የአይሲል (ISIL) እንቅስቃሴ ምንነትና አንደምታው (ከአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዕይታ)

የአይሲል (Islamic State of Iraq and the Levant – ISIL) እንቅስቃሴ ከሰማይ ዱብ ያለ አዲስ ክስተት አይደለም። አይሲል ( አንዳንዶቹ ISIS ይሉታል – Islamic State of Iraq… Read more “የአይሲል (ISIL) እንቅስቃሴ ምንነትና አንደምታው (ከአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዕይታ)”

ግልጽ ደብዳቤ ለህወሃት –– ኦባንግ ሜቶ September 25, 2014 ግዜ መልኩን ሳይቀይር አሁን ባላችሁ ዕድል ተጠቀሙ! … ቀናነት ነጻ ያወጣችኋሌ! አባይ ወሌደ የህወሃት ሉቀመንበር መቀሌ፤ ትግራይ አቶ… Read more

ኢማም ሀጂ ዙልመካ እና ስስ ፌስታላቸው (መሀመድ ሰልማን) =============== =============== === ኢማም ሀጂ ዙልመካ ከማሰገጃ ቦታቸው ጫማ እስከመልበሻዉ የመስጊድ በረንዳ እስኪደርሱ ባሉ ጥቂት ሜትሮች ውስጥ የህዝብን ፍቅር እንዲህ ያጣጥሙት ነበር፡፡ . . ከሰጋጁ ያን ሁሉ ሺ ‹ዚያራ› እና በረከት የሚቀበሉትም ይህችኑ ርቀት በመራመድ ላይ ሳሉ ነበር፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ኢማሙ ከማሰገጃ መቅደሳቸው እስከ መውጫ እስኪደርሱ እጅግ ዝግ ብለው መራመድ ስለሚኖርባቸው በግምት 30 እና 40 ደቂቃ ይወስድባቸዋል፡፡ ፈጣሪም ይወዳቸዋል መሰለኝ እንደታፈሩ እና እንደተከበሩ ወደእርሱ ጠራቸው፡፡ አላህ ይርማቸው!(ነፍስ ይማር! እንደማለት) . . በእርግጥም ከእርሳቸው በኋላ የሚያስፈራራ እንጂ የሚፈራ ኢማም አልመጣም፡፡ ከዚያ በኋላ የመጡ አስተዳደራዊም ሆነ መንፈሳዊ መሪዎች በትርፍ ሰአታቸው ፑል የሚጫወቱ፣ ውል ውል መኪና የሚነዱ፣ ፈጣሪንና የፓርቲን ትእዛዛት የሚደባልቁ ሆነው ተገኙ፡፡ እነዚህንም ነፍስ ይማር እንላለን(ባይሞቱም)፡፡ . . ከፍተኛ የህዝብ ፍቅር የነበራቸው ሀጂ ዙልመካ ባለ መኪና እንኳ አልነበሩም፡ በዝግታ እየተራመዱ በእግራቸው ወደመኖሪያ ቤታቸው ያዘግማሉ፤ እግረ መንገዳቸውንም ሽንኩርትና ቲማቲም በስስ ፌስታል ገዝተው ይቋጥራሉ፡፡ ይህች ስስ ፌስታላቸው አትዘነጋኝም፡፡ አእምሮን ንፁህ አድርጎ ቀላል ህይወትን መምራት እንዴት እንደሚቻል የሚያስተምሩባት ምስጥር ትመስለኛለች፡፡ . . የእኚህን ኢማም የአእምሮ ሰላም በስስ ፌስታላቸው ውስጥ አየዋለሁ፡፡ የቱንም ያህል ሀብት በማግበስበስ ይህች ሰላም አትገኝም፡፡ ሀያ ምናምን ክፍሎች ባሉት ቪላ ውስጥ እየኖሩ ይህች ሰላም አትገኝም፡፡ ጃኩዚ ውስጥ በመነከር ይህች ሰላም አትገኝም፡፡ የአለምን ከንቱነት እየሰበኩኝ ጎማው ቢሸጥ አምስት መቶ ነዳያንን ማጉረስ የሚችል ዘመን አመጣሽ መኪና የሚዘውር ‹ኢማም›ን እንዴት እሰማዋለሁ? . . መንፈሳዊ አባት ህይወቱ ምሳሌ ካልሆነኝ ስብከቱ ጩኸት ነው-ለኔ፡፡ የቆርቆሮ ጩኸት፤ ያደነቁረኛል፡፡ ድምፁ ከመንፈሳዊ ህይወት የሚያስሸሸኝ የጦር መሳሪያ ነው ለኔ፤ ይረብሸኛል፡፡ የኢማም ሀጂ ዙልመካ ፌስታል ትርጉሟ የትየለሌ ነው፡፡ በድህነት ተቆራምዶ መኖርን ሳይሆን ቀላል ህይወትን ትወክላለች፡፡ ኢማሙን ስስ ፌስታል ያስያዛቸው የንዋይ እጥረት አልነበረም፤ ለዚህ አለም ብዙም ቁብ ካለመስጠት የመነጨ፤ ተምሳሌት ኾኖ ከመኖር የመነጨ እንጂ፡፡ ይህንን የምለው እንዲሁ አይደለም፡፡ እርሳቸው ቢፈቅዱ አንድ ‹‹ቢጠሩት የማይሰማ›› ተራ የመርካቶ ሀብታም ጥይት የማይበሳው መርሴዲስ በማግስቱ ሊያበረክትላቸው እንደሚችል ስለምረዳ ነው፡፡ እርሳቸው ግን ይህን አልመረጡም፡፡ . . ዛሬም ድረስ ትዝ የሚለኝ ሙስሊም አማኞች ኢማሙን መንገድ ላይ ሲያዩዋቸው እንዴት ከመኪናቸው ተስፈንጥረው በመውረድ መዳፋቸውን በአክብሮት ይስሙ እንደነበር ነው፡፡ ኢማም ሀጂ ዙልመካና ስስ ፌስታላቸው ሰው ለኑሮው ከሚያስፈልገው በላይ መንሰፍሰፍ እንደሌለበት ታስተምራለች፡፡ የፌስታሏ ስስነት ንፁህ አእምሮን ትወክላለች፤ ንፁህ አእምሮ ምቹ ትራስ ናት እንዲሉ፡፡ መንፈሳዊ እና ምድራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሙስና ውስጥ ተጨመላልቆ መንፈሳዊ አባትነት አይገባኝም፡፡ ምንና ምን ተገናኝተው፡፡ . . . የህዝብ ፍቅር የፈጣሪን ፍቅር ወሳኝ ነው፤ ለኔ፡፡ ለአብነት ሀጂ ዙልመካን ብንወስድ የጁምአ እለት ሰላትን ከተጠናቀቀ በኋላ እንደ ማንኛውም ግለሰብ ብድግ ብለው ከመቅደሳቸው መውጣት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ከመስጊድ ውጪ እስከ ጣና ገበያ፣ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ እና ጎጃም በረንዳ ድረስ እንደ አሸዋ የተዘራው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝበ ሙስሊም መፈናፈኛ አይሰጣቸውምና ነው፡፡ ብድግ ብለው ከወጡ እርሳቸውን ለመሳም በሚደረግ ተጋድሎ በእንደኔ አይነቱ ጥቃቅን ፍጥረት ላይ የመጨፍለቅ አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡ . . . . ህዝበ ሙስሊሙ ወደመጣበት ከተመለሰ በኋላ ነው ኢማሙ ከማሰገጃ መንበራቸው የሚንቀሳቀሰሱት፡፡ ይህ የህዝብ ፍቅር በምርጫ ካርድ እንኳ አይገኝም፡፡ ስስ ፌስታል አንጠልጥሎ የሚሄድ መንፈሳዊ አባት ናፈቀኝ! እኚህ ታላቅ መንፈሳዊ አባት ከብዙ አመታት በፊት በታላቁ አንዋር መስጊድ የሳሙኝ ግንባሬ ዛሬ በታላቁ ‹‹ላ ሞስክ ዴ ፓሪስ›› ይገኛል፡፡ ————— ————— ————— ————— ————— ————– መሀመድ ሰልማን ‹‹የፒያሳ ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ›› መፅሀፍ ደራሲ ነው፡፡ ይህ ፅሁፍ እንቁ መፅሄት ‹‹አንድ የጁመአ ሶላት በፓሪስ›› በሚል ካሰፈረው የተወሰደ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ሙስሊም ሰራተኞችን አስተዳደሮችን የሚያሸማቅቅ ህገ ደንብ አወጣ።

Originally posted on Freedom4Ethiopian:
የኢትዮ ቴሌኮም ስራተኞችና አስተዳደሮች ፂማቸውን እንዳያሳድጉ ተከለከለ! እንደሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ከወርሃ ሃምሌ 2003 ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ,ውስጥ ከነበረው አህባሽን በግዳጅ ከመጫን ሂደት ጀምሮ…

ወያኔ በፀረ _ እስልምና አቋሙ ፖለቲካዊ ሚናውን ማሳደግ ይፈልጋል ኢህአዴግ በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ እንዲኖረው ለሚፈልገው ታላቅ ሚና ሙስሊሙ ስጋት ይሆኑብኛል ፍርሃት ሊኖረው ይችላል።ኢትዬጵያ በአፍሪካ ቀንድ ካሉት… Read more