በሑመራ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 የተገደሉትን የኢህአዴግ ሰራዊት አዛዦች ለቤተስባቸው የሚሆን ገንዝብ እንዲያዋጡ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለጸ።

Freedom4Ethiopian

aseeበሑመራ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 የተገደሉትን የኢህአዴግ ሰራዊት አዛዦች ለቤተስባቸው የሚሆን ገንዝብ እንዲያዋጡ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለጸ።

View original post 69 more words

ፍርድ ቤቱ አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲቀለቀቅ ወሰነ

Freedom4Ethiopian

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር11212178_449222835253952_5616984280646183603_o
የአራዳ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሃሴ 22/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ አደራጅቶ መርቷል እንዲሁም ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡
አቃቤ ህግ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አቶ ማሙሸት ገንዘብ ከፍሎ ወጣቶችን ሰልፍ እንዳስወጣቸው፣ ወጣቶችን እንዳደራጀ፣ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም መንግስትን የሚተቹ መፈክሮችን በመሪነት ሲያሰማ እንደነበርና ለሚያዝያ 14 ሰልፍም ሲያደራጅ እንደነበር ያስረዱልኛል ያላቸውን ሶስት የሰው ምስክሮችን ማሰማቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የግል ሰራተኛ እንደሆነ በምስክርነት ቃላቸው ቢሰጡም በመስቀለኛ ጥያቄ አንደኛው የመንግስት ሰራተኛ፣ ሁለተኛው የወጣቶች ሊግ ከዚህም አለፍ ሲል የኢህአዴግ አባል፣ ሶስተኛው ደግሞ የጥቃቅንና አነስተኛ ባልደረባ መሆናቸውን በማመናቸው የሰጡት ምስክርነት ትክክል አለመሆኑን ያስረዳል ብሏል፡፡ በተጨማሪም ምስክሮቹ ገዥው ፓርቲን የሚደግፉና የወጣት ሊግ አባል ሆነው ገዥው ፓርቲን የሚቃወም ግለሰብ ላይ የሰጡት ምስክርነት ገለልተኛ ነው ብሎ ለማመን ያስቸግራል ብሏል፡፡
ከዚህም ባሻገር ምስክሮቹ…

View original post 130 more words

የማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት ማምረቻ ክፍል ቃጠሎ ደረሰበት

Free Freedom Alone

kidusan

ማህበረ ቅዱሳን በድረገጹ እንደዘገበው:-በማኅበረ ቅዱሳን የልማት ተቋማት አስተዳደር የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻ ክፍል ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ቃጠሎ እንደደረሰበት የልማት ተቋማት አስተዳደር ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ፍስሐ ገለጹ፡፡ መረጃው ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እንደደረሳቸው የገለጹት አቶ ኃይሉ በማምረቻ ክፍሉ ተከስቶ የነበረውን ቃጠሎ በአካባቢው ሕዝብና በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ወረዳ የእሳት አደጋ ማጥፊያና መቆጣጠሪያ ክፍል አባላት ርብርብ ወደ ሌሎች ክፍሎች ሳይዛመት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በቃጠሎው 12 የልብስ ስፌት ማሽኖች፤ 2 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ካውያዎች፤ 1 መዘምዘሚያ ማሽን፤ 1 ቁልፍ መትከያ ማሽን፤ በዝግጅት ላይ የነበሩና ያልተጠናቀቁ፤ ለስፌት የሚያገለግሉ የግሪክ ጨርቆች፤ የካህናት፤ የዘማርያንና የሰባኪያን አልባሳት፤ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጁ አልባሳት፤ የግሪክ ጣቃ ጨርቆች፤ የማምረቻ ክፍሉ በሮች፤ መስኮቶችና ኮርኒስን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡ ግምታቸውንም ለጊዜው ማወቅ እንዳልተቻለ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ ቀኑን ሙሉ መብራት ጠፍቶ ስለነበር ምንም ዓይነት ሥራ አገልጋዮቹ እንዳለከናወኑ የገለጹት ዳይሬክተሩ ቃጠሎው የተከሰተው አገልጋዮቹ ከወጡ በኋላ በመሆኑ የአደጋው መንስኤ እሰካሁን አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡ አደጋው…

View original post 81 more words

የአርበኞች ግንቦት 7 መልዕክት

Freedom4Ethiopian

asee

የግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው። በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።

በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን…

View original post 333 more words

ሰበር ዜና በሽብር ክስት ታስረው የነበሩት እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ከእስር ተፈቱ።

Freedom4Ethiopian

11035502_771235849624393_3401706099381023667_n

ጀግኖቹ እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ሓሙስ 14 / 12 / 2007 ዓ/ም ከእስር በነፃ ተፈቱ።

ከዓመት በፊት በሽብር ክስት ታስረው የነበሩት ጀግኖቹ የሰለማዊ ትግል ጀግኖች ከተከሰሱበት የፈጠራ ክስ ነፃ ተብለው ተፈትተዋል።

፩) ኣብራሃ ደስታ ከዓረና

፪) ሃብታሙ ኣያሌው ከኣንድነት

፫) የሺዋስ ኣሰፋ ከሰማያዊ

፬) ዳኑኤል ሺበሺ ከኣንድነት
ከተከሰሱበት የሽብር ክስ በነፃ ተሰናበቱ።

ለመላው ኢትዮዽያውያን ስለነዚህ ጀግኖች መታሰር የተጨነቃቹ ወገኖች እንኳን ደስ ኣላቹ።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

View original post

የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል።

Freedom4Ethiopian

የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል።

እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” ኣርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው። “ኣባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በሗላ ድርጅቱ ኣጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ ኣባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው ኣጥብቀው በመያዝ ኣሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ ኣምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል። ወፍ የለም “ኣባይ ደራ ” የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል።

ኣባይ ወልዱ የቴሌው…

View original post 76 more words

የ77 ንጹሃን ህይወት የቀጠፈው አንዲሪው ብራቪክ ጋር ፍቅር የያዘኝ ያለች ወጣት ራስዋን አጋለጠች )የሳምንቱ ታላቅ ዜና በDCESON ሬድዮ ይከታተሉ

Freedom4Ethiopian

በኖርዌጃውያን ማህበረስብ  እጅግ የሚጠላው አንዲሪው ብራቪክ በፈጸመው አ ስቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋ ክስ የ21 እስር የተፈረደበት ቢሆንም ከ 2012ጀምሮ  በአመት ከ800 የሚልቅ የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚደርስው ሲሆን 2 መስረት ያለው የግድያ ዛቻ ደብዳቤዋች እንደደረሱት ዳገ ብላዴት ዘገባዋል

እነዚህን ኒያ ናትዚ ያላችውን ደጋፊ ግለስቦች  ደብዳቤ ለማስተናገድም 5 ቋሚ ፖሊሶች እንደተቀጠሩ የእስርቤቱ ሀላፊ ገልጸጹ ሲሆን እስካሁን ለብራቪክ ከሚደርሱት የፍቅር የድጋፍ  እና  የትዳር ደብዳቤዋች መካከል  150 እንደላከች ያመነችው አንዲት ስዊድናዊ ወጣት ስምዋን ለግዜው ግልጽ ላለማድረግ ቪክቶርያ  በሚል ስም በመጠቀም ቃልዋን ስታለች፣  በሃያዎቹ እድሜ  የምትገኘው ይህች ወጣት በጤና  ችግር ምክንያት ስራ  መስራት እንደማትችል ገልጻ ከዚህ  የተጠላስው ጋር ፍቅር እንደያዛትና  ከሱ ውጪ ህይወት እንደሌላት ለአፍተን ፖስተን ጋዜጣ አስታውቃለች   ለላከቻችው 150 ደብዳቤዎችም 2 የምላሽ ደብዳቤ አግኝታለች ሆኖም በአካል ለማግኘት ያደረገችው በርካታ  ሙከራዎች  ውድቅ እንደተደረባት ገልጻለች የስነአይምሮ ተመራራሪዎች  ሀይብርስሮ=ፌሊያ በመባል የሚታወቀው የስነ አይምሮ  ችግር  ሲሆን አንዳንድ  እንስቶች ይህንን መስል ተስፋ  የሌላችው ስዎችን የማፍቀር ችግር እንደሚጠናወታችው የነገራል በድርጊታችው ዝናን ለማትረፍ የሚሹም እንዳሉ የዌስሊያን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፐሮፌስር አማንዳ  ቪካሪ በጉዳዩ ማብራሪያ …

View original post 33 more words

ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስተርነታቸው ይቀጥላሉ ተባለ

Free Freedom Alone

በአሁኑ ወቅት በሶሥቱ ትላልቅ ፓርቲዎች ውስጥ የተፈጠረው አለመተማመን ሃይለማርያም በቦታቸው እንዲቆዩ እንደኢያደርጋቸው የሚገልጹት ምንጮች በተለይም በብ አዴን እና በ ኦህዴድ ውስጥ ተገቢ የሚባል ጥያቄ የሚጠይቁ አባላትን በሙስና ለማሰር ሃሳብ እንዳለ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል::

ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን በያዝነው ወር ድርጅታዊ ጉባኤያቸውን በተናጠል በማካሄድ እያንዳንዳቸው ዘጠኝ አባላት ያሏቸውን የሥራ አስፈፃሚ አባላትን የሚመርጡ ሲሆን እነዚህ አባላትም በያዝነው ወር መጨረሻ ወይንም በመስከረም ወር መግቢያ በመቀሌ ከተማ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ የግንባሩን ሊቀመናብርት ይመርጣሉ ተባሏል:: የኢሕ አዴግ ሊቀመንበርም ሃይለማርያም ደሳለኝ ሆነው እንደሚቆዩና ሆኖም ግን ሌሎች ድርጅቱን ብዙ ዓመት አገልግለዋል የተባሉ ባለስልጣናት እንደሚሸኙ ተገልጿል::

የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ቦታን ሕወሓቶች አሁንም የሚፈልጉት ሲሆን የራሳቸውን ሰው ለማስቀመጥ ከላይ ታች እየተሯሯጡ ይገኛሉ:: ሆኖም ግን እርስ በ እርሳቸው መግባባት ስላልቻሉ ኃይለማርያም እንዲቀጥሉ ምክንያት ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል::

Posted By/Lemlem Kebede

View original post

አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ ማራሚያ ቤት ታዬ!

Freedom4Ethiopian

10527591_777173005661004_6003304103558780783_nአርበኞች ግንቦት ሰባትን በ አሸባሪነት በምዕራባዊያን ዘንድ ለማስፈረጅ ያደረገው ከንቱ ውትወታ ያልሰመረለትና በተቃራኒው ጫናው የበረታበት ወያኔ የነጽነት ኮከቡን አንዳርጋቸው ጽጌ ሰውሮ ካስቀመጠበት ያፈና እስር ቤት ወደ ቃሊቲ ተዛውሮ መታየቱ ታወቀ።

ከየመን አየር ማረፊያ ትራንዚት ላይ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እስከዛሬ በማይታወቅ ቦታ ታስሮ ከፍተኛ ቶርች እየተፈጸመበት ሲሆን ባለፈው ሊጠይቁት የሄዱት የእንግሊዝ አምባሳደር እንዳሉት አንዳርጋቸው ካለሁበት ሁኔታ ይልቅ ሞትን እመርጣለሁ እንዳላቸው የሃገራቸው ጋዜጣ አምባሳደሩን ጠቅሶ ማውጣቱ ይታወሳል፥፥

ከዚህ ቀደም የውጪ ሃይሎች ጫና የበረታበት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ወደ ቃሊቲ ለማዘዋወር እስክንድር ነጋ ታስሮበት የነበረበትን ክፍል ሲያድሱ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እስከዛሬ ሳይዘዋወር ቆይቷል፥፥በዚህ ሰሞን የአሜሪካ የአውሮፓ ሕብረት እና የእንግሊዝ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናት የጻፉትን ደብዳቤ እና የአልጀዚራን ዘገባ ተከትሎ ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እነ አንዱአለም አራጌ ያሉበት አከባቢ ሆኖ ለብቻው ከሁለት ሰዎች ጋር ቃሊቲ እስር ቤት ዋይት ሃውስ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ መዘዋወሩን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፥፥

አፈትላኪ

View original post