እንኩዋን አደረሰዎት እሁድ ነው እየተባለ ነው

የራሰ በራነት
መድሃኒቶች ምን ያህል ውጤታማ
ናቸው?
ራሰ በራ ነዎት? ወይስ ራሰ በራ ሰው
በቤትዎ አለ? እርስዎስ ፀጉርዎ ገባ
ገባ፤ሸሸት ሸሸት ማለት ጀምሮብዎ
ይሆን? ራሰ በራ የሆነ ሰው ሲመለከቱ
ምን ይሰማዎት ይሆን?
አንዳንዶቻችን መምለጥ የስነልቦና
ተፅዕኖ አሳድሮብን ይሆናል፡፡ በተለይ
ምዕራባዊያን መላጣ ወንዶች
የሴቶችን ቀልብ የመግዛት
ግርማቸው እንደሚገፈፍ ያምናሉ፡፡
በእርግጥ ይህ በግልፅ ምክንያቱ
ባይታወቅም በኛም ሀገር ተመሳሳይ
ሁኔታዎች እንዳሉ ከሴቶቻችን ሁኔታ
መረዳት ይቻላል፡፡ ይም ሆነ ይህ
መምለጥን አስቀድመን ማስቀረት
እንችላለን?
በቅርቡ ለሕትመት የበቃን አንድ
ጥናት ባነበብኩ ወቅት ለፅሑፌ መነሻ
እንዲሆን ሻትኩ፡፡ ጥናቱ እስከዛሬ
ስለራሰ በራነት ያልተነገሩ
እውነታዎችን ለማስነበብ በቅቷል፡፡
በመሰረቱ ራሰ በራነት በጥንት ዘመን
መጥፋት ሲገባው በትንሽ የዘረመል
ስሕተት ከትውልድ ትውልድ ሊተላለፍ
የበቃ ለአብዛኞቹ የራስ ምታት፤
ለዘመኑ ተመራማሪዎች የስራ ዕድል
የፈጠረ መሆን ችሏል፡፡ አለመታደል
ሆኖ ነው እንጂ የራሰ በራነት
የዘረመል ቀመር ድሮ የሰው ልጅ
የዝግመተ ለውጥ ውስጥ ሲያልፍ
ሊጠፋ ሲገባው በትንሽ አጋጣሚ ከዘር
ዘር እየተባዛ አሁን ላይ ላለው
በሚልዮን ለሚቆጠረው ወፈሰማይ
ሕዝብ መለያ ምልክት ሆኖ ሊቀር
ችሏል፡፡
baldness
ሰዎች ለምን ፀጉራቸው ይሳሳል
በመጨረሻም እንዴት ሊመለጥ
ይችላል ብለን ብንጠይቅ አያሌ
ምክንያቶችን እንሰማለን፡፡ ነገር ግን
የሰው ፀጉር በምንም ዓይነት መልኩ
ቢወድም ተመልሶ መብቀል እስከቻለ
ድረስ አብዛኞቹ ምክንያቶች
ተቀባይነትን ያጣሉ፡፡
አዲሱ ጥናት ምን ይላል?
አብዛኞቹን ከዚህ ቀደም የነበሩ
ጥናቶችን ይደግፋል፡፡ በዚህ
መሠረትም አብዛኛው መላጣ ግለሰብ
መምለጥ የሚጀምረው ዕድሜ ከ30
ሲሆን ከዛ በፊትም ሊሆን ይችላል
ነገር ግን የአብዛኛው መላጣነት
አይቀሬ መሆኑ የሚታወቀው ከፊት
ፀጉሩ ገባ ገባ ማለት ሲጀምር ነው፡፡
በመቀጠልም ከወደ ኋላ መሳሳት
ይጀምራል፡፡ ይህ ዓይነት አመላለጥ
በሕክምና እንኳን ላይቆም ይችላል፡፡
በጥናቱ መሠረት ሰዎች ወደ
መላጣነት የሚያመሩበት ዋነኛ
ምክንያት የወንድ የዘር ፍሬ
(ቴስቴስትሮን) ክምችት በሰውነት
ውስጥ መብዛት ነው፡፡ ይህ የዘር ፍሬ
ክምችቱ ሲጨምር በሰውነታችን
አማካኝነት ወደ
ዲሀይድሮቴስቴስትሮን ሆርሞን
ይቀየራል ሆርሞኑም ወደ ራሳችን
በማምራት የራስ ቅላችንን የፀጉር
ማምረቻ ቀዳዳዎችን በመድፈን
አገልግሎታቸውን እንዲያቋርጡብን
ያደርጋል፡፡ በዚህ ጊዜም ፀጉር
መብቀል ይቀራል፡፡ ራሳችንም
መምለጡን እንረዳለን፡፡
ሁለተኛውና ብዙዎቹ ጥናቶች
የሚደግፉት በዘር የሚተላለፍ
መላጣነት ሲሆን፡፡ እስካሁን
የመላጣነትን የዘረመል ኮድ ተንትኖ
ማብራሪ የሰጠ ተመራማሪ ባለመኖሩ
አንዳንድ መላጣዎች በሕክምና
መፍትሔ ሲያገኙ ብዙዎቹ
ሙከራቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የወንድ የዘር ፍሬ መጠን በሰውነት
ውስጥ መጠኑ አለቅጥ መጨመሩ
ለመላጣነት ቢዳርግም መኮላሸት
ደግሞ ራሰ በራነትን እንደሚከላከል
ጥናቱ ደምድሟል፡፡ በእርግጥ የፀጉር
ቀዳዳዎች በራሳቸው የሕይወት ዑደት
ውስጥ የሚሄዱ ቢሆኑም
የዲሀይድሮቴስቴስትሮን ሆርሞን
ካገኛቸው ያለምንም ምክንያት
ልንመልጥ መቻላችን በመኮላሸት
መፍትሔ ማግኘት እንደሚቻል ጥናቱ
ቢጠቁምም አብዛኛው መላጣ
ግለሰብ የማይቀበለው መፍትሔ
ነው፡፡ ከዚህ የተሻለ ሀሳብም
በማቅረብ ደረጃ ወሲብን በለጋ
ዕድሜ መጀመር ጥሩ እንደሆነ
የሚመክሩ ተመራማሪዎችም
አልጠፉም፡፡ ነገር ግን ወሲብ ያን
ያህል አስተማማኝና ቋሚ ላይሆነ
ስለሚችል ይህኛውም መፍትሔ
ተቀባይነት አላገኘም፡፡ እንግዲህ ልብ
ይበሉ እነዚህ መፍትሔዎች ሁሉ ገና
ላልመለጡና የመምለጥ ስጋት
ላለባቸው ነው፡፡
በቫለሪ ሆስሌ የተመራ
የተመራማሪዎች ቡድንም በዬል
ዩኒቨርሲቲ የራስ ቅል ፀጉር አብቃይ
ሕዋሳትን ለመፍጠርና ለማባዛት ደፋ
ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡ የራስ ቅል
ሕዋሳትን በማውደም ለቀዳዳዎቹ
መደፈን ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች
ብዙ ቢሆኑም፡፡ሕዋሳቶቹን
በማነቃቃት የፀጉር መሠረት የሆነ
የፕሮጄኒተር ሕዋስ እንዲፈጠር
ማድረግ ችለዋል፡፡ይህ ግኝታቸውም
ለሁሉም ራሰ በራዎች የሚሆን
መፍትሔ እንዲፈልጉ አነሳስቷቸዋል፡፡
የራሰ በራነት መድሐኒቶች፤ከጥንት
እስካሁን
ከ5000 ዓመተ ዓለም ጀምሮ
አርቴፊሻል ፀጉር(ዊግ) የሰው ልጅ
ይጠቀም እንደነበር የታሪክ
መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ጊዜ
አሴራዊያን፣ሱሚሪያውያን፣
ፋርሳዊያን እና ግሪካዊያን በስፋት
እሚጠቀሙበት ሕዝቦች እንደነበሩ
ይታወቃል፡፡ ከዊግ ባሻገርም ራሰ
በራነትን ለመከላከል የሚውሉም
የባሕል መድሀኒቶችም ነበሩ፡፡ለምሳሌ
ያህለ ግብፃውያን 3500 ዓመት
የሚሆነው በፓፒረስ ያሰፈሩት
የአይረን ኦክሳይድ፣የእርሳስ
ማዕድን፣ሽንኩርት፣ማር፣ከ እባብ፣አዞ
እና አንበሳ ሥጋ የሚሰራ ነገር ግን
ለፀሀይ አምላክ ተፀልዮ የሚሰጥ
መድሐኒት ብለው ያስቀመጡት
ሙከራቸው አንዱ ነው፡፡ ባጠቃላይ
የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ መፍትሔ
ፍለጋውን አቋርጦ አያውቅም፡፡
በአሁን ዘመን ፀጉርን በቀዶ ጥገና
ማስተከል ዝነኛና ውጤታማ እየሆነ
የመጣ ነው፡፡ ዳሩ ግን ይህ የሚሆነው
ለጥቂቶቹ ዕድለኞችና ሚልየነሮች
ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚሆነውም ፀጉር
ካለው የራስዎ ቅል ወይም ፀጉራም
ከሆነ ወዳጅዎ የፀጉር ቀዳዳ ሕዋሳት
ይወሰድና በመላጣው ራስዎ ቦታ ላይ
ልክ እንደ ችግኝ ይተከልልዎታል፡፡
በሒደትም ሕዋሳቱ በአካባቢው
መስፋፋት ይጀምራሉ፡፡ ራሰ በራነትን
መከላከል ይልዎታል ይህ ነው፡፡
አርቴፊሻል ፀጉርንም ማስተከል
በአሁን ዘመን ቢቻልም ይህ
ለቢልየነሮች ብቻ የሚሆን አማራጭ
ነው፡፡ አርቴፊሻል ፀጉር ማስተከል
ከመላጣ መላጣ ስለማይለይም ጥሩ
መፍትሔ ሆኗል፡፡
አሁን የስነውበት ኢንዱስትሪውን
እያጥለቀለቁ ከመጡ ራሰ በራነትን
ከሚከላከሉ እንክብሎች መካከል
ፕሮፔሺያ የሚባለው ይገኝበታል፡፡ ይህ
እንክብል በሰውነታችን ውስጥ
የሚገኘውን የወንድ የዘር ፍሬ
(ቴስሬስትሮን)መጠን በመቀነስ
የፀጉራችን ቀዳዳዎች በሆርሞናችን
እንዳይደፈን ይደርጋል፡፡ ይህ
እንክብል ለቅድመ መከላከል ወይም
መምለጥ ለጀመራቸው ጥሩ መፍትሔ
እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል፡፡
ሌላኛው ዝነኛ መድሐኒት ሚኖዚዲል
ይባላል፡፡የንግድ ስያሜው ሮጄን
ይባላል፡፡ የደም ፍሰትን በማፋጠን
ፕሮስታግላንዲን የተሰኙ የፀጉር
ዕድገት አፋጣኝ ኬሚካሎች
ስራቸውን እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡ ይህ
ብዙዎቹ ሞክረውት መምለጥ
የጀመረው የራስ ቅላቸው ተግባሩን
እንዲገታ አድረጎላቸዋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም ይህ መድሐኒት
ትንንሽ በአማርኛ የአንበሳ ፀጉር
የምንላቸውን ብናኝ መሳይ ፀጉሮችን
ማብቀል ችሏል፡፡
በቅርብ ጊዜ በመላጣነት ዙሪያ ሳይንስ
ትልቅ የሚለውን መፍትሔ ይዞ
እንደሚመጣ ከወዲሁ ብዙ
ተመራማሪዎች እየጠቆሙ ነው፡፡
በተለይ አሁን ስለ ራሰ በራነት ያለው
ግንዛቤ ሰፊ በመሆኑ ለሁሉም ራሰ
በርሃ የሚሆን መፍትሔ በባዮሎጂ
ባለሞያዎች እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
መድሐኒቱም የፀጉር ቀዳዳዎች
እንዳይደፈኑና ፋፍተው ስራቸውን
እንዲያከናውኑ ከማድረግም በላይ
በራሰ በራ ሰዎች የተደፈኑት የፀጉር
ቀዳዳዎች እንዳዲስ ተከፍተው ፀጉር
ማብቀል እንዲችሉ የሚያደርግ
እንደሆነ ተነግርለታል፡፡
እርስዎስ ምን አስበው ይሆን?
የተጠቀሱትን መድሐኒቶች መሞከር
ይፈልጋሉ ወይስ በራሰ በራነቴ
እኮራለሁ ይላሉ? መልሱን ለእርስዎ
እየተውኩ እኔ ግን ቸር እንሰንብት
እላለሁ፡፡

ተሀጁድ ሊቀር ነው ?
ወላሂ አሁን ዝሁር ላይ በኢማሙ
በኩል
የተላለፈው መልእክት
በትክክል መሞታችንን ያመለክታለወ
ኮካ
መስጂድ ነው ኢማሙ ተገደው
እንደሆነ ያስታውቃል ሳቅ እያሉ ነው
የሚያወሩት እናም እንዲህ አሉ
የተሃጁድ ሰላት እንዳይሰገድ
ተረሃዊም ባጭሩ
እንዲሰገድ ከበላይ ትዛዝ
ተላልፉዋል አሉ
ከዚህ በፊት የመሰጂድ ኮሚቴና
ጀመአው
መሹራ በማድረግ ነበረ የምንወስነው
አሁን
የሚተደደረው በመጅሊስ ስለሆነ
ተዛዙም
ከዛው ነው የመጣው አሉ
ኢናሊላሂ ተዲያ በትክክል
አልሞትንም?
ወላሂ ምን እንደምንጠብቅ
አላቅም !
እስኪ ወንድሜ # malcolm king
ግድግዳውላይ ከለጠፋት ፁፍ ጥቂቷን
ተውሼ
ላስነብባቹ !
ኣህባሽ የሚባል ከኢስልምና ያፈነገጠ
በኣይሁዳ የሚረዳ ሃይማኖት
ከሊባኖን ኣምጥቶ በግድ ቀይሩ ኣለን
ተደናግጠን እያለን ይግረም
ብሎ ደሃ ሲሞት ታጥቦ
የሚቀበርበትን ኮሌጅ
ኣወሊያን ኣስተማሪወቹን
ኣባሮ ወሰደው እንዴ ከዛስ? ከዛማ
ተማሪወች
ተሰባሰቡና
ኣስተማሪዎቻችን ይመለሱ ብለው
ተቃውሞ
ጀመሩ ከዛ ሌላውም
ኢትዮጲያዊ ተከትሎ ኮሚቴ ተመርጦ
መንግስትን የሚሰራው ነገር
ትክክል ስላልሆነ ወደ ራሱ
እንዲመለስ እሱ
ያዋቀረውንም መጅሊስ
ኣፍርሶ ሙስሊሙ እራሱ
የሚፈልገውን
በመስጊዱ እንዲመርጥ
እንዲፈቅድልን መልከተኛ ላክን
ከዛስ?
ወዲያው ደነገጡና ፈቀዱ
ኣይደል?ኣይደለም መጀመሪያ ጥሩ
መልስ
እንደሚሰጡንና
የኮሚቴውም ኣወቃቀር ህጋዊ
እንደሆነ
ነገሩንና መልሱን ከኣንድ ወር
ቡሃላ እንደሚሰጡ ነገሩን ሲገርም
ለመብታቹህ እንዴት ኣንድ ወር
ይቀጥራሉ ወዲያው
ኣይመልሱም፧ወር
ኣስጠብቀው ሁሉንም መለሱ
ኣይደል? ኣይደለም ጸባያቸው ሁሉ
ተቀያይሮ
ኣሸባሪ ምናምን ኣገር
ሚበጠብጡ ብለው ኣንድ ምሽት ላይ
ህጻን
ሴት ኣዋቂ ሳይመርጡ
መስጊድ ሰብረው በመግባት
ደብድበው ለሰደቃ
የተዘጋጀ ከበሬ ጀምሮ
ሁሉንም ነገር ወሰዱ እንዴ? ክዛ
ኢሄንን
ያደረጉ ለፍርድ ይቅረቡ
ብላቹህ ኣገር በጠበጣቹህ ኣይደል?
ኣይደለም
ጭቆናው ይቁም
ብለን ኣንዋር መስጊድ ላይ
ኣስጠነቀቅናቸው
ከዛስ? ከዛማ በበነጋታው
ጥያቄያችንን እንዲያቀርቡ
የላክናቸውን
ኮሚቴዎች ኣሰሯቸው ለኣንድ
ወርም ማንም እንዳይጠይቃቸው
ኣደረጉ
እንዴ ከዛስ? ከዛ ቡሃላማ
በየመስጊዱ ኣህባሽ ኢማሞችን
እየቀየሩ
መስጊድ የተባለን ሁሉ
ነጠቁን እንዴ ከዛስ? ከዛማ በኣህባሽ
ኣንሰግድም ብለን በራሳችን
ኢማም ሁለተኛ ጀማአ መስገድ
ስንጀምር
እስሩ እና ዱላው ተጧጧፈ
እንዴ ከዛስ? ከዛማ ምንድነው ነገሩ
እያልን
ስንገረም በተለያዩ
ክልሎች ሆነ ብለው ብጥብጥ እያስነሱ
የብዙ
ሙስሊሞችን ህይወት
ቀጠፉ ኣሃ ከዛ ኣገሪቷን
ድብልቅልቋን
ኣወጣቹሃት ኣይደል? ኣይ
ይግረም ብለው በየቤቱ ፍተሻ ብለው
ሙስሊሙን መዝረፍ እንደውም
ኣንድ ቤት ኣንዲት የኣስራ ሰባት
ኣመት ልጅ
ደፈሩ ገባኝ ከዛ እቤት
ኣንመልስም ብላቹህ ወደ
ቤተመንግስት
ሄዳቹህ ኣይደል? ኣይ
እንደውም ኮሚቴው ኣሸባሪ ነው
ብለው
የሃሰት ፍልም ሰርተው
በስህተት ይሁን ወይም ምን ያመጣሉ
ብለው
እኛም እንድንፈራ
ሲያሰቃዯቸው የሚያሳይ ፊልም
ኣሳዩን ኣሃ
ከዛ ቡሃላ ነው ቤት
ኣንመለስም ያላቹህት? ኣይደለም
ከዛማ
የኢድ በኣላችን ላይ
መንግስት ፕላን ኣውጥቶ ህጻን
ወጣት ሴት
ኣዛውንት ሳይል በርካታ
ሙስሊሞችን ገድሎ ቁጥር ስፍር
የሌለውን
ህዝብ ኣቆሰለ በሺወች
የሚቆጠሩትንም ኣሰረ ገባኝ ያኔ
ትግስታቹህ
ኣለቀ ምን ኣደርርጋቹህ?
ምን እናደርጋለን ሙስሊሙን ሁለት
ሶስት
ሳምንት እያሰሩ ደጎም ባለ
ዋስ ሰበብ በቁሙ ዘረፉ እንዴ ባክህ
እኔ ቀልድ
ኣልፈልግም እውነቱን
ንገረኝ ከዛስ? ከዛማ በማሃል የሆኑ
ሰውዬን
ገድለው በሃሰት
ሙስሊም ወንድሞቻችንን
በማሰቃየት እኛ
ነን የገደልነው ኣስባሏቸው
ወይ ጉድ ከዛስ ከዛማ ከሁለት ቀን
በፊት
መንግስት ኣይዟቹህ
የሚላቸው ኣህባሾች ሃረር ወስጥ
ተሰበሰቡና
ኣህባሽ ያልሆነውን
ሙኣዚን ፈነካክተው ለቀቁት ኣሃ
ኣገሪቷ
በኣንድ እግሯ ቆመች በለኛ?
ኣይ ዛሬ ደግሞ ኣንድ የዩኒቨርሲቲ
ተማሪ
የነበረች እህታችን ከኣመት
በላይ መታሰሯ ሲገርመን መከላከያ
ኣቅርቢ
ተብላ ፍርድቤት ስትናገር
ኣራት ፖሊሶች ልብሷን ኣስወልቀው
እንደገረፏት ለፍርድ ቤት
መናገሯን ሰማን ኣሃ በቃ ተወው
ኣሁን ገባኝ
ለካ ኣንተም ሁሉንም
ታሪክ ስትነግረኝ በህይወት ያለህ
መስሎኝ
ነበር ኣውፍ በለኝ ለሙሉ
ኢትዮጲኣዊ ሙስሊም ኣለም ላይ
ባሉ
መስጊዶች ሁሉ ሰላተል ጀናዛ
እንዲሰገድልን ኣደርጋለሁ በል ኣሁን
ኢሄ
ዱንያን ማፍቀር ከኣንተ
እንዳይጋባብኝ ዞር በልልኝ ኣላህ
ሁላችንንም
ይቅር ይበለን።

ረመዳንን አስመልክቶ ሌሎች
ዑመቶች ያልተሰጡ ለዚህ ዑመት ብቻ
የተሰጡ አምስት ልዩ ነገሮች
ወንድሞቼ! እህቶቸ! የተከበረው ወር፣
ታላቁ ወርመጣላችሁ!! በውስጡ
አጅር የሚደራረብበት፣ የአላህስጦታ
የሚበረከትበት፣ መልካምን ፈላጊ
ሁሉ የበጐነገራት በሮች የሚከፈቱበት
የኸይር ወር፣ የበረካ ወር፣የስጣታና
የገፀበረከት ወር፡፡ የረመዳን ወር
ሰዎችመሪ፣ ከቀን መንገድና
(እውነትን ከውሸት)
ከሚለዩምገላጮች ሲኾን ቁርአን
የተወረደበት ነው፡፡ እዝነትናምህረት
ያካበበው ወር ነው፡፡እነዚህንና
ሌሎችንጉዳዮች በተመለከተ ብዙና
ግልፅ መረጃዎችከቀደመው
ትልውልድ ደርሶናል፡፡ ከአቢ
ሁረይራረዲየላሁ ዓንሁ፣ ተይዞ
እንደተወራው ነብዩ ( ﷺ)እንዲህ
ብለዋል “ረመዳን በመጣ ጊዜ የጀነት
በሮችይከፈታሉ፤ የእሳት በሮች
ይዘጋሉ፣ ሰይጣናትምይታሰራሉ፡፡”
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡
መልካም ስራዎች ስለሚበዙና
የሰራውንም ባለቤቶችለማበረታታት
የጀነት በሮች የሚከፈቱ
ሲኾንከሙእሚሞቹ ዘንድ ወንጀል
ሰለሚቀንስ የጀሀነምበሮች ይዘጋሉ
ሰይጣኖችም ይታሰራሉ፡፡
ኢማሙአህመድ አቡ ሁረይራን ረዐ
ጠቅሰው እንደዘገቡትነብዩ ሰዐወ
እንዲህ ብለዋል
“የእኔ ኡመቶች ረመዳንን
አስመልክቶከነሱ በፊት ማንም
ያልተሰጠውንአምስት ልዩ ነገሮች
ተሰጥተዋል፡፡ የአላህዘንድ የፆመኛ
አፍ ሽታ ልክ እንደሚስክሽታ ነው፣
እስከሚያፈጥሩ ድረስመላኢካዎች
ምህረትን ይጠይቁላቸዋል፣አላህ
በየቀኑ ጀነትን እያሰማመረመልካም
ባሮቼ የሚያስቸግራቸውንናየሚያስ
ከፋቸውን ነገር በመተው
ስራእንደሚሰርቁት አሁን
አይሰርቁምበመጨረሻው ሌሊት
ምህረትይደረግላቸዋል፡፡ የአላህ
መልዕክተኛሆይ ይህች ሌሊት
ለይለቱል ቀደር ናትን?ብለው ሰሃቦች
ጠየቋቸው፡፡ አይደለችምግና ሰራተኛ
ስራውን እንደጨረሰ ነውምንዳው
የሚከፈለው አሏቸው፡፡እነዚህ
አምስት ነገሮች ለሙስሊሞች ነው
የተዘጋጁት አላህ በሙስሊሞች ላይ
ፀጋዎቹን ሊያሟላ ከሌላው ህዝብ
በተለየ መልኩ ለሙስሊሞች አደረገ፡፡
“ እናንተበላጭ ህዝቦች ናችሁ፤
በመልካምታዛላችሁ፤ ከመጥፎ
ትከለክላላችሁበአላህም
ታምናላችሁ፡፡” ዘርዘር አርገን አንድ
በአንድ ስናያቸው
¤ የመጀመሪያው ገፀ በረከት የፆመኛ
የአፍ ሽታ ልክእንደሚስክ ነው አንድ
ሰው ከምግብ ሲርቅ አፉመጥፎ
ጠረን ያመጣል፡፡ ምንም እንኳን ይህ
ጠረንሰዎች ዘንድ የተጠላ ቢሆንም
አላህ ዘንድ ግንከሚስክ ሽታ የተሻለ
ጥሩ ሽታ ነው፡፡ ምክንያቱ
ደግሞአላህን በመታዘዝና በማምለክ
የመጣ ስለሆነ ነው፡፡ማንኛውም
አላህን በመተዘዝና በማምለክ
የመጣነገር እሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ
ነው፡፡ አላህ ለሰራውባለቤት የተሻለንና
በላጭን ነገር ይተካዋል፡፡
ስለዚያበአላህ መንገድ ላይ የአላህ
ቃል የበላይ ትሆን ዘንድሲዋጋ
ስለተገደለ ሰው ሰምተሃልን?
የውመል ቂየማቁሱሉ ደም እያፈሰሰ
ይመጣል፤ መልኩ ልክ እንደደምነው
ጠረኑ ደግሞ እንደሚስክ ነው፡፡
በሐጅ ጊዜበተመሳሳይ መልኩ አላህ
መላኢኮችን አረፋ ላይስለቆሙ ሰዎች
እንዲ ይላቸዋል “እነኝህን
ባሮቼንተመልከቱ፤ ፀጉራቸው
ተንጨባሮና አቧራ ለብሰውወደ እኔ
መጡ፡፡” አህመድና ኢብኑ
ሒባንዘግበውታል፡፡ እዚህ ቦታ ላይ
የፀጉር መንጨባረርአላህ ዘንድ
ተወዷል፡፡ መነሻው አላህን
መታዘዝናኢህራምን ላለመፍታት
እንዲሁም አለባበስንከማሳመር
መጠንቀቅ ስላለባት በመሆኑ ነው፡፡
¤ ሁለተኛው ገፀ በረካት መላኢካዎች
እስከ ሚያፈጥሩ ድረስ ምህረትን
ይጠይቁላቸዋልመላኢካዎች አላህ
ዘንደ የተከበሩ ካዘዛቸው
ዝንፍየማይሉ ከከለከላቸው
የማይቀርቡ ብፁአን ፍጡርናቸው፡፡
ለፆመኞች የሚያደርጉት ዱዓ በአላህ
ፈቃድላይ የተመሰረተ በመሆኑ
ተቀባይነቱ ጥርጥርየለውም፡፡ አላህ
ለዚህች ኡማህ መላኢካዎች
ዱዓእንዲያደርጉ መፍቀዱ የኡማዋን
ትልቅነት፣ የዝናውከፍ ማለትም
የፆማቸውንም ታላቅ ትሩፋት
ይገልፃል፡፡ምህረት (ኢስቲግፋር)
መፈለግ ማለት አንድ ሰውወንጀል
በዱንያ ሆነ በአኺራ ድብቅ
እንዲሆንለትይህችንም ወንጀል አላህ
እንዲያልፈው መጠየቅማለት ሲሆን
ይህ ደገሞ
ከምንፈልጋቸውናከምንመኛቸ ው
ነገሮች ሁሉ እጅግ በላጩ ነው፡፡
የአደም ልጆች ምንጊዜም ተሳሳቾችና
ድንበርአላፊዎት ናቸው በመሆኑም
የአላህን ምህረት
መከጀልይገባቸዋል፡፡
¤ ሶስተኛ ገፀ በረከት ሰይጣናት
በሰንሰለትና እግረ ሙቅ ይታሰራሉ
እስራቱ መልካም የአላህ ባሪያዎችን
እንዲያጠሙና ከሐቅ እንዳያዘናጋቸው
ያደርጋል፡፡ ይህም የእሳት ባልደረቦች
ይሆኑ ዘንድ ጥሪ የሚያደርጉ
ጠላቶቻቸውን በማገት አላህ ባሮችን
የገዘበት መንገድ ነው፡፡ በዚህ ወር
ላይ የሚታየው ከፍተኛ መልካም
ስራን ለመፈፀም የሚደረግ ጉጉትና
ከመጥፎ ነገር ለመታቀብ
የሚደረገው ጥረት የሰይጣናቱ
መታሰር ውጤት ነው፡፡
¤ አራተኛው ገፀ በረከት አላህ በየቀኑ
ጀነትን ያስውባታል ባሮቼ
የሚያስከፋቸውንና የሚያስጠላቸውን
ነገር እርግፍ አድርገው ትተው
ወዳንቺ መምጣትን ፈልገዋል፣
ቀርበዋል ይላታል፡፡ አላህ ለመልካም
ባሮቹ ለማዘጋጀት ያሰማምራታል
በየቀኑ ባሮቹ ለእሷ ያላቸው ጉጉት
ይጨምር ዘንድ፡፡ እንዲህም ይላታል
ባሮቼ የዱንያ ጣጣን ትተው
ሲያንገላታቸውና ሲያደክማቸው
ሲያስቸግራቸው የነበረን ነገር ሁሉ
በመተው በጐ ነገርን በመስራት ላይ
ታጥቀው ተነስተዋል፡፡ ወደ ሰላሟና
የክብረ ሀገሯ ጀነት የሚያደርሳቸው፣
የዱንያም የአኺራም ብቸኛ የደስታ
ምንጭም ይህ መሆኑን
አውቀዋል፡፡
¤ አምስተኛው ገፀ በረከት አላህ
በዚህ በተባረከ ወር ሌሊቶች
በተገቢው ሁኔታ ለሚቆሙ እና
ለሚፆሙ ለነብዩ ሙሐመድ ኡመቶች
ምህረትን ይለግሳቸዋል፡፡ ይህም
ሰዎች ስራቸውን በሚደመድሙበት
ጊዜ የሚከፍላቸው ትሩፋት ነው፡፡
ሰራተኞች የስራ ዋጋቸው
የሚከፈላቸው ሰራቸውን ሲያጠናቅቁ
ነውና፡፡ አላህ ለባሮቹ በሶሰት መልኩ
ችሮታውን ይለግሳቸዋል፡፡አንደኛ
ኃጢአትን ለማሰማር ደረጃን ከፍ
ለማድረግ የሚያስችልን መልካም
ስራ ባሮች እንዲሰሩ መደንገጉ
አንደኛው ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ባይኖር
ኖሮ አላህን በዚህ መልኩ ማምለክ
ባልቻሉ ነበር፡፡ ኢባዳ በራዕዩ መልክ
ከአላህ ወደ መልዕክተኛው ሰዐወ
የሚተላለፍ ነው፡፡ ለዚያም ነው
ከአላህ ውጭ ሸሪዓን ወይም ስርዓተ
ህግን የሚደነግጉ ሰዎችን ያወገዘውና
የሽርክ ስራ እንደሆነ የገለፀው፡፡
“ከሃይማኖት አላህ በርሱ
ያልፈቀደውን ለርሱ የደነገጉ
ተጋሪዎች ለነርሱ አሏቸውን?”
ሁለተኛ ብዙዎች ወደኃላ ያሉበትን
መልካም ስራ እንዲሰሩ አላህ
ገጠማቸው፡፡ የአላህ እርዳታና
መገጠም ባይኖር ኖሮ ለዚህ
ባልታደሉ ነበር ችሮታው የአላህ
ነውና፡፡ “በመስለማቸው በአንተ ላይ
ይመፃደቃሉ፤ በእስልምናችሁ በእኔ
ላይ አትመፃደቁ፤ ይልቁንም አላህ
ወደእምነት ስለመራችሁ
ይመፃደቅባችኃል፤ እውነተኞች
ብትሆኑ (መመፃደቅ ለአላህ ነው)
በላቸው፡፡” (አል ሑጅራት 17)
ሶስተኛአላህ ለኸይር ስራዎች ከፍተኛ
ምንዳን አዘጋጅቷል፡፡ አንድ ሀሰና
በአስር፣ በሰባት መቶ፣ በብዙ እጥፍ
ድርብ ተባዝቶ ይሰጠዋል፡፡ ይህ ችሮታ
የአላህ ነው፡፡ ምስጋና የተገባው
ይሁን፡፡ ወንድሞቼ! እህቶቼ!
የረመዷን መድረስ ትልቅ ፀጋ ነው
ሐቁን መወጣት ለቻለና አላህን
ከመወንጀል ትዕዛዛቱን ወደመፈፀም፤
ከዝንጋታ አላህን ወደ ማውሳት፤
ከአላህን መራቅ ወደ እሱ መመለስን
ምርጫው ላደረገ ሰው እውነትም
ታላቅ ፀጋ ነው፡፡
አንተ በረጅብ ወር ወንጀል ያልበቃህ
ከዚያም በሻዕባን የቀጠልክ አሁን
የፆም ወር
መጥቶልሃልእንደለመድከው
የኃጢአት ወር አታድርገው ቁርአንን
አንብብበት ተስቢህም አድርግበት
ባለፈው የፆም ነበረ ስንትና ስንት
ከቤተሰብ ከወንድሞች ከጐረቤት ግና
ወሰዳቸው አይቀሬው ሞት ለአንተ
ጊዜ ሰጠህ እንድትማርበት ጌታችን
ሆይ ጠልቀን ከገባንበት ዝንጋታ
አንቃን፣ ከሞታችን በፊት የተቅዋን
ስንቅ ሰንቀን፣ ጊዜያችንን በከንቱ
ከማባከን ጠብቀን፣ ለእኛም፣
ለወላጆቻችንም በጥቅሉ ለሁሉም
ሙስሊሞች ምህረትን ለግሰን አንተ
የአዛኞች አዛኝ ነህና፡፡
ድናችንንም እንወቅበት

ራስን ማሳደግ
እነሆ ረመዳን ደረሰ …
ለለውጥ እንዘጋጅ
( 4
Votes )
ስለ ለውጥ እስኪሰለች
ድረስ ብዙ እናወራለን፡፡
ብዙዎቻችንም ስለ ለውጥ
በተዘጋጁ ፕሮግራሞች ላይ
በተሳተፍንና ዳዕዋዎችንም
በሰማን ቁጥር ለለውጥ
እንነሳሳለን፡፡ በቅጽበትም
ለውጥን አስበን ጉዞ
እንጀምራለን፡፡ ሆኖም
ግን ብዙም ሳንጓዝ
እንቆማለን፡፡ ከመቆምም
አልፈን ወደኋላ
እንመለሳለን፡፡
ለመመለሳችን ምክኒያቶቹ
ብዙ ሲሆኑ እዚህን
ለማንሳት ጊዜውም
አይበቃንም፡፡
ልዩ የረመዳን መገለጫዎች
የወሮች ቁንጮ የሆነውና
ታላላቅ ችሮታዎችን ጠቅልሎ
የያዘው የረመዳን ወር
ከነሙሉ ስጦታው ሊሰፍር
እያንዣበበ ይገኛል። ታላላቅ
ትሩፋቶችን አዝሎ በአላህ
ፀጋዎች ደምቆ ልቦቻችንን
በብርሀኑ ሊሞላን አንድ ሁለት
እያለ ነው…፤ በመሰረቱ
የረመዳን ወር በሙስሊሞች
ልብ ውስጥ ምን ያህል ታላቅ
ቦታ እንዳለው ለማንም ድብቅ
አይደለም፤ አዎ! ረመዳን
የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት
ነፃ መውጫ ወር ነው፤ በዚህ
ወር ብዙ ስጦታዎችና
ልግስናዎች ከአላህ (ሱ.ወ)
ዘንድ ወደ ባሮቹ ይንቧቧሉ።
ከዚህ ቀጥለን ይህ ወር
ከሌሎች ወራት
የሚለይባቸውን መሰረታዊ
ነጥቦች እንመለከታለን።
የረመዳን ወር መለያዎች

የሙስሊሙ አንድነት እርፍት
የሚነሳቸው ትንሽ ክፍተት ሲያገኙ
አጋጣሚውን በመጠቀም ሙስሊሙ
ላይ ወዥንብር ለመፍጠር የሚጥሩ
ለዲናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደርሩ
ቅጥረኞችን ማወቅ ይፍልጋሉ???
አንገዲያውስ ከታች የተዘረዘሩትን
ሰሞች እና ሊንኮች በደንብ ይመልከቱ
ለሌሎችም ሼር በማድረግ በእነዚ
ግለሰቦች ስም ፖስት የሚደረጉ
ዜናዎች እንዲሁም ሌሎች ፅሁፎች
ከእውነት የራቁ መሆናቸውን
ያስገንዝቡ
1- amira oumer
https://
http://www.facebook.com /
amira.oumer
2- habib galbi
https://
http://www.facebook.com /
habib.galbi.5
3-yousuof ameen
https://
http://www.facebook.com /
profile.php?id=1
00003093878 805
4- africa muslims
https://
http://www.facebook.com /
eskandera2?fref= ts
5- mehdi hamidissa
https://
http://www.facebook.com /
mahdi.hamidissa
6- hasrolla rayudin
https://
http://www.facebook.com /
abduselam.awel.7
7-meryem bntel halal
https://
http://www.facebook.com /
meryem.bintelhal al.1
8- mohammed mohamed
https://
http://www.facebook.com /
mohammed.mohamed .106
9- umer al faruq
https://
http://www.facebook.com /
rabia.mustfa
10- ቆራጡ የኢስላም ልጅ
https://
http://www.facebook.com /
bint.mesud?hc_lo
cation=timeline
11- akrem ezedin
https://
http://www.facebook.com /
akrem.ezedin.5
12- አዛን አህባሽ
https://
http://www.facebook.com /
umria.haji
13- hizaki hesru
https://
http://www.facebook.com /
hizaki.nesru
14- ahbash peace
https://
http://www.facebook.com /
ahbash.peace
15- nejashi al habashiyy
https://
http://www.facebook.com /
nejashi.habashiy y
16- ከድር ጋሹ
https://
http://www.facebook.com /
pages/ከድር-ጋሹ/
137945256382601
17- ked peace full
https://
http://www.facebook.com /
semiramuhammed.a
hmed?hc_locatio
n=timeline
18- abdulkadir hajibushra
https://
http://www.facebook.com /
hajibushra
19- temam ahmed
https://
http://www.facebook.com /
temam.ahmed.3
20- abdellah islam leader
https://
http://www.facebook.com /
abdellah.ezedin
21- neim seid
https://
http://www.facebook.com /
neim.seid.35
22- anwar yimam
https://
http://www.facebook.com /
anwar.yimam.921
እነዚ ከላይ የተዘረዘሩት ጥቂቶቹ
ሲሆኑ በሌላ ጊዜ የሌሎቹንም ስም
እና ሊንክ በተመሳሳይ መልኩ ፖስት
አደርገዋለው
አብዛኛው አካውንት አንድ ግለሰብ
የሚያንቀሳቀሰው እንደሆነም
ልትገነዘቡ ይገባል ለነዚ ሰዎች
ኮመንት ከመስጠት በመቆጠብ
የማያቃቸው ሰው አንዳይወዛገብ
ይረዳው ዘንድ የነዚን ተላላኪ
ቅጥረኞች እኩይ ተግባር እናጋልጥ
ሰራቸውን እናክሽፍ
ድል ለሙስሊሞች!!!
ድል በአምባገነን መንግስት
ነጻነታቸውን ለተነፈጉ የኢትዮጲያ
ልጆች!!!
ድምጻችን ይሰማ !!!
አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ
አክበር አላሁ አክበር አላሁ አክበር
አላሁ አክበር!!!

የረመዳን ወር አቀባበል
( 21
Votes )
ታላቁ እንግዳችን!
የተከበረውን የረመዳን ወር
ለመቀበል ሁሉም በየፊናው
ተፍተፍ እያለ ይገኛል። ከፊሉ
ቤቱን በማሰናዳት፣ ሌላው
የምግብ አይነቶችን
በመሸመት፣ እኩሉም የወሩን
ትሩፋት ለመጠቀም እቅድ
እያወጣ…ወዘተ እየተንቀሳቀሰ
ይገኛል።
ለመሆኑ ይህ አያሌ የፈጣሪ
ትሩፋትን በውስጡ ይዞ
የመጣውን ይህን ወር
ለመቀበል ትክክለኛው መንገድ
የትኛው ነው?
በወሩ ውስጥ ያሉትን
እያንዳንዱን የጦዓ (አምልኮ)
ወቅቶችን ሁሉ አሟጦ
ለመጠቀም ምን ማድረግ
ይጠበቅብናል? በነዚህ በተከበሩ
ጊዜያት ውስጥ በኸይር ነገሮች
መሽቀዳደም ያስፈልጋልና፤
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﻓِﻲ ﺫَٰﻟِﻚَ ﻓَﻠْﻴَﺘَﻨَﺎﻓَﺲِ
ﺍﻟْﻤُﺘَﻨَﺎﻓِﺴُﻮﻥَ ] ٨٣:٢٦ [
“በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች
ይሽቀዳደሙ።” (አል-
ሙጦፊፊን 83፤ 26)
በመሆኑም ከዚህ በመቀጠል
የረመዳንን ወር በተሻለ
መንገድ ለመቀበል የሚረዱ
መንገዶች እንጠቁማለን፡-
1. ዱዐ ማድረግ፡- በፆም፤
በሶላትና በዚክር ላይ
እንድትጠነክር አላህ (ሱ.ወ)
በሙሉ ጤንነትና አቅም ላይ
ሆነህ ረመዳን ወር
እንዲያደርስህ ከአሁኑ ዱዓ
አድርግ፤ አነስ ቢን ማሊክ
(ረ.ዐ) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ)
የረጀብ ወር ሲገባ እንዲህ ይሉ
ነበር ብለዋል፡- “አልላሁመ
ባሪክ ለና ፊረጀብ ወሸዕባን
ወበሊግና ረመዳን” – “አላህ
ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ብሩክ
አድርግልን፤ ረመዳንንም
አድርሰን” (አህመድና ጦብራኒ
ዘግበውታል)።ሰለፎች
(ቀደምት ደጋግ አቦዎች)
ረመዳንን እንዲያደርሳቸውና
ከዚያም ሥራቸውን
እንዲቀበላቸው አላህን (ሱ.ወ)
ይለምኑ ነበር፤ ስለዚህ አንተም
የረመዳን ጨረቃ ስትወጣ
እንዲህ ብለህ ዱዓ አድርግ፡-
“አላሁ አክበር አላሁመ አሂለሁ
ዐለይና ቢል አምኒ ወል ኢማን፤
ወስሰላመቲ ወል ኢስላም፤
ወትተውፊቅ ሊማ ቱሂቡሁ
ወተርዳህ፤ ረቢ ወረቡከላህ፤” –
“አላሁ አክበር አላህ ሆይ! ይህን
ጨረቃ የአማንና የኢማን፣
የሰላምና የኢስላም፣ እንዲሁም
አንተን የሚያስደስት ተግባር
መስራት የምንችልበት ጊዜ
አድርግልን፤ የኔም የአንተም
ጌታ አላህ ነው፤” (ቲርሚዚ
ዘግበውታል)።
2. ምስጋና ማቅረብ፡- ረመዳን
ወር ከደረስክ ምስጋና ለአላህ
አቅርብ፤ ኢማሙ ነወዊይ
አል-አዝካር በተባለው
ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ
ብለዋል “አንድ አዲስ ፀጋን
ያገኘ ወይም አንድ ችግር
የተወገደለት ሰው ለአላህን
ምስጋና ለማቅረብ ሱጁድ
አድረጎ አላህን በሚገባው
መልኩ ማወደስ ይገባዋል።
”አላህን ማምለክና የሱን
ትእዛዝ መፈጸም መቻል በራሱ
አላህ (ሱ.ወ) ለአንድ ሙእሚን
ከሚለግሰው ታላላቅ ፀጋዎች
ነው። አንድ ሙእሚን
የረመዳን ወር ሲገባ በጥሩ
ጤንነት ላይ መገኘቱ ብቻ
ፀጋውንና ችሮታውን ለለገሰው
አላህ (ሱ.ወ) ምስጋና
እንዲያቀርብ የሚያስገድደው
በቂ ነገር ነው፤ ስለዚህ
የረመዳንን ወር በሰላምና
በጤና የደረሰ ሰው ለአላህ
(ሱ.ወ) ትልቅ ምስጋና
ሊያቀርብና እሱን በብዛት
ሊያወድስ ይገባል፤ ለልቅናውና
ለግዙፍ ስልጣኑ የሚመጥን
ታላቅ ምስጋናና ውዳሴ ለአላህ
(ሱ.ወ) ይሁን!!
3. መደሰት፡- ነቢያችን
(ሰ.ዐ.ወ) የረመዳን ወር ሲመጣ
እንዲህ በማለት
ባልደረቦቻቸውን ያበስሩ
እንደነበር ተረጋግጧ፡-
ﺟﺎﺀﻛﻢ ﺷﻬﺮ ﺭﻣﻀﺎﻥ
ﺷﻬﺮ ﻣﺒﺎﺭﻙ ﻛﺘﺐ ﺍﻟﻠﻪ
ﻋﻠﻴﻜﻢ ﺻﻴﺎﻣﻪ ﻓﻴﻪ ﺗﻔﺘﺢ
ﺃﺑﻮﺍﺏ ﺍﻟﺠﻨﺎﻥ ﻭﺗﻐﻠﻖ ﻓﻴﻪ
ﺃﺑﻮﺍﺏ ﺍﻟﺠﺤﻴﻢ
“የተባረከው
የረመዳን ወር መጥቶላችኋል፤
እሱን መፆም አላህ (ሱ.ወ)
በናንተ ላይ ደንግጓል፤
በረመዳን ወር የጀነት በሮች
ይከፈታሉ፤ የገሀነም በሮች
ደግሞ ይዘጋሉ” (አህመድ
ዘግበውታል)።
ሰሐባዎችንና ታቢዒዮችን
ጨምሮ ያለፉት ደጋግ አቦዎች
(ሰለፎች) ለረመዳን ወር ልዩ
ትኩረት ይሰጡ ነበር፤ ረመዳን
ሲመጣም ይደሰቱ ነበር፤ አዎ
ይህ ትልቅ ደስታ ነው! የኸይርና
የአላህ እዝነት መውረጃ የሆነ
ወቅት ሲመጣ ጤና ሆኖ
በሂይወት ከመኖር የበለጥ
የሚያስደስት ነገር አለን?!
4. ወሩን በአግባቡ ለመጠቀም
መወሰንና ቀድሞ እቅድ
ማውጣት ፡- ብዙ ሙስሊሞች-
ዲነኞችን ጨምሮ- ለዱንያ
ጉዳያቸው በሚገባ እቅድ
ሲያወጡ ይታያሉ፤ ነገር ግን
ለአኺራቸው እቅድ በማውጣት
የሚሰሩት ጥቂቶች ናቸው።
ይህም የሚሆንበት ምክንያት
ሙእሚን በዚች ህይወት
ያለውን መልዕክት ካለመረዳትና
አንድ ሙእሚን ነፍሱ በአላህ
ዲን ላይ ፅናት እንዲኖራት
ራሱን ለማለማመድ ከአላህ
ዘንድ የሚገኙ መልካም
አጋጣሚዎች ችላ ከማለት
የሚመነጭ ነው።
ለአኺራ ከምናቅድባቸው
ጉዳዮች መካከል የረመዳንን
ወር በጧዐና ኢባዳ ለማሳለፍ
የምናደርገው ዝግጅትና እቅድ
አንዱ ነው፤ ስለሆነም
ማንኛውም ሙስሊም
የረመዳንን ወር በትክክል
አላህን በመታዘዝ ማሳለፍ
እንዲችል ተግባራዊ ሊሆን
የሚችል ፕሮግራም ማውጣት
ያስልገዋል።
5. ቁርጠኛ አቋም፡-
የረመዳንን ወር በመልካም
ሥራዎች ለመሙላት ቁርጠኛ
አቋም መያዝ። ከልቡ
በእውነት ወደ አላህ የቀረበ
ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ እሱን
ለመገዛትና ኸይር ለመስራትም
ያግዘዋል፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ
ይላል፡-
ﻓَﻠَﻮْ ﺻَﺪَﻗُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﻜَﺎﻥَ ﺧَﻴْﺮًﺍ
ﻟَّﻬُﻢْ ] ٤٧:٢١ [
“እውነተኞች በኾኑ ኖሮ
ለእነርሱ የተሻለ በኾነ
ነበር።” (ሙሐመድ 47፤
21)
6. የረመዳን ህግጋትን
መማርና መረዳት፡-ሙእሚን
አላህን መገዛት ያለበት
በእውቀት ላይ ተመስርቶ ነው።
አላህ (ሱ.ወ) በባሮቹ ላይ ግዴታ
ያደረጋቸውን ነገሮችና
አፈጻጸሙን አለማወቅ
ማንኛውም ሙስሊም ይቅርታ
ሊደረግለት የማይችል ጉዳይ
ነው። ማወቅ ግደታ ከሚሆኑት
ነገሮች መካከል የረመዳን ፆም
አንዱ ነው፤ ስለዚህ ማንኛውም
ሙስሊም ረመዳን ከመግባቱ
በፊት ፆሙ ትክክለኛና አላህ
ዘንድ ተቀባይነት ያለው
እንዲሆን ስለ ፆም ህግጋቶች
(አህካም) መማርና ጠንቅቆ
ማወቅ ይገባዋል። አላህ
(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
ﻓَﺎﺳْﺄَﻟُﻮﺍ ﺃَﻫْﻞَ ﺍﻟﺬِّﻛْﺮِ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ
ﻟَﺎ ﺗَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ ] ٢١:٧ [
“የማታውቁም ብትኾኑ
የመጽሐፉን ባለቤቶች
ጠይቁ።” (አል-አንቢያእ
21፤ 7)
7. ተነሳሽነትን መጨመር፡-
የፆምን ትሩፋቶች (አጅር/
ፈዳኢል) እና ህግጋቶች
የሚያብራሩ የተለያዩ
መጽሀፍትን በማንበብና
ካሴቶችን በማዳመጥ ለረመዳን
ፆም የሥነ-ልቦናና መንፈሳዊ
ዝግጅት ማድረግ ይገባል።
ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረመዳንን
ወር በአግባቡ እንዲጠቀሙበት
ባልደረቦቻቸውን ሲያዘጋጇቸው
የሸዕባን ወር መጨረሻ ቀን
ላይ “የረመዳን ወር
መጣላችሁ…” ይሉ ነበር፤
(አህመድ ዘግበውታል)።
8. ንሰሀ፡-የረመዳንን ወር
ከወንጀል ሁሉ ለመራቅ፣
ለመፅዳትና ወደ ወንጅል
ላለመመለስ ወስነንና እውነተኛ
ተውበት በማድረግ ወደ አላህ
ለመመለስ ቆርጠን ልንቀበለው
ይገባል። እንደሚታቀወቀው
ረመዳን የተውበት ወር ነው፤
በዚህ ወር ያልቶበተ (ወደ አላህ
በንሰሀ ያልተመለሰ) ሰው መቸ
ይመለሳል ተብሎ ይታሰባል?!
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﺃَﻳُّﻪَ
ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ
] ٢٤:٣١ [
“ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ
ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ
(በመመለስ)
ተጸጸቱ።” (አን-ኑር 24፤
31)
9. ዳዕዋ፡- በረመዳን ወደ አላህ
(ሱ.ወ) ደዕዋ (ጥሪ) ለማድረግ
በጥሩ ሁኔታ መዘጋጀት፤
ለዚህም፡-
በመስጅድ ውስጥ የሚሰጡ
ሙሀደራ (ስብከት) የሚሆኑ
ጥሩ መልእክት ያላቸውን
ፅሁፎች ከወዲሁ አዘጋጅቶ
መያዝ፤
የረመዳንን ወር የተመለከቱ
ትንንሽ መጽሐፍትን /
ፓምፍሌት/ አዘጋጅቶ
ለሰጋጆችና ለአካባቢ ሰዎች
ማሰራጨት፤
የረመዳን ስጦታ ማዘጋጀት፤
ለምሳሌ አንድ ፖስታ ውስጥ
ሁለት ካሴቶች /ሲዲ/ እና አንድ
ትንሽ መጽሐፍ አሽገን ከላዩ
ላይ (የረመዳን ስጦታ) ተብሎ
ሊጻፍበት ይችላል፤
ድሃዎቸን ማስታወስና
የምስፅዋትና ዘካ ገንዘብ
አሰባሰብን ከወዲሁ ማቀድ፤
10. አዲስ ምእራፍ፡-
ረመዳንን አዲስና ንፁህ
ምዕራፍ በመክፈት ልንቀበለው
ይገባል፤ ይህም የሚሆነው
ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር ባለን
ግንኙነት ትክክለኛ እውነተኛ
ተውበት በማድረግ
መልክተኛውም (ሰ.ዐ.ወ)
ያዘዙንን በመተግበርና
የከለከሉንን በመራቅ
ለወላጆቻችን፤ ለቤተሰባችንና
ለዘመዶች ጥሩ በመዋል
ዝምድናችንን ማጠናከር
ከምንኖርበት ማህበረስብ ጋር
አዲስ ምዕራፍ በመክፈት
መልካምና ጠቃሚ ሰው ሆንን
መገኘት፤ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ይላሉ፡ ﺧﻴﺮ ﺍﻟﻨﺎﺱ
ﺃﻧﻔﻌﻬﻢ ﻟﻠﻨﺎﺱ ከሰዎች“
በላጩ ለሰዎች የሚጠቅም
ነው”።
አዎ! ደረቅ መሬት ዝናብን
እንደሚቀበል፤ በሽተኛ
ሐኪምን እንደሚቀበልና
አፍቃሪ ተለይቶት የቆየ
ወዳጁን ሲያገኝ በጉጉት
እንደሚቀበለው ሁሉም
ሙስሊምም የረመዳንን ወር
በከፍተኛ ጉጉት ይቀበላል።
ያ አላህ! ረመዳን አድርሰን
ከኛም ተቀበለው፤ አንተ ሰሚና
አዋቂ ነህና። አሚን!
Share this post

ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም /ኢየሩሳሌም አርአያ /

Freedom4Ethiopian

ሰላይ ሴት
ዝማም ትባላለች፤ የሕወሐት ታጋይ ናት። ባለቤቷ አቶ ቢተው በላይ ይባላሉ። ቢተው እስከ1993 ዓ.ም የደቡብን ክልል በበላይነት ሲያሽከረክሩና ሲመሩ የቆዩ ናቸው። በመጋቢት 93 ከአቶ መለስ ጋር በተፈጠረ የፖለቲካ ውዝግብ ከሌሎች ጋር ተነጥለው ወጡ። ከዚያም ከደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ ጋር በሙስና ተከሰው ዘብጥያ ወረዱ። ፍ/ቤት መቅረብ እንደጀመሩ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ጋር ለዜና ዘገባ ስንመላለስ የቢተውን ባለቤት ዝማምን ተዋወቅኳት። በክልል 14 ቢሮ ተመድባ ነበር የምትሰራው። ባለቤትዋ ከታሰረ በኋላ ግን ዝቅ ተደርጋ በቀበሌ ደረጃ ተመደበች። ዝማም በርካታ ምስጢሮችን ታውቃለች። አርከበ ወደ ከንቲባነት ሊመጡ እንደሆነና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን አቀብላኝ በኢትኦጵ ጋዜጣ ሰርቼዋለሁ። ..ዝማምን ዛሬ እስር ቤት የሚገኘው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴና አየር መንገድ ያለው ሃይሌ አጠመዷት። የሕወሐት ነወረኛ ደህንነቶች ጋር መጠጥ እየተጋተች አንሶላ እንደተጋፈፈች ስገልጽ ከልብ እያዘንኩና ይህን ዘገባ ለምታነበው ሴት ልጇ እየተሸማቀቅኩ ነው። ነገር ግን ይህን ነውረኛ ድርጊቷን ባልዋ አቶ ቢተው እስር ቤት ሆኖ ያውቅ ነበር። እቤቱ ውስጥ በፓርቲው አንጃዎች ይካሄድ የነበረ ስብሰባ እየተቀረጸ አቶ መለስ ዘንድ ተልኳል። ይህ ሁሉ በዝማም…

View original post 119 more words

ፈንጅ አምካኝ ወታደሮች በብሄራችን የተነሳ አድሎ ተፈጽሞብናል ሲሉ ተናገሩ

Abraham's view

ፈንጅ አምካኝ ወታደሮች በብሄራችን የተነሳ አድሎ ተፈጽሞብናል ሲሉ ተናገሩ
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዩ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ፈንጅ ያመክኑ የነበሩ ወታደሮች እስከዛሬ ለከፈልነው መስዋትነት ከ3 እስከ 7 ሺ ብር ብቻ እየተሰጠ፣ ብሄራችን እየተመረጠ ከመከላከያ እንድንሰናበት ተደርገናል ብለዋል።
ሰሞኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ተክለብርሃን ወ/ዓረጋይ ወደ አማራ፣ ኦሮምያና ደቡብ ክልሎች ተዘዋውረው ወታደሮችን ያነጋገሩ ሲሆን “ጊዜው ለልማት እና ለስራ የሚነሳሱበት እንጅ አድማ በመምታት ነገር የሚያሰሩበት አይደለም” በማለት አስጠንቅቀዋቸዋል።
“የግፍ ግፍ ተፈፅሞብናል” ያሉት ፈንጅ አምካኝ ወታደሮች፣ ከፍተኛ መስዋትነት የከፈልነው የአማራ ኦሮሞ እና ደቡብ ብሄር ተወላጆች ከስራ እየተሰናበትን የህወሃት አባላት አዲስ ምልምል ወታደሮች የስራ እድል እየተሰጣቸው ነው በማለት በተለይ በሰላም አስከባሪ ስም እየተፈጸመ ያለውን አድልዎ በማንሳት ተቃውሞቸውን አሰምተዋል፡፡
200 የሚደርሱ በአባይ ግድብ ተቀጥረው እንዲሰሩ የተደረጉ ፈንጅ አምካኞች “አታስፈልጉም” ተብለው መባረራቸውንም አውስተዋል፡፡
በሶስቱ ክልሎች መስዋትነት ከፍለን በብሄራችን የተነሳ ከስራ ተባረርን የሚሉ 513 ፈንጅ አምካኝ ወታደሮች አሉ።
ከደህንነት ክፍል የተገኙው መረጃ እንደሚያሳየው መንግስት የሶስቱ ክልል ፈንጅ አምካኝ ተወላጅ ወታደሮች ላይ…

View original post 17 more words

በቨርጂኒያ በደረሰ አሳዛኝ የመኪና አደጋ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ሲሞቱ አንዱ በጠና ቆስሏል

Freedom4Ethiopian

ትላንት ማክሰኞ ማታ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ክፍለ-ግዛት ዋሽንግተን በተባለ አውራጃ ውስጥ 81 ተብሎ በሚጠራው አገር አቋራጭ መንገድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ሲሞቱ አራተኛው በሄሊኮፕተር ወደ ሆስፒታል ተስዶ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጾል::
የሞቱት ሶስቱ ወጣቶችም የሚከተሉት ናቸው:-
1ኛ) አቤናዛር ቴዎድሮስ የ19 አመት (ሹፌር)
2ኛ) አቤል አየለ የ19 አመት (አብሮ ተጓዥ)
3ኛ) አለሙ አምሃ የ25 አመት (አብሮ ተጓዝ)
በጠና ቆስሎ ሆስፒታል የሚገኘው አርከጻዲቅ ይልማ የተባለ የ19 አመት ወጣት ነው::
ፓሊስ እንዳለው አደጋው የተፈጠረው አቤናዛር ሲያሽከረክረው የነበረው ቶዮታ የቤት መኪና የመንገዱ ዳር ላይ ጎማ ተንፍሶበት የቆመ ትልቅ የጭነት መኪና ሲገጭ ነው:: በግጭቱ ወቅት የጭነት መኪናው ባለቤትና ተሳፋሪዎች ከመኪናው ውጭ ስለነበሩ በማናቸው ላይ አደጋ አልደረሰም::
አደጋው አሁንም በፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ቢሆንም ከአልኮል መጠጥ ጋር የተያያዘ እንደማይመስል ተጠቅሷል::
ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን ይመኛል::

posted by Aseged Tamene

View original post