርን…
በ ባለ 50 ፣ 32 ፣ 16 ሉክ
ደብተሮች ለብደን የተማርን
የስዕል ደብተር በ ልሙጥ ሉክ
ሰፍተን የሰራን
ጋዝ ቀብተን አስደግፈን ስዕል
የሳልን
ሙዚቃ ፣ እጅ ስራ ፣ እርሻ ፣ ኑሮ
በዘዴ ፣ woodwork ፔሬድ
የተማርን
በአጥር ፎርፌ የገጨን
እጅ በጆሮ /የሞት ቅጣት/
የተቀጣን
የ መማርያ መፅሃፍ የ
መጀመርያው ገፅ ላይ ኢትዮዽያ
ትቅደም ብለን ትምህርት
የጀመርን
የ ሳይንስ የፊት ገፅ መፅሃፍ ላይ የ
እባብ ስእል ያየን
እነ አብዲሳ አጋ ፣ የቡልቻ ልብ ፣
ታታሪው አየለ ፣ ሽልንጌ ሽልንጌ ፣
Ahamed has two wives
በሚሉ የመማርያ መፅሃፎች
የተማርን
አርት እና ሳይንስ የመረጥን
ሃይስኩል ስንጨርስ አውቶግራፍ
ያስፈረምን
ግቢ ክላስ ቀጥተን ፑል
የተጫወትን
በጣት በ ሚቆጠሩ የመንግስት
ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች በ 5
ኢን ዋን ደብተር ተማረን
የጨረስን
በ መጀመሪያዎቹ የግል ኮሌጆች
ተምረን የተመረቅን
የካልሲ ኳስ ያንቀረቀብን
ኳስ ተጫውተን በ ብርቅርቅ
ሲጋራ ልጣጭ የተጠቀለለ የቅል
ዋንጫ የበላን
ለ በረኪና እቃ ዋንጫ
እስክንጋጋጥ ኳስ የተራገጥን
እርግብ ማርባት የምንወድ
ለ ፓሎኒ ኳስ መግዣ ብር
ያጠራቀምን
ፓሎኒ ኳስ ጎሚስታ ወስደን
ያስለጠፍን ያስነፋን
ለ ሰፈር ቡድን ማልያ ዋንጫ
ይዘን በ የቤቱ የለመንን
እርግጫ የተጫወትን
ብይ ፣ ጠጠር ፣ ሱዚ ፣ ፔፕስ ፣ ዲሞ
የተጫወትን
ማሪዮ እና ስኔክ ጌም ነፍሳችን
የነበረ
ዱቤ ዱቄት ፣ በካኪ ሚመጣው
ረጅም ፓስታ ፣ ጋሌጣ ፣ ኮቾሮ ፣
ኦፖፕ ፣ ፊዚዝ ፣ ጦር ማስቲካ ፣
ጠጠር ከረሜላ ፣ ጉንፋን ከረሜላ
፣ ዱላ ከረሜላ ፣ ሜንት ከረሜላ ፣
ሎሚ በከረሜላ የበላን
ጀላቲ ፣ ማይክል ዳቦ ፣ ፓስቲ ፣ በ
ከለርድ ያበድ ዳቦ ቆሎ ተደብቀን
የገዛን
አንባሻ ቤት ተደብቀን የገባን
ከተያዝን በርበሬ የታጥንን በ ሳማ
፣ በ አለንጋ ፣ በቀበቶ ፣ በሲሊፐር
ተገርፍን በቁንጥጫ ፣ በኩርኩም
የተቀጣን
ፖስታ ሳጥን ቁጥር የ ነበረን
የፍቅር ደብዳቤ የተፃፃፍን
የብእር ጏድኛ የነበረን
ገርል ፍሬንዳችንን በጩጬ
አስጠርተን በር ላይ የጀነጀንን
ብዙ ስልክ ቁጥር በቃላችን
የሸመደድን
በ ናሽናል ቴፕ ሪከርደር ሙዚቃ
የሰማን
በ ካሴት አዲስ እልበም የ ገዛን
ካሴት ደምሰስን ከ ሬድዮ
እንግሊዘኛ ዘፈን የ ቀዳን
እንዳይደመሰስ ከኃላ ያለችውን
አራት መአዘን ነገር በስኪብርቶ
የሰበርን እንደገና ለመቅዳት
ቀዳዳውን በ ሶፍት የደፈንን
በስኪቢርቶ ካሴት ያጠነጠንን
በጥፍር ቀለም የተበጠሰ ካሴት
የሰራን
እቤታችን JVC ዴክ የነበረን
VHS ካሴት የተከራየን
VHS ካሴት ማጠንጠኛ ይዘን
ያጠነጠንን
ከ ብላክ ኤንድ ዋይት ቲቪ ወደ
ከለርድ ቲቪ ያስቀየርን
21 ኢንች ከለርድ ናሽናል እንጨት
የ ሚመስለው ቲቪ ወይም NEC
ቲቪ ወይም 14 ኢንች ቲቪ
ቤታችን የነበረ
የ ከሰል ካውያ ወደ ኤሌክትሪክ
ካውያ ያስቀየርን
ስጋጃ ምንጣፍ ቤታችን የነበረ
ወይም ጣውላ ወለል በሰም
አሽተን ጉልበታችን እስኪዝል
በበርኖስ ያሸን
ሞ አንበሳ ባለው ትሪ ከቤተሰብ
ጋር ተሰብስበን የ በላን
በቡታ ጋዝ ሻይ የተፈላልን
ሰፈር ውስጥ የ ቡታ ጋዝ ክር ወደ
ውስጥ ገብቶ ፈንድቶ ቤት
ያቀጠለብን
ሽርርር የሚለው ስልክ የነበረን
ስልክ የተቆለፈብን ጠቅ ጠቅ ጠቅ
አድርገን የደወልን
ስም በተፃፍበት የ አባቶቻችን የ
ቆዳ ቀበቶ የተገረፍን
ለድግስ ቤታችን ዋይት ሆርስ ፣ ሬድ
ሌብል ፣ ሄግ ዊስኪ የተገዛ ወይም
እንግዳ ይዞልን የመጣ
ታላቅ ፊልም ላይ ሺና ፣ ጋድ መስት
ቢ ክሬዚ ፣ ዘ ስሪ ኮማንዶስን ያየን
ፍሬንድስ ፣ ቢል ኮዝ ቢ
ምንወዳቸው ሲት ኮም የነበሩ
ቫንዳም ፣ ቻክኖሪስ ፣ ሸዋዚንገር ፣
ሻሩኬ ፣ ማክጋይቨርን የምንወድ
በ እንግዳዘር ፣ አለባቸው ፣
ልመንህ ፣ አበበ በለው ፣ ደረጀ እና
ሃብቴ ፣ ተስፋዬ ካሳ ቀልዶች
የሳቅን..
ጂሚ ጂሚ ሃጃ ሃጃ ብለን የዘፈንን
won’t you take me to
funky town የሚለውን ዘፈን
ኮቱም ጃኬቱም ቆሽሿል እያን
የዘፈንን
በ 50 ሳንቲም ቪዲዮ ቤት ገብተን
ፊልም ያየን
እሁድ እሁድ ከ 8-10 ሰዓት 120
እያየን የተደበርን
space 1999 / ማያ / ፣ ፋዘር
ዶሊንግ ፣ ጄክ ኤንድ ፋትማን ፣
አካፑልኮ ፣ ነፃ ትግል ፣ ቲቪ አፍሪካ
፣ ቅዳሜና ማክሰኞ ማታ ህበረት
ትርዒት ፣ አርብ ከያቅጣጫው
ቅዳሜ ማታ ታላቅ ፊልም ያየን…
አንዳይነት ባንዳይነት ፣ በፍሬዘር
ሱሪ ፣ የጫማ ስእል ከነማሰርያው
ጀርባው ላይ ባለው ጂንስ ጃኬት ፣
ካራቴ ጫማ ፣ ራንግለር ጂንስ ፣
አንበሳ ጫማ ፣ ሰንደል ጫማ ፣
ዶክተር ሹዝ ፣ ክሬሽን ቱታ ፣ ሆት
ፓንት ፣ ስምንት ቅድ የዘነጥን…
ትዊንስ አራዳ ላይ ፣ ሄርሞን ፒያሳ
፣ ኮስሞስ ስቴድየም ፣ ለገሃር ሚኒ
፣ ቦሌ ሮድ ሮቢ ፣ ፐርፕል ፣ ፓራዲዞ
፣ ቦሌ ሚኒ ፣ ድንበል ዶም
ቺኮቻችንን ቀጥረን ተቆራጭ እና
ማኪያቶ አዘን 2 ሰዓት የጠበቅን…
ኩዊንስ በርገር የበላን
ፒዛ ዴሌ ሮማ ፒዛ የበላን
ብሩኖስ አይስክሬም የበላን
ፒያሳ ማሃሙድ ጋር ቺክ የቀጠርን
ትሬን ሃውስ ፣ ሃራምቤ ፣ ኢንተር
ላንጋኖ ሄደን የተሳሳምን
አራት ኪሎ ጊርጊሮ እና ብሄራዊ
ሥጋ ቤት ፣ ዶሮ ማነቅያ በቀለ ሥጋ
ቤት ፣ መስቀል ፍላወር ሙሉ ሸዋ
ስጋ ቤት ፣ ዱከም ምሥራቅ በር
ሥጋ ቤት ፣ ናዝሬት ይልማ ሥጋ
ቤት አዋጥተን ሄደን ቁርጥ እና
ጥብስ የበላን
በ አካል-ፀ ፣ ብላክ ላየን ፣ ድሪምስ
፣ ዛንዚባር ፣ ሲዱ ፣ ዴጃቩ ፣
ዲቫይን ፣ ፋንከን ፣ ሚልክ ሃውስ ፣
ሮሚና ፣ አሊዜ ፣ የጨስን
በቢጎዲን ፀጉራችንን የጠቀለልን ፣
ስኒ ላይ በ ሻማ ጭስ ኩል
በመስራት የተኳልን /የ ስር ኩል/
እንደ ኬሊ ሮውላንድ ስታይል ደረጃ
ቁርጥ ፀጉራችንን የ ተቆረጥን ፣ የ
አሊሺያ ኪስን ሹሩባ የተሰራን
ፓንክ ፣ ቱፓክ ቁርጥ ፀጉራችንን
ተቆረጥን ካተርፒለር እና
ቲምበርላንድ ግድንግድ ጫማ
አድርገን ፣ ሰፋፊ ቲሸርት ለብሰን ፣
ዎክ ማን በትልቅ ሄድፎን ሙዚቃ
እየሰማን ነጠር ነጠር እያልን
የሄድን
ክረምት ክረምት ትልልቅ ቴፕ
ይዘን ብሄረ ፅጌ ፣ አንበሳ ግቢ ፣
ባቦጋያ ፣ ሶደሬ ፣ ላንጋኖ ትሪፕ
የሄድን
የማይክል ጃክሰን ፣ ባብ ማርሊ ፣
ቱፓክ ፣ ኖቶሪየስ ቢ አይ ጂ ፣ አር
ኬሊ ፣ ማክሲ ፕሪስት ፣ አሸር ፣
ቦይዝ ቱ ሜን ፣ ባክስትሪት ቦይዝ ፣
ማይክል ቦልተን ፣ ክሬግ ዴቬድ ፣
ሾን ፖል ፣ ዊትኒ ሂዮስተን ፣ ሴልን
ዲዮን ፣ ማሪያ ኬሪ ሙዚቃ የ
ሰማን…
ሪተርን ኦፍ ዘ ማክ ፣ ኬንት ተች
ዚስ ፣ ዘፈኖችን በአማርኛ የዘፈንን
ሃው ዊል አይ ኖ ፣ ሊን ኦን ሚን
ለፍቅረኞቻችን የጋበዝን
የ አበበ ተካን
“አዬ ጉዷ መላመዷ
አዬ ጉዴ መላመዴ” ን ብለን
አብረን የዘፈንን
ታይታኒክ ፣ ዘ ቦዲ ጋርድ ፣ ዘ ቻምፕ
፣ ፎረሰት ጋምፕ ፣ ብሬቭ ሃርት
ምንወዳቸው ፊልሞች የ ነበሩ
የ ነቀዘች ህይወት ፣ ጉዲ ፈቻ ፣
ቀዝቃዛ ወላፈን ፊልሞች ሲኒማ
ገብተን ያየን
ሳቤላ ፣ ብርቅርቅታ ፣ ፍቅር እስከ
መቃብር ትረካ እሁድ ማታ
ያዳመጥን አምልጦን ሰኞ ጠዋት
ትምርት ቤት አርፍደን የደገምን
እሁድ ጠዋት ከ 4-5 ሰዓት አብዬ
ዘርጋውን ፣ ግዞ ፣ ባይከዳኝን
እንዲሁም የመአበል ዋናተኞች
ለመስማት የጏጏን..
የቅዳሜ ከሰዓት የሬድዮ
ድራማዎች በ ቲና ተርነር ዘፈን
ክላሲካል ታጅቦ ያዳመጥን…
ቅዳሜ ቅዳሜ በ ኢቲቪ
ፕሪሚየር ሊግ ቤታችን ያየን
ሮማሪዮ ፣ ቤቤቶ ፣ ትልቁ
ሮናልልዶን ያደነቅን… በሮናልዲኒሆ
ጥበበኛ እግሮች የፈዘዝን ለዚዳን
ብቃት ቆመን ያጨበጨብን በ
ቤክሃም አቋም የተማረክን..
ሺረርን የጎል ማሽን ያልን…
ስብሃት ገ/ እግዚአብሄር ፣ አዳም
ረታ ፣ በውቀቱ ስዩምን ፣ ሲድኒ
ሸልደን ፣ ዳንኤላ ስቴላ ፣ አጋታ
ክርስቲ መፅሃፍ ያነበብን….
ከ አዲስ ነገር ጋዜጣ እወቀት
የሸመትን
ሚኒሊክ ፣ ሳተናው ፣ ሊብሮ ፣
ወርልድ ስፖርት ፣ ኢንተር ስፖርት
ጋዜጦችን ያነበብን
በ ማዶና ፣ ቃል ኪዳን ፣ ኤሮቲካ
ጋዜጦች የሻፈድን
FM 97.1 ያስጀምርን በ ዲጄ ዚ ፣
ዲጄ ኪን ፣ ዲጄ ዊሽ ፣ ዲጄ ፋትሱ
ሙዚቃ ምርጫዎች የተዝናንን
የመጀመርያ ስልካችን NOKIA
3310 ፣ SONY ERICSSON
ወይም ሞቶሮላ የሆነ ሲም ካርድ
የተከራየን ያከራየን ሞባይል ስልክ
ቁጥራችን 0911 ብሎ
የሚጀምር
ዲ ኤክስ ፣ ወያኔ ዲ ኢክስ ፣ ሃችባክ
፣ ሊፍት ባክ መኪኖች የባረቁብን
በ ውይይት ታክሲ የሄድን
በ ጎልድ ኩዌስት ብር የተበላን
የ 10 ሳቲም ሻይ ቅጠል ፣ የ 25
ስኳር ፣ የ 50 ሳንቲም ዘይት
ተልከን የ ገዛን ቢ 29 ሳሙና በ
90 ሳንቲም ጊቭ በ 1.50 ብር የ
ገዛን
ነዳጅ በ 4 ብር የቀዳን
በኛ ዘመን ጀግኖች ሃይሌ ገ/ስላሴ
፣ ደራርቱ ቱሉ ፣ ቀነኒሳ በቀለ ፣
ጥሩነሽ ዲባባ ፣ መሰረት ደፋር
ድሎች በደስታ የፈነጠዝን
በነ ሳላዲን ሰኢድ ፣ አዳነ ግርማ ፣
ጌታነህ ከበደ የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ
ብሄራዊ ቡድንን ከ 30 አመት
በኃላለ አፍሪካ ዋንጫ ያሳለፍን…
የጂጂ አንድ ኢትዮዽያ እና የቴዲ
አፍሮ አቦጊዳ አልበም ነፍሳችን
የነበረ
አራት መሪ ያየን
ጏድ መንግስቱ ሃ/ማርያም
ሜ/ ጀ ተስፋዬ ገ/ኪዳን
ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ
ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ
ኢህአዴግ ኢትዮዽያን ሲቆጣጠር
ኤለመንተሪ ተማሪ የነበርን
በቀድሞ ጠ/ሚያችን መለስ ዜናዊ
ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና የ አመራር
ብቃት የተደመምን እና በዛቻቻው
የደነገጥን
ኤርትራ ስትገነጠል በልጅ
አእምሮዋችን ምፅ ምፅ ያልን
የ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ላይ
ታላቅ ወንድሞቻችን የተዋጉ እና
የሞቱብን
ታሪካዊዉ ምርጫ 97 ላይ በ
ስፋት የተሳተፍን ልደቱ አያሌውን
ያነሳን ያፈረጥን
በምርጫ 97 በተነሳው ብጥብጥ
ጏድኞቻችን የሞቱብን…
እኛ በ 70 ዎቹ ተወልደን በ 90
ዎቹ ፈንድተን በቅርብ ትዳር ይዘን
አንድ ሁለት ልጅ የወለድን ንብረት
ለማፍራት ተፍ ተፍ የምንል
ፅድድድድድት ያልን ትውልዶች!!
እነዛን ሰገጤ ተላልቀው ያለቁ የ
60 ዎቹን እና የ 70 ዎቹን
ወጣቶች “እንትን በኛ ግዜ ቀረ
ፍሪኮች” የምንጠላ እና የምንፀየፍ
ነቄ ትውልዶች!!

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s