ባለ532 ብር ደመወዝተኛው የሕወሓት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማግበስበሱ ተሰማ

Abraham's view

 

(ኢሳት ዜና) የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል።

birr4123111በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ ወልደስላሴ ወንድም አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ የመከላከያ ሚኒስቴርን ሲለቁ በመጨረሻ ይከፈላቸው የነበረው ወርሃዊ ደሞዝ 532 ብር ብቻ እንደነበር አመልክቷል ፡፡ ይሁንና፣ ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ በተለያዩ ባንኮች በስማቸው 5 ሚሊዮን ብር ከማስቀመጣቸውም በተጨማሪ፣ አዲስ አበባ ቤቴል ሆስፒታል አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ እያካሄዱ ፣ በአፋር ክልል ደግሞ ከ1 ሚሊዮን 400 መቶ ሽ ብር በላይ በሆነ ወጪ የእርሻ ኢንቨስትምንት እያከናወኑ መሆናቸው እንዲሁም በስማቸው 2 ሚሊዮን 700 ሺ ብር ግምት ያላቸው 2 ሎደር መኪኖች መገኘታቸውን ገልጽዋል።

የአቶ ወልደስላሴ እህት የሆኑት ወ/ሮ ትርሃስ ደግሞ የ8ኛ ክፍል ተማሪና ምንም ስራ ያልበራቸው ሲሆን፣ በወንድሞቻቸው ድጋፍ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ አንድ…

View original post 175 more words

ሳውዲ አረቢያን ያጠቃው መደሃኒት አልባ የግመል ጉንፋን «ኮሮና ቫይረስ» ለኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ተገለፀ !

Freedom4Ethiopian

በሽታው የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን የሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ይፋ ካደረጉ ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራቶች ውስጥ በቫይረሱ ከተለከፉ ህሙማን መሃከል 500 ያህሉ ህይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፤ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች እና ተጓዳኝ የሆኑ እንደ ስኳር ደም ብዛት ኩላሊት ወዘተ መስል በሽታ ያሉባቸው እና በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅመ የሌላቸውን የቫይረሱ ተጠቂዎች በ 10 ቀናት ውስጥ በሽታው ለህልፈት ህይወት እንደሚዳራጋቸው ከሳውዲ አረቢያ ሆስፒታሎች የሚወጡ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ሳውዲያኑ ጨምሮ የተለያዩ ሃገር ዜግነት ያላቸው የቫይረሱ ተጠቂዎች መሞታቸውን በተለያዩ ግዜያት ከሚወጡ የሆስፒታሎች ዘርዝር መረጃ እስካሁን አንድም ኢትዮጵያዊ የቫይረሱ ሰለባ እንዳለሆነ ለማወቅ ተችሏል ።በሽታው ሲጀምር ጉንፋል መስል ባህሪ እንዳለው የሚናገሩ ባለሙያዎች ማስነጠስ ሳል ትኩሳት እና እራስምታት የሚታይበት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አካባቢው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ቀርቦ በመርመር ከፋይረሱ ነጻ መሆኑንን ማረጋገጥ እንደሚገባው ይመከራል።

ለጥናቄ ይረዳ ዘንድ ማንኛውም ሰው እጆቹን በሳሙና ከመታጠቡ በፊት አፍንጫውን አፉን እና የአይኑን ሰውነት ክፍሎች በእጁ መነካካት እንደሌለብት የህክምና ጠበብቶች አክለው ይገልጻሉ ። በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ደማም ጣይፍ እና ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለያዩ የስራ…

View original post 129 more words

“ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ

Freedom4Ethiopian

በቅርቡ በግብጽ ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸንፋሉ እየተባለ የሚጠበቁት ዕጩ ተወዳዳሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” ሲሉ ገለጹ፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ በውጭ የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን ምሁራን የግድቡ መሠራት ግብጽን “በማይቀር አደጋ” ላይ እንደማይጥላት አስረዱ፡፡

በግብጽ በተላለፈ የቴቪ ስርጭት ትላንት ቃለመጠይቅ የሰጡት የቀድሞው የግብጽ ጦር መሪ ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ ግድቡን አስመልክቶ ሰፊ ትንተና እንዳልሰጡ አልሃራም የቲቪ ስርጭቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሆኖም ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ ማለት ለእኛ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡

አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊደረግ የሚገባው ንግግር ትኩረት ሳይሰጠው ለረጅም ጊዜ የቆየ መሆኑና ውይይቱም የተጀመረው ዘግይቶ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን ተገቢውን ጥረትsisi አለማድረጋችንን ማመን አለብን፤ በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ለመተባበርና መፍትሔ ለማግኘት ድርድርና የጋራ መግባባት ቁልፍ ናቸው” በማለት አል-ሲሲ የግብጽን ፍላጎት አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ የአባይ ግድብ ዙሪያ…

View original post 288 more words

በቅርቡ የታሰሩት ጋዜጠኞች እና ዞን 9 ብሎገሮች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

Freedom4Ethiopian

ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ከጠዋቱ 4፡00ሰዓት የነበረው ቀጠሮ ባልታወቀ ምክንያት ወደ 8፡00 ሰዓት ተዛውሮ ነበር፡፡ በ8፡00 ሰዓት በነ በረው ቀጠሮም አጥናፍ ብርሃን፣ ኤዶም ካሳዬ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያው ዙር ወደ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ በ9፡00 ሰዓት ደግሞ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ዘለዓለም ክብረት ቀርበዋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ ፖሊስ) ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመጠየቁ ለቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ጉዳዩ በዝግ ችሎት ነው በሚል ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ ጓደኛ እንዲሁም በስፍራው የነበሩ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ፣የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች፣ ዲፕሎማቶች ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ችሎቱን መታደምም ሆነ መግባት በመከልከሉ ጉዳዩ በዝግ ችሎት ተከናውኗል፡፡
ቀሪዎቹ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህት ፋንታሁን ነገ ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ የዛሬ ፍርድ ቤት ሌላ ለየት ያለው ክስተት የህግ ባለሙያ የሆነው ወጣት ኪያ ፀጋዬ ችሎቱን ለመታደም አራዳ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ ፎቶ…

View original post 35 more words