ይቺ ነሃሴ በመጣች ቁጥር ባዶ እጇን አትሄድም:: አንዱን የኢህአዴግ ባለስልጣን ይዛ መሄድ ለምዳለች:: መለስ የጫረው በነሃሴ ወር ነው አሁን ደግሞ በረከት ሞቷል እየተባለ ነው መቼም ባለ ስልጣን ሲሞት ደስ ይላል:: ቢያንስ በሟች ስም ችግኝ መተከሉ ስለ ማይቀር ደስ ይላል አዳሜ መስከረም ላይ በበረከት ፋውንዴሽን ስም ዛፍ ለመትከል ተዘጋጂ::አንድ በአድd ሁላቸውም አልቀው ኢትዮጵያችን አረንጓዴ በአረንጓደ መሆኗ አይቀርም::

የዒድ ሶላትን በኢሕአዴግ አሥተባባሪነት በአዲስ አበባ ስታዲየም አልሰግድም! ኃፍረት የለሹ የኢሕአዴግ መንግሥት ባለፉት ጥቂት ቀናት ቅሌታም ካድሬዎቹን በማሰማራት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላትን ‹‹ለዒድ ሰላት ውጡ፣ ትራንስፖርት ተዘጋጅቶላችኋል›› የሚል የቤት ለቤት ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚሰገደው የዒድ ሶላት ላይ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሙስሊም ሲወጣ እንደኖረ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የዘንድሮው ዒድ በ‹‹ጥቁሩ ሽብር›› ማግሥት የሚካሄድ ከመሆኑ ባሻገር፣ ሌላ ኢሕአዴጋዊ የሁከት ዕቅድ የተነደፈለት እንደመሆኑ፣ ህዝበ ሙስሊሙ የግፈኞች የሁከት ድራማ ሰለባ መሆን ያለበት አይመስለኝም፡፡ የዘንድሮውን የዒድ ሰላት በአዲስ አበባ ስታዲየም መስገድ፣ ‹‹ጥቂት አክራሪዎች ሁከት ለመቀስቀስ ቢሞክሩም፣ የፀጥታ ኃይሎች ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት የዒድ ስግደት በሰላም ተከናውኗል›› ለሚል የኢቴቪ ማላገጫ ግብዓት መሆን ነው፡፡ አምና ከስግደት በመመለስ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ያን ለመሰል አሰቃቂ ጭፍጨፋ እየተዳረጉ በነበሩበት ቅጽበት፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹‹ህዝበ ሙስሊሙ ስግደቱን አከናውኖ በሰላም ወደየቤቱ ገብቷል›› ብሎ ማላገጡ አይረሳም፡፡ በግሌ የዒድ ሶላትን በኢሕአዴግ አሥተባባሪነት በአዲስ አበባ ስታዲየም አልሰግድም!

ኢድ ሙባረክ all world muslims

የዒድ ሶላትን አስመልክቶ አንዳንድ
ማስታወሻዎች
እሁድ ሐምሌ 20/2006
1. አሁን የደረሱን አንዳንድ
መረጃዎች በስታዲየም አካባቢ
በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው የፌደራል
ፖሊሶች እንደተበተኑ ያሳያሉ፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ በነገው ዕለት
ሊኖሩ የሚችሉ ትንኮሳዎች ካሉ
ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተለመደው
ታጋሽነቱ እንዲያሳልፋቸውና ሁከት
እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ
እንዲያደርግ እናስታውሳለን፡፡
2. በመደበኛነት ዒድ ከሚሰገድባቸው
ቦታዎች ውጪ በየአካባቢው በሚገኙ
መስጂዶች ዒድ ለመስገድ መሞከር
ከዚህ በፊት የነበሩ ልምዶች
እንደሚያሳዩት ለፖሊሶች ትንኮሳ
ያጋልጣል፡፡ በመሆኑም ሰላም
አደፍራሽ ከሆኑ ፖሊሶች ጋር
አላስፈላጊ ግጭትን ለማስቀረት
ሲባል በየሰፈሩ ባሉ መስጂዶች
ለመስገድ ከመሞከር መታቀብ
ያስፈልጋል፡፡
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል
ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
(በድምፃችን ይሰማ የሚወጡ
ጽሁፎች እና መግለጫዎች
መብዛታቸው ሳይሆን ተደራሽነታቸው
እና ተፅእኖ መፍጠር መቻላቸው ነው
ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው!
እርሶዎም መረጃዎችን በሚፈለገው
መልኩ መከታተል እና መልእክቱን
ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግ
ይጠበቅብዎታል!)

አቶ አላሙዲን የሚባሉት ትክክለኛ
ሙስሊም ናቸው? ??
የእስላምን ጥላት ብር አውጥተው
የሚያሳክሙት
ስንቱ ሙስሊም ኡማ በህመም
በችግር እየሞቀቁ እሱ ይህንን
አይሁድ የሚያሳክመው በተባረከው
ወር ደግሞ ለሙስሊሙ ኡማ ሰደቃ
ግዳጅ በሆነበት ሰአት
ልባቸው ላይ ፕላስቲክ ትቦ
የተገጠመላቸው አቶ በረከት ስምኦን
በጂዳ ሕክምና ላይ ናቸው።
#mabdllselam
አቶ በረከት ስምኦን በሳኡዲ አረቢያ
ጅዳ ከተማ እሁድ ሌሊት ጀምሮ
ከቤተሰቡ ጋር ቡግሻን ሆስፒታል 4
ፎቅ በህከምና ላይ ይገኛል። አቶ
በረከት አርቴፊሻል የፕልስቲክ ቧንቧ
ከልባቸው ጋር በድጋፍ ተገጥሞ
እንደሚኖሩ ይታወቃል።
ክዚህ ቀደም ደቡብ አፍሪካ ለህክምና
ሄደው የነበሩት አቶ በረከት መቸም
ሰው ይሙት አይባልም ባህላችንም
አይደለም ። እግዜር ይማርህ ነው ;
ከፖለቲካ ወጣ ስንል ለክፉ መልካም
አይመለስም ..እኒ ግን እንደ ፖለቲከኛ
ሆኜ ነው የማስበው ግን ቀኝህን
ሲመታህ ግራህን አታስደግመው
በተቻለህ መጠን በፍጥነት መልሰህ
አጩኸው ነው። በወያኔ ወገኖቻችን
የሚሰቃዩትን ስቃይ አሰቃዮች
በተፈጥሮ ሕመም ሲያገኙት የወገንን
ስቃይ ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ
እና መረዳት አለባቸው፡፤
ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን
እናቀርባለን ይጠብቁን።

… መስጊዳችሁን አይሁዶች
ስላፈረሱባችሁ ከቤተክርስትያናችን
ገብታችሁ ሰላታችሁን ስገዱ(ጸልዩ)…”
አባ መናዊል ሙሰለም-በተወረረችዋ
ፍልስጤም የላቲን አሜሪካ
ቤተክርስትያን የበላይ ጠባቂ
ይሉናል አባ መናዊል “…እነዚህ
ጽዮናውያን አላማቸው ሙስሊሙን
ከፍልስጥኤም ማስወገድ ብቻ
አይደለም::ከዚያ በማስከተል እኛ
ክርስትያኖችንም የማጥፋት እቅድ
ነው ያነገቡት::አዶልፍ ሂትለር
ከአይሁድ ቀጥሎ ሌላውን የምስራቅ
አውሮፓ ጂፕሲዎችና ሶሻሊስታዊ
አመለካከት ያላቸውን ሶቭየታውያን
የማጥፋት ፕላን እንደነበረው
ጽዮናውያንም ከሙስሊሙ ቀጥሎ
ክርስቲያኑን የማስወገድ (Mass
cleansing) ፍላጎት አላቸው::
አይሁዶች በ2002 የቤተልሄምን
ቤተክርስቲያን በቦንብ ደብድበው
፥ቀሳውስትና ተማሪ ዎች ገድለው
ተያይዞ የነበረውን ትምህርት ቤት
ካፈረሱ በኋላ ከቦታው ለመጎብኘት
ተገኝቼ ነበር::ከቦንቡ ድብደባ ከዳኑት
ታዳጊ ህጻናት ተማሪ መካከል አንዱ
“አባ መናዊል” ብሎ ጠራኝ “አቤት”
አልኩት:: “ለምን ይዋሻሉ?”
አለኝ::ደንገጥ ብዬ “ምን ዋሸሁ?”
አልኩት:: “ከዚህ በፊት አይሁዶች
ቤተክርስቲያን አይደፍሩም
አላሉንም?ህጻናት አይገድሉም
አላሉንም?ከዚህ በላይ ምን ሊደርጉ
ፈልገዋል?” አለኝ::ለዚያ ታዳጊ
የምመልሰው መልስ
አልነበረኝም::ሆኖም እነዚህ
ጽዮናውያን ሌላውን ሁሉ አስወግደው
ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩባትን
ጽዮናዊት ሀገር የመገንባት ድብቅ
ሰይጣናዊ ህልም እንዳላቸው ከልቤ
ተረዳሁ::ጉዳዩ ከሙስሊሞች ጋር ብቻ
አድርጎ የሚያስበው አለም
የተስፋፊነት ህልማቸውን ለመግታት
መረባረብ ይገባዋል::…”
ጽዮናዊቷ እስራኤልበ2006
ሊባኖስን ከመውረሯ በፊት
ያቀረበችው ምክንያት “ወታደሮቼ
ተጠለፉብኝ” የሚል ነበር::ዘንድሮ
ጁላይ 8 ጋዛን ለመውረሯ ምክንያት
ያደረገችውም “ሶስት ሰፋሪ ዜጎቼ
ተጠልፈው ተገድለውብኛል” የሚል
ነበር::
በመሰረቱ የሰው መሬት ነጥቀው
ሰፍረው የነበሩትን ሶስቱ ጽዮናውያን
ጠለፍኩ ያለ የትኛውም የፍልስጤን
ተቃዋሚ ሽምቅ ተዋጊ የለም::በሺህ
የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊ
ለመግደል፣የተቃዋሚዎችን ሀይል
ለማዳከም፣ማንቁርቱ ላይ
በቆመችበት ኢኮኖሚያቸው ላይ
የኋልዮሽ ለመመለስ እስከረዳት
እስራኤል ዚጎቿን አትገድልም
አይባልም::እነዚህ ሶስት ጽዮናውያን
በእስራኤል በራሷ ለመገደላቸው
በርካታ የሚመስሉ ማስረጃዎች አሉ::
ቁም ነገሩ ያ አይደለም::ዛሬ
(ቅዳሜ) በነበረው የአስራ ሁለት
ሰአት የተኩስ አቁም ስምምነት
እንደተጣራው እስራኤል ከሶስት
ሳምንት ባነሰ ጊዜ 1040
ፍልስጤናዊ ገድላለች::ከ5700 በላይ
አቁስላለች::ከአምስት ነጥብ አምስት
ቢሊዮን ዶላር በላይ ውድመት
አስከትላለች::በተባበሩት መንግስታት
ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ስር
በጋዛው ወረራ የእሥራኤልን የጦር
ወንጀለኝነት የሚያጣራ ኮሚቴ
እንዲቋቋም የቀረበውን ሀሳብ
አሜሪካ ስትቃወመው፥17 የአውሮፓ
ሀገሮች ድምጽ ከመስጠት
ተቆጥበዋል::
ከውሻ የረከሰው የፍልስጤናውያን
ህይወት በጽዮናዊቷና ወራሪዋ
እስራኤል ሲቀጠፍ ነገሩን
ከሀይማኖት አያይዘው “እሰይ
አበጀሽ” የሚሉ የመኖራቸውን
ያህል፥ከሟቾቹ ውስጥ ክርስትያኖች
መኖራቸውን ልብ ያሉ በሰብአዊነት
ልባቸው መነካቱ አልቀረም::
ፍልስጤናውያን ከግማሽ ምእተ
አመት በፊት የራሳቸው በነበረችው
ሀገር ላይ በጉልበት እንድትሰፍር
የረዷት ምእራባውያን ድንበር
ተሻግራ ጋዛን በጦር አውሮፕላን
ስትደበድብ “ራስ መከላከል” እያሉላት
ነው!ወደፍልስጤናውያን ዞር
ብለውም “ራሳችሁን ተቆጣጠሩ”
የሚል ምክር አዘል ማስፈራርያ
ያቀብላሉ!ፍልስጤናውያን ለወረራው
አጸፋ መስጠት ከሞከሩ በአሸባሪነት
ይሞግቷቸዋል::
“ከሁለት ሺ አመት በላይ በምድር ላይ
ተንከራተናል” የሚሉት አይሁዳውያን
እስራኤል የምትሰኝ ሀገር
ከተመሰረተች ስድሳ አራት አመት
ውስጥ የሰሩት ግፍ ከአሁን ወዲያ
አምላክ ቢበትናቸው ለስንት ዘመን
እንደሚያንከራትታቸው ለመገመት
የሚያዳግት ነው!!
http:// electronicintifa
da.net/content/ israeli-
distorti ons-during-sieg e-
church-nativi ty/3984

ሰበር ዜና ህዝባዊ አመጽ ! መሬ አመረረ!!

Freedom4Ethiopian

ላለፉት ሀያ ሶስት አመታት የኢትዮዽያን አንጡራ ሀብት ወደ ትግራይ ሲያግዝ የኖረዉ ወመኔዉ የዘራፊ ቡድን እንደልማዱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መራብቴ ወረዳ አለም ከተማ በጠራራ ጸሀይ ያደረገዉ የዝርፊያ ሙከራ ከህዝቡ የለመደዉን ይሁንታ ሳይሆን የተኩስ ሩምታ የጠበቀዉ ሲሆን እስካሁን ከወንበዴዉ ቡድን ሰባት ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን ከህዝብ ወገን አንድ የተሰዋ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።ዝርዝሩን በመረጃ አስደግፈን እንመለስበታለን ይከታተሉ።
በሰሜን ሸዋ የመርሃቤቴ ወረዳ ህዝብ ከወያኔ የፀጥታ ሃይሎችና ፌደራል ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄደ ነው፣
ለወረዳው አለም ከተማና አካባቢዋ አገልግሎት ይውላል ተብሎ ከብዙ ጊዜ በሁአላ የገባውን መብራት የወያኔ መንግስት ህዝቡ የሚገለገልበትን መብራት አቁሞ ትራንስፎርሜሽኖቹን ነቅሎ ለአስቸኩአይ ጉዳይ ይፈለጋል ብሎ ወደ ትግራይ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የወረዳው 27ቱም ቀበሌ ተጠራርቶ ትራንፈርመሩን በቁጥጥር ስር በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊኣ እያደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ ታጣቂ በኩል 1 ሞቷል።
ባሁኑ ሰዓት ወረዳውን መሉ በሙሉ የህዝቡ ታጣቂ ተቆጣጥሮት ይገኛል። ወያኔ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢወች ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው እያንቀሳቀሰ መሆኑ…

View original post 16 more words

ጅምላ ጨራሽ ተውሳክ (Biological Weapons) በድብቅ ወደ ትግራይ ተወሰደ

Freedom4Ethiopian

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በመሰረቱ ጅምላ ጨራሽ ተውሳክ ወይም ባዮሎጂካል መርዝ በሰው ልጅ ላይ መጠቀም በተባበሩት መንግስታት የተከለከለ ነው። ሆኖም ይህንን የሰውን ልጅ በጅምላ የሚጨርስ ተውሳክ በህወሃት ጄነራሎች የሚመራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር በድብቅ ወደ አገር ውስጥ አስገብቶ ነበር። “ለምን እና በማን ላይ ግድያውን ለመፈጸም ነው?” የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ፤ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ክፍልም ቢሆን እንደዚህ አይነት ጥቆማ ቢደርሰው እርምጃ ለመውሰድ ይችላልና ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶችን ይህንን ጉዳይ ልብ ሊሉት ይገባል። እናም ዛሬ የደረሰን ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ፤የዛሬ ዓመት በድብቅ ተጭነው ወደ አገር ቤት ውስጥ የገቡትን አንትራክስ ስፓርስ (anthrax spores )፥ ብሩሲሎሲስ (brucellosis)፣ እና ቦቱሊስም (botulism) የሚባሉ ጅምላ ጨራሽ ባዮሎጂካል መርዞች ታሽገው ከተቀመጡበት ደብረዘይት መከላከያ ኮሌጅ ላቦራቶሪ ውስጥ ወደ መቀሌ ዛሬ ሌሊት በኮንቴነር ተጭነው እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።

ጥቆማውን ያቀረበው እና አባ ኮስትር በሚል ስም መጠራት የመረጠው ግለሰብ ከሙያውም አንጻር ይህንን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ለግንዛቤ እንዲሆን ከዚህ በታች ያለውን የግንዛቤ ጽሁፍ አዘጋጅቶ አቅርቧል።

ሥነህይወታዊ በሽታ አምጭ(Biological Ethiologic Agents ) ተዉሳክን እንደ ጦር መሳርያ (Biological Weapons )የሰዉ ልጅ መጠቀም…

View original post 281 more words

ደስ የሚል ሠበር ዜና ከጋዛ ጀግናው ኢዘዲን ቀሳም ጦር ዛሬ ፈጅር ላይ ከገደላቸው 32 የእስራኤል ወታደሮች ሌላ ሾኦል አሮን የተባለ አንድ የእስራኤል ወታደር መማረኩን ገልፆዋል ጋዛም ሀዘኖዋን ረስታ ደስታ ላይ ናት 1 የእስራኤል ወታደር መማመረክ በቀጣዩ ቀን የጦርነቱንና የድርድሩን አቅጣጫ ይቀይረዋል ተብሎ ይጠበቃል ጋዛ ውስጥ ያሉ መስጊዶች በሙሉ የደስታ ተክቢራ እያሰሙ ይገኛሉ

የጨነቀው የወመኔው መንግስት በእለተ ጁምአ የወሰደውን የሃይል እርምጃ ተከትሎ የሙስሊሞችን ጥያቄ የሚፈታ ግብረ ሃይል በተለጣፊው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ ቤት አማካኝነት መቋቋሙን የወመኔው መንግስት ንብረት ፋና ራዲዮ ጣቢያ ነገረን፡። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጠየቁት፡ጥያቄ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ እንጂ ጥናት የሚያስፈልገው እና ግብረ ሃይል የሚያቋቁም ነገር የለውም፡፤ የወመኔው መንግስት የተቆጣጠረውን የአምልኮ ቦታችንን መልስልን የህይማኖት መሪዎቻችንን መምረጥ የኛ ሃላፊነት እንጂ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት አንሻም፤ ንብረቶቻችንን እኛው እናስተዳድር መጤ ሃይማኖት አይጫንብንም ፣ የታሰሩ ኮሚቴዎቻችን/ ወኪሎቻችን ይፈቱ የሚል ነው። ይህ ቀላል እና ግብረ ሃይል አሊያም አጣሪ ቡድን የሚያስፍልገው ጉዳይ አይደለም ሕገመንግስታዊ መሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ ነው፡፤ ጥያቄው ግልጽ መልሱም በህግ የተቀመጠ ግልጽ ነው። የወመኔው መንግስት ለራሱ በሚያምቸው መንገድ ለመሄድ እና የመብት ስላማዊ ትግሉ ስላስጨነቀው የሚያስወግድበትን መንገድ ለማስላት አዲስ የተጠቀመበት የማዘናጊያ ዘዴ ግብረ ሃይል ያዉም ጥያቄዎችን የሚፈታ … እስከዛሬ የት ነበር ? አሁንስ ለምን ታስበ ? በርጋታ እና በሰላማዊ መልኩ ተከታታይ የሆነ ጥያቄ በወመኔው መንግስት ላይ ያጭራል። ወመኔው መንግስት ጨንቆታል ። ሲጨንቀው ግብረሃይል እንደ ማስወገጃ እና ማዘናጊያ መፍጠር ከባለፈው የታየ ጉዳይ ነው። የወመኔው መንግስት ድርቅና እና ፈጣጥነት የተለመደ ማጭበርበሪያ ነው

እገታውና አፈሳው አሁንም ቀጥሏል!
ህገ ወጥ እርምጃ እልኽና ቁጭትን
እንጂ መፍትሄን
አይወልድም!
አርብ ሐምሌ 11/2006
የመንግስት ወታደሮች ሰላማዊው
ህዝበ ሙስሊም ላይ
ጭካኔ የታከለበት ጥቃት ከፈፀሙ
በኋላ በአንዋር መስጊድ
ቅጥር ግቢ ውስጥ ያገቱትን ሰው
ወደተለያዩ ማጎሪያ
ካምፖች ማጋዛቸውን በምሽቱም
ቀጥለዋል፡፡ እስካሁን
አፍነው የወሰዷቸውን ሙስሊሞች
በጨው በረንዳ፣
በጅንአድ፣ በአራተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣
በኮልፌ 18 ማዞሪያ
እና በሌሎችም ቦታዎች ወስደው
እያንገላቱ ይገኛሉ፡፡
በማጎሪያ ካምፕ ያሉትንም አንድ ዳቦ
እና ውሃ ብቻ
በመስጠት ስፖርት በማሰራትና
በመደብደብ ላይ
እንደሚገኙ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮች ጾማቸውን እንኳ
እንዲያፈጥሩ እድል
ያልሰጧቸውን ሙስሊሞች በመኪና
ጭነው ሲያልፉ አላፊ
አግዳሚው ሰው ማፍጠሪያ ተምር
እና ብስኩት
ሲወረውርላቸው መመልከት
በእጅግም የመንግስትን ጭካኔ
እና የህዝቡን ተምሳሌታዊ አብሮነት
አቃርኖ ለማነጻጸር
የሚያስችል አስገራሚ ክስተት ነው፡፡
የመንግስትን ኢ-
ሰብአዊነት በራሱ ሰብዓዊነት እያበሰ
ያለው ህዝበ
ሙስሊም በእርግጥም ታላቅ ክብር
ይገባዋል!
እስካሁን የህዝቡን ስቃይ ከምንም
ያልቆጠሩት ፖሊሶች
በመስጂዱ የተያዙትን ሴቶች
‹‹እናስፈታለን›› እያሉ
ከቤተሰቦች 2 ሺህ ብር እና ከዚያም
በላይ ጉቦ በመጠየቅ
ላይ መሆናቸው በእርግጥም
መንግስታዊ ስርአቱ
የደረሰበትን የዝቅጠት ደረጃ
የሚያመለክት ነው፡፡
አንዳችም ወንጀል ያልሰራን ህዝብ
ከበው፣ ደብድበውና
አስረው ‹‹እንድንፈታ ገንዘብ ስጡን››
ማለታቸው
‹‹እንጥፍጣፊ የሚሞላ ኢትዮጵያዊ
ርህራሄ የላቸውምን?››
ያስብላል፡፡
በዚህ ሁሉ በደል መሃል ደግሞ ኢቲቪ
በዜናው ‹‹በዒድ
ሰላት ላይ የተነሳ ሁከት በቁጥጥር ስር
አውያለሁ›› የሚል
ዜና ማሰማቱ ሺዎችን አስገርሟል፤
አሳዝኗልም፡፡ ያለፈውን
ዓመት የፕሮፓጋንዳ ዜና እየደገሙ
እያነበቡ የሚመስሉት
የኢቲቪ ሐሰተኛ ጋዜጠኞች ህዝበ
ሙስሊሙን ከነጭራሹ
የማያውቁት ይመስላሉ፡፡ ረመዳን
ባለተጠናቀቀበት ወቅት
‹‹በዒድ ሰላት ላይ ረብሻ ያስነሱ
ሰዎችን በህዝበ
ሙስሊሙ ድጋፍ በቁጥጥር ስር
አውያለሁ›› ማለታቸው
በደበደቡት ህዝበ ሙስሊም ላይ
ንቀት የተሞላበት ሹፈት
መሆኑ ሳያንስ የቅጥፈት በሬ ወለደ
ዜናዎቻቸውን በምን
መልኩ እየሰሩ እነደሆነም
የሚያሳብቅ ክስተት ነው፡፡
በተዛዋሪ ‹‹እንደበድብህ ዘንድ
ስላገዝከን እናመሰግናለን››
እያሉ ላሾፉበትም በፍትህ ፊት
የሚቀርቡበት ጊዜ ሩቅ
አይደለም!
አንድ ነገር ግልጽ ነው! ሰላማዊ ዜጎች
ሕገ መንግስታዊ
መብታቸው ይከበር ዘንድ በሰላማዊ
መንገድ የሚያሰሙትን
ድምፅ ኹከትና ብጥብጥ በመፍጠር
በኃይል ለማኮላሸት
የሚደረገው ህገ ወጥ እርምጃ እልኽና
ቁጭትን እንጂ
መፍትሄን እንደማይወልድ
በተደጋጋሚ የተስተዋለ ጉዳይ
ነው፡፡ ሰላማዊ ዜጎች ለሚያነሱት
አግባብ ያለው ሮሮ
ምላሽ ለመስጠት ብቸኛና አዋጭ
የመግባቢያ ቋንቋ
ዜጎችን ቀርቦ በመግባባት መንፈስ
ውይይት ማድረግ
እንጂ ብረት እና ዱላ ሊሆን
አይችልም፡፡
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላነሱት
ሃይማኖታዊ የመብት
ጥያቄ እየተሰጣቸው ያለው ምላሽ
ማን አለብኝነትና አጉል
ጀብደኝነት የተጠናወተው ቢሆንም
ይህንኑ ተቋቁመው
ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌትነት
የተጎናፀፈውንና ፍፁም
ሰላማዊ መርህ የተከተለ
ተቃውሟቸውን መቀጠልን ብቸኛ
አማራጫቸው አድርገው እነሆ
ዛሬም በተቃውሞ አደባባይ
ላይ ይገኛሉ! ታሪክ የተበዳዩን ህዝብ
ትግል፣ የበዳዩንም
በደል ይመዘግባል! ሩቅ ያልሆነው
ድልም ይመጣል!
አላህም ከበደለኞች ስራ ዘንጊ
አይደለም!
መላ የአገራችን ህዝቦችና የመገናኛ
ብዙሃን ሆይ!
እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሦስት
ዓመት ሊሞላው
የተቃረበውን ሰላማዊ ትግላችንን
በቅርብ ሆናችሁ
በመከታተል ስታደርጉት ለቆያችሁት
ሁለንተናዊ ድጋፍ የላቀ
ምስጋናችን ይድረሳችሁ እያልን
መንግስት ዛሬም ካለፈው
ስህተቱ ሳይማር በንፁሃን ወገኖቻችሁ
ላይ የሚወስደውን
ኃላፊነት የጎደለው እርምጃ በፅኑ
እንድታወግዙና የመገናኛ
ሚዲያዎችም የህዝቡን ድምጽ
ታሰሙ ዘንድ ጥሪያችንን
እናስተላልፋለን!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል
ደጃፎች ድረስ
ይቀጥላል!
ድምጻችንይሰማ!
አላሁ አክበር!