12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በኩዌት ታሰሩ

Freedom4Ethiopian

       የኩዌት መንግስት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በህገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በማስገባት በቤት ሰራተኝነት ያስቀጥራሉ የተባሉ  12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እንዳስታወቀ አረብ ታይምስ ዘገበ፡፡
የሚኒስቴሩን መግለጫ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፤ 12 ሴቶችንና አንድ አሽከርካሪን በአባልነት ይዞ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ስራ ላይ እንደተሰማራ የተገለጸው ይህ ቡድን፣ በአንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት መሪነት በህገወጥ መንገድ ወደ ኩዌት የሚያስገባቸውን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለአገሪቱ ዜጎችና ለሌሎች አገራት በቤት ሰራተኝነት ሲያስቀጥር ቆይቷል፡፡
የኩዌት የነዋሪዎች ጉዳይ ምርመራ ክፍል ባለስልጣናት፤ በድኑ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ላይ እንደተሰማራ ከታማኝ ምንጭ ያገኙትን መረጃ መሰረት በማድረግ ባካሄዱት ክትትል፣ የቡድኑን አባላት የህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚያከናውንበት ጀሊብ አል ሹዮክ የተባለ የአገሪቱ ክፍል በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
የቡድኑ አባላት ከአገሪቱ የሰራተኞች ቢሮ ጋር የስራ ግንኙነት ያላቸውና በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ በማስመሰል በበርካታ የኩዌት ነዋሪዎች ላይ የማጭበርበር ድርጊት ሲፈጽሙ ነበር ብሏል፤ ዘገባው፡፡
በቁጥጥር ስር በዋሉት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር…

View original post 8 more words