በቨርጂኒያ በደረሰ አሳዛኝ የመኪና አደጋ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ሲሞቱ አንዱ በጠና ቆስሏል

Freedom4Ethiopian

ትላንት ማክሰኞ ማታ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ክፍለ-ግዛት ዋሽንግተን በተባለ አውራጃ ውስጥ 81 ተብሎ በሚጠራው አገር አቋራጭ መንገድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ሲሞቱ አራተኛው በሄሊኮፕተር ወደ ሆስፒታል ተስዶ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጾል::
የሞቱት ሶስቱ ወጣቶችም የሚከተሉት ናቸው:-
1ኛ) አቤናዛር ቴዎድሮስ የ19 አመት (ሹፌር)
2ኛ) አቤል አየለ የ19 አመት (አብሮ ተጓዥ)
3ኛ) አለሙ አምሃ የ25 አመት (አብሮ ተጓዝ)
በጠና ቆስሎ ሆስፒታል የሚገኘው አርከጻዲቅ ይልማ የተባለ የ19 አመት ወጣት ነው::
ፓሊስ እንዳለው አደጋው የተፈጠረው አቤናዛር ሲያሽከረክረው የነበረው ቶዮታ የቤት መኪና የመንገዱ ዳር ላይ ጎማ ተንፍሶበት የቆመ ትልቅ የጭነት መኪና ሲገጭ ነው:: በግጭቱ ወቅት የጭነት መኪናው ባለቤትና ተሳፋሪዎች ከመኪናው ውጭ ስለነበሩ በማናቸው ላይ አደጋ አልደረሰም::
አደጋው አሁንም በፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ቢሆንም ከአልኮል መጠጥ ጋር የተያያዘ እንደማይመስል ተጠቅሷል::
ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን ይመኛል::

posted by Aseged Tamene

View original post

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a comment