Monthly Archives: December 2014

ሜሮን ጌትነት – ሀገሬ ልክ ነበርክ አንተ እዚህ ለፍተህ ስትኖር ባገርህ አፈር ላይ ‘አባን ከና’ የሚል ያንተን ልፋት የሚያይ አንዳችም ሰው የለም ህዝቡ ውጭ አምልኳል ልቡ ተንበርክኳል ላገር ስታነባ በጥቅም ይለካል በነጻ ያላበህ በዶራል ይተካል አሁን በቀደም ለት ለቤታችን ምርጊት … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ንብረት የሆነ ተዋጊ ሔሊኮፕተር ባለፈው ዓርብ ተጠልፎ ኤርትራ ግዛት አሰብ ማረፉ ተረጋገጠ፡፡ የዘወትር የበረራ ልምምድ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሩሲያ ሠራሽ ኤምአይ 35 ተዋጊ ሔሊኮፕተር ይዞ ወደ ኤርትራ የኮበለለው ዋና አብራሪ ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ ይህንን ዓይነት … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

10 ቢሊዮን ብር በከንቱ ለባከነበት “የነፋስ ተርባይኖች” ቅሌት፣ ተጠያቂው ማን ነው?

Originally posted on Freedom4Ethiopian:
“ለነፋስ ተርባይኖች” ግዢ በሚል ሰበብ በየአመቱ እንደዘበት የሚባክነው የቢሊዮን ብሮች ሃብት ሲታይ፣ በእርግጥም በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የማይገኝለት ቅሌት ነው ማለት ይቻላል። በየትኛውም አገር ቢሆን፣ በበለፀጉት አገራትም ጭምር፣ ከፍተኛ ሃብት በከንቱ እንዲባክን ማድረግ አሳፋሪ ተግባር ነው።…

Posted in Uncategorized | Leave a comment

ጎጃም ሃገሬ ሆይ እውነት ሱሪህ ወልቋልን? ተነስ አንተ የተኛህ ያንቀላፋህ ሱሪህን የፈታህ ጎጄ፥ ወንድነትህን ሳታጣ ማንነትህን አሳይ፥ ተነስ ተነስ ተነስ!!!!!!!!! በ አደኩበት ጎጃም ሰው ተከባብሮ ይኖር ነበር፥፥ ማንም ባለስልጣን ነኝ ብሎ ደፍሮ አንድን ግለሰብ ያለግባብ አይበድልም፥ አይገድልም ነበር፥፥ ከገደለ፥ የሟች ወገን የወንድሙ ልጅ ደም ፈሶ ዝም ብሎ አይተኛሞ ነበር፥፥ ህዝባችን በመከባባር ላይ የተመረኮዘ መፈራራት ነበረው፥፥ ዛሬ ላይ ግን ልጅህን አንድ ፓሊስ በርህ ላይ ደፍቶብህ ሲሄድ አባት ወይም ወንድም እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥበት ሁኔታ ነው ያለው፥፥ ይህ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው፥፥ ፍትህ በሌለበት አገር፥ መንግስት አልባ በሆነ አገር በጉልበት ባሪያ አደርግሃለው ብሎ ለተነሳ ወንበዴ ጉያህ ያለውን ሲወስድብህ ዝም ብሎ መተኛት የ ጎጃም ባህል አልነበረም፥፥ የወገኔ ሱሪን ያስፈታው ምን እንደሆነ አላውቅም፥፥ ማንነትህን ፥ እምነትህን እንድታጣ ለወያኔ እጅ እና ጓንት ሆኖ የሚገልህን ሆዳም ባልጊዜ ነኝ ባይ ሲዝናናብህ፥ ሲገድልህ፥ ሲገርፍህ ተኝተህ መገረፍህ እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው፥፥ አገሬ እንዲዚህ አለነበረም፥፥ ትምክተኛው ወያኔ መተማመኛው መግደያ መሳሪያው ነው፥፥ የ ወንዜን ልጅ ምን ነካው? አንድ ነገር መሰመር ያለብት ነገር በግሌ በመገዳደል የሚመጣ ሰላም የለም፥፥ ነገር ግን አንድ ወገን ዘላለም ተጠቂ ሆኖ ሲቀጥል አምላክ ያውቃል ብሎ አንገትን መድፋት ግን ከሽንፈትም በላይ ውርደትና ማንነትን የማጣት እጣፋንታ ነው፥፥ አሁን በወገኔ ላይ እየደረሰ ያለው ይህ ነው፥፥ ወያኔ ገና ሲገቡ ያደርጉት ነገር ቢኖር የ አገሬውን ህዝብ ጠመንጃ ማስፈታት ነው፥፥ አሁን መለየት አለበት፥፥ ባለጌ ባልጊዜ ነኝ ብሎ ወንድምህን፥ አባትህን ፥ እናትህን ከጉያህ እየነጠቀ የሚገርፍብህን፥ የሚግድልብህን ባለጌ ባለስልጣን ዝም ብለህ እያየህ ከተኛህ ማሪያምን የ ዚያ የጀግናው የበላይ ዘለቀ አድባር ትጣልቶሃል ማለት ነው፥፥ ወንድነትህን ሽጠሃል ማለት ነው፥፥ ወገኔ፥ አንገቱን የደፋ እንደተደፋ ይቀራል፥፥ አንገትህን ያሰደፍህን ባለጊዜ ጠብቀህ ምላሹን ይሰጠኸው ጊዜ ወንደነትህ ይታደሳል፥፥ ተነስ አንተ የተኛህ ያንቀላፋህ ሱሪህን የፈታህ ጎጄ፥ ወንድነትህን ሳታጣ ማንነትህን አሳይ፥ ተነስ ተነስ ተነስ

Posted in Uncategorized | Leave a comment

ሕወሐት ደ/ፂዮንን ጠ/ሚ/ር ለማድረግ አቅዷል

Originally posted on Freedom4Ethiopian:
ሕወሐት ደ/ፂዮንን ጠ/ሚ/ር ለማድረግ አቅዷል * የአዜብና የደህንነቱ ሹም ያልታሳካ እቅድ (ከኢየሩሳሌም አርአያ) የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል…

Posted in Uncategorized | Leave a comment