ሰበር ዜና! ኮማንደር ወልደሚካኤል ገ/እዝጊአብሄር እና ካሕሳይ ነጋሽ እርምጃ ተወሰደባቸው

Freedom4Ethiopian

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ-ሰገን በተባለው አካባቢ የሚገኙትን የኢህአዴግ የሰራዊት አባላት በግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰባቸው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ምክንያት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ተገለፀ።
ባለፈው ቀናት በሑመራ አካባቢ ማይ ሰገን በተባለው ቦታ ላይ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ ባደረሱት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን የገለጸው መረጃው በውጊያው ከተገደሉት ታጣቂ አመራሮችም።….
ኮማንደር ወልደሚካኤል ገብረእዝጊአብሄር የሃይል አዛዥ የነበረ፤ ካሕሳይ ነጋሽ በባዕኸር የሚልሻ አዛዥ የነበረ፤ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው የሻምበል ማእርግ ያለው በ24ኛ ክፍለጦር የሓይል አዛዥ የሆነውና ሌሎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ የስርዓቱ ታጣቂዎች- በአካባቢው ሰላማዊ ህዝብ የተለያዩ ግፍ ሲፈፅሙ የቆዩ በመሆናቸው የተነሳ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በላያቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን የተገኘው መረጃው አስረድቷል።

Sorce: TPDM.net

View original post

የሱዛን ሳቅ ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፍ ምን ያስቃል?

Freedom4Ethiopian

ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱዛን ራይስ ወደኬኒያ እና ኢትዮጵያ ስለሚደረገው ጉብኝት መግለጫና ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሸ ሰጥተው ነበር፡፡

የጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር በማስረዳት ንግግር የጀመሩት ራይስ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢህአዴ ሹማምንትና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች እንዲሁም ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስረድተዋል፡፡

ከጠያቂ ጋዜጠኞች መካከል ተራው የደረሰው አይዛክ አምባሳደር ራይስን ስለ ጉዞው የጸጽታና ደኅንነት ጉዳይ ከጠየቀ በኋላ ከዚህ በፊት ሌላኛዋ ጋዜጠኛ (ክሪስቲ) ያነሳችውን ሃሳብ በማጠናከር “ፕሬዚዳንት (ኦባማ) የኢትዮጵያና የኬኒያ መሪዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ አድርገው ይቆጥሯቸዋል?” በማለት ጠየቀ፡፡

ሱዛን ራይስ ማስረዳት ጀመሩ የጸጥታውና የደኅንነቱ ጉዳይ እምብዛም የሚያሳስብ እንዳልሆነ ዝርዝሩን በተመለከተ የምሥጢራዊ አገልግሎት ኃላፊው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ጠቆሙ፡፡ በአካባቢው ያለውን የአልሻባብን ሁኔታን አስረዱ፡፡ “ዴሞክራሲን በተመለከተ” አሉ ሱዛን ራይስ “የኬኒያው ፕሬዚዳንት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንደተመረጡ አስባለሁ፤ የምርጫውም ሂደት ፉክክር የበዛበት ነበር፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ በተደረገ ምርጫ በመቶ ድምጽ ያሸነፉ ይመስለኛል፤ ይህንን በተመለከተም እኛም ባወጣነው መግለጫ በምርጫው ውጤት ላይ ባይሆንም እንኳን ቢያንስ የምርጫውን አካሄድ በሚያግዙ አሠራሮች ላይ እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን…

View original post 85 more words

ፕሬዝዳንት እጩ ተወዳዳሪ ሴነተር ማርኮ ሩቢዮ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ሰብዓዊ መብትን ቀዳሚ አጀንዳቸው እንዲያደርጉ አሳሰቡ

Freedom4Ethiopian

ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ሴነተር ማርኮ ሩቢዮ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ጊዜ ሰብዓዊ መብት ቀዳሚ አጀንዳቸው እንዲያደርጉ አሳስበዋል:: ሴነተሩ ለፕሬዝዳንት ኦባማ በጻፉ ደብዳቤ “ምንም እንኳን አሜሪካና ኢትዮጵያ አሸባሪነት በመዋጋትና አካባቢዉ የተረጋጋ በማድረግ የጋራ ጥቅሞች ቢኖሯቸውም: አሜሪካ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን ስትጥስ እንዳላየች ማለፍ የለባትም” ብለዋል:: አስከትለውም “አማራጭ ሃሳቦችን የማንሸራሸሪያ ጎዳናዎችን በፖለቲካ ሂደቱ: በሲቭል ሶሳይቲውና: በሚዲያ ዙሪያ በመዝጋት የኢትዮጵያ መንግስት የበለጠ አለመረጋጋት በሃገር ውስጥ ሊያመጣ ይችላል” ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል::

ሴነተር ማርኮ ሩቢዮ ለፕሬዝዳንት ኦባማ የጻፉት ሙሉ ደብዳቤ እንደሚከተለው ይነበባል:-

July 22, 2015

President Barack Obama
The White House
1600 Pennsylvania Avenue NW
Washington, DC 20500

Dear Mr. President,

As you prepare for your upcoming visit to Ethiopia, I am writing to highlight my concerns regarding ongoing human rights abuses by the Ethiopian government against its own people. I am concerned that unless you make these issues a priority during your trip, your visit to Ethiopia could grant legitimacy to a government…

View original post 436 more words

ከፍተኛ ወታደራዊ የወያኔ ባለስልጣን መሰወራቸዉና ወደ አርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀላቸዉ

Freedom4Ethiopian

11144995_814272385352811_3462902730849957444_o

አንድ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ እንዲገለጽ ያልተፈለገ ከፍተኛ ወታደራዊ የወያኔ ባለስልጣን መሰወራቸዉና ወደ አርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀላቸዉ በወያኔ በኩል ከባድ እራስ ምታት ፈጥሯል። የእኚሁን ባለስልጣን ጉዳይ በተመለከተ አርበኞች ግንቦት 7 ምንም የሰጠዉ መግለጫ ባይኖርም በወያኔ በኩል ግን ያለዉ የደህንነት ክንፍ አጣርቻለዉ ብሎ መረጃዉን ማሳለፉን ለመረዳት ተችሏል።

በተያያዘ ዜና ከአርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትዕዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን ያበሳጨ ነዉ ተብሏል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የወያኔ ንብረት የሆነዉን በጎንደርና በተለይም አዘዞ ላይ የሚገኘዉን ሱር ኮንስትራክሽን የደመሰሰና ያቃጠለ ሲሆን በቅርበት የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ይታወሳል

አሰግድ ታመነ

View original post

ዜና ግርምት እናትና ልጅ በአንድ ሣምንት ውስጥ ከአንድ ሰው ሁለት ወንድ ልጆች ወለዱ

Freedom4Ethiopian

10407933_10153462647266411_6465457970895587765_n

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው ። ወ/ ሮ ሚልድሬድ ማሼጎ እና የአብራካቸው ክፋይ የሆነችው ፓትሪሲያ ስማቸው የአለማችን የድንቆች መዝገብ ውስጥ የሰፈረው።
በደቡብ አፍሪካ ካስቲል ነዋሪ የሆኑት የ38 አመቷ እናት ወ/ሮ ማሼንጎና የ19 አመቷ ወጣት ልጃቸው ፓትሪሲያ በአንድ ወር ውስጥ፣ በአንድ ሣምንት ውስጥ እንዲሁም ከተመሳሳይ ሰው በመውለድ ወ/ሮ ማሼንጎ ልጅና የልጅ ልጅ አገኙ ፣ ወጣት ፓትሪሲያ ልጅና ወንድም አገኘች እንዲሁም አቶ ቪንሴንት ማሉማን እናትና ልጅ በአንድ ሣምንት ውስጥ አስረግዘው ከዘጠኝ ወራት በኋላ የሁለት ወንዶች ልጆች አባት ሆኑ።

እናት እርጉዝ በነበሩበት ወቅት ልጃቸው ፓትሪሲያም እንደ እሳቸው ነፍሰጡር መሆኗን የተረዱ ቢሆንም ያረገዘችው ግን እሳቸውን ፅንስ ካሲያዛቸው አቶ ቪንሴንት ማሉማን መሆኑን በፍፁም አልገመቱም ነበር። ለዚህም ይመስላል የወ/ሮ ማሼንጎ ንዴትና ድንጋጤ ከፊታቸው ይነበብ የነበረው ።
ሌላው አስገራሚ የነበረው አቶ ቪንሴንት አስቀድሞ ያስረገዘው የወይዘሮዋን ልጅ መሆኑ ነዉ። አስቀድሞም ምጥ የመጣው የልጅ ፓትሪሲያ ነበር። ልጅ ፓትሪሲያ በአካባቢያቸው ወደሚገኘው የማዋለጃ ክሊኒክ በመሄድ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ በተገላገለች በአራተኛው ቀን ወላጅ እናቷም በዚያው ክሊኒክ ለእርሷና ለልጇ ታናሽ ወንድም አበርክተውላቸዋል።

አልሞ…

View original post 22 more words

አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ

Freedom4Ethiopian

**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ

** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም”

ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል::

የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አስረድተዋል::
በውይይቱ የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች አስር ፈጽሞ ያልተገባ መሆኑን ጠቅሰው: ሲፈቱም ሙሉ ነጻነት እንዳልተሰጣቸው ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰላቸው አስረድተዋል::ከዚሁም ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ኤርትራን ስለመምታት የተናገሩትን ዛቻ በተመለከተ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ኢትዮጵያ የኤርትራን ድንበር ጥሳ እንዳትገባና ብትገባ ግን አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸዋል::

ሌሎችም ሌሎችም ውይይቱ ይህን ይመስል ነበር ::

View original post

ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 29/2007 ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጠ

Freedom4Ethiopian

64002-imagesአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበር ቢሆንም ይገኙበታል ለሚባሉት ማረሚያ ቤቶች በተለይም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚላከው ማዘዣ ዘግይቶ በመላኩ እንዳልደረሰለት ገልጾ ለዛሬ ሀምሌ 15/2007 ለምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም አቶ አንዳርጋቸው ዛሬም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለምን እንዳላቀረበ የተጠየቀው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ማዘዣው እንደደረሰው ገልጾ ነገር ግን ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ መፃፍ ሲገባው ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተብሎ በመፃፉ አቶ አንዳርጋቸውን ማቅረብ እንዳልቻለ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ ተፅፎ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 29/2007 ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት 10 ግለሰቦች መካከል ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል የሚል ክስ የቀረበባቸውና…

View original post 25 more words

የቴፒው ትንቅንቅ አሁንም ቀጥሏል። የሳምንቱ አበይት ዜናዎችን በDCESON ሬዲዮ ያዳምጡ

Freedom4Ethiopian

aseac

የትጥቅ ትግሉ በአራቱም አቅጣጫ ተጠናክሮ ቀጥላል  የወያኔም ስጋቱ አይላል፤ ተባላ

አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ግንባሮች በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት ተከትሎ ከወያኔ ጎራ የተምታቱ ዜናዎች እየተደመጡ ነው።

የቴፒው ትንቅንቅ አሁንም ቀጥሏል።

ርዕዮት ዓለሙና የዞን 9 ጦማሪዎች በድንገት መፈታት እያነጋገረ ነው

የሚኒስትር-ሬድዋን ሁሴን-አማካሪ-መኮብለላቸው ተሰማ

እግዚአብሔር 10ቱን ለሙሴ የተሰጡትን ትእዛዝ እንዳሻሽላቸው አዞኛል “” የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ

አሰግድ ታመነ

View original post

ሰበር ዜና – የኦህዴዱ ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ አሊ ሲራጅ ስብሰባ ላይ ድንገት ታመው ወዲያው ሕይወታቸው አለፈ

OromiaTimes

ሰበር ዜና – የኦህዴዱ ከፍተኛ ባለስልጣን ስብሰባ ላይ ድንገት ታመው ወዲያው ሕይወታቸው አለፈ

unnameየኦህዴዱ ከፍተኛ ባለስልጣን ስብሰባ ላይ ድንገት ታመው ወዲያው ሕይወታቸው አለፈ

የሕወሓት አስተዳደርን በማገልገል የንግድ ሚኒስትር ደኤታ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት አቶ አሊ ሲራጅ ዛሬ በድንገት ማረፋቸው ተዘገበ:: እኚህ የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣን  በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ በነበሩበት ወቅት ድንገት በመታመማቸው ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ እንዳሉ በ46 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን መንግስታዊ ሚዲያዎች ዘግበዋል::

አቶ አሊ የንግድ ሚኒስትር ደኤታ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የኢፌዴሪ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ማገልገላቸውን የሚዘግቡት አፍቃሬ ሕወሓት ድረገጾች  በቅርቡ በተካሄው የውሸት ምርጫም ኢህአዴግን ወክለው በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድረው በማጭበርበር ማሸነፋቸው ይታወሳል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44955#sthash.elqbct0S.dpuf

View original post

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ተፈታች

ይመቻት ደስ የሚለኝ ሁሉም ቢፈቱ ነበርክ

Abraham's view

reyot


ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ተፈታች

(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ትናንት ጁላይ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የ እስር ጊዜዋን አጠናቃ ተፈታች። የመንግስት ሚድያዎች ጋዜጠኛዋ የአመክሮ ጊዜ ተሰጥቷት እንደተለቀቀች አድርገው ቢዘግቡም እውነታው ግን ርዕዮት የአመክሮ ጊዜዋን ጨርሳ የነበረው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር።

በሽብር ወንጀል ተከሳ 14 ዓመት ተፈርዶባት የነበረችው ይህችው ጋዜጠኛ በይግባኝ ቅጣቱ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላት የነበረ ሲሆን እነዚህን ዓመታት በእስር አሳልፋ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቅላለች።

በእስር በነበረችበት ወቅት በሚደርስባት የሰብአዊ መብት ጥሰት የርሃብ አድማ እስከማድረግ ደርሳ የነበረችው ርዕዮት እህቷ እስከዳር ዓለሙ ሳይቀር እንዳትጠይቃት ታግዳ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ባለቤቷ ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝቷል በሚል በፖሊስ ጉዳት የደረሰበት መሆኑም ይታወሳል። ር ዕዮት እስር ቤት እያለችም የዩኔስኮን የፕሬስ ነፃነት አዋርድ እንዲሁም በዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት – International Women’s Media Foundation – IWMF “በጋዜጠኝነት ለተሠራ ጀብዱ ሽልማት” የሚል አዋርዶችን አሸንፋለች።

View original post