ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢዶሎ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የ12 ሰዎችን ህይዎት ቀጠፈ

Freedom4Ethiopian

ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ደንቢዶሎ 68 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 12 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ቀሪዎቹ 56 ተሳፋሪዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች አምቦ እና አዲስ አበባ በሚገኙ ሆስፒታሎች ለህክምና እንደተላኩም ፖሊስ አስታወቋል። አውቶቡሱ 194 ኪሎ ሜትር እንደተጓዘ ረፋድ 4 ሰአት ላይ ምዕራብ ሸዋ ጨሊያ ወረዳ ራቾ ገጠር ቀበሌ ልዩ ስሙ መሳለሚያ አካባቢ ሲደርስ ነበር አደጋው የደረሰው። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ከበደ ደቢርሳ ተናግረዋል።

posted by Aseged Tamene10420270_936584116374429_3710191187454730855_n

View original post

#ውድ_ኮሚቴዎቻችንን በነጻ ማሰናበት ህዝብ በሙሉ ልብ ሊቀበለው የሚችለው ብቸኛ መንገድ ነው!!! በህግ ፊት ተበዳይ የሆነው ህዝበ ሙስሊም ከህግ በላይ በሆኑ አመራሮች የሚሰጠውን ገምድል ፍርድ ፈጽሞ እንደማይቀበለው ሲያሳውቅ ቆይቷል፡፡ አሁንም በወኪሎቹ ላይ የሚሰጠውን ‹‹ድርጅታዊ›› ውሳኔ ውድቅነት ደጋግሞ ያሰምርበታል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ህጋዊነት የጎደለውም ይሁን ፖለቲካዊ ብስለት ያልታከለበት መንግስታዊ አካሄድ ክህገ ወጥነት ያልዘለለ፣ ብሎም ከህዝብ ጋር መቃቃርን የሚያተርፍ እንጂ ሃገራዊ ፋይዳ እንደማይኖረው ታስቦበት አሁንም መረጃ እና ማስረጃን ብቻ የተደገፈ ፍትሃዊ ፍርድ በመስጠት ኮሚቴዎቻችንን በነጻ ማሰናበት ህዝብ በሙሉ ልብ ሊቀበለው የሚችለው ብቸኛ መንገድ መሆኑን በአጽንኦት እንገልጻለን! ሕዝበ ሙስሊሙ በጀግኖች መሪዎቹ ላይ የሚሰጥን የሐሰት ፖለቲካዊ ብይን በጭራሽ አይቀበልም! በጽኑም ይታገለዋል!!!