“ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ

Freedom4Ethiopian

በቅርቡ በግብጽ ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸንፋሉ እየተባለ የሚጠበቁት ዕጩ ተወዳዳሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” ሲሉ ገለጹ፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ በውጭ የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን ምሁራን የግድቡ መሠራት ግብጽን “በማይቀር አደጋ” ላይ እንደማይጥላት አስረዱ፡፡

በግብጽ በተላለፈ የቴቪ ስርጭት ትላንት ቃለመጠይቅ የሰጡት የቀድሞው የግብጽ ጦር መሪ ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ ግድቡን አስመልክቶ ሰፊ ትንተና እንዳልሰጡ አልሃራም የቲቪ ስርጭቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሆኖም ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ ማለት ለእኛ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡

አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊደረግ የሚገባው ንግግር ትኩረት ሳይሰጠው ለረጅም ጊዜ የቆየ መሆኑና ውይይቱም የተጀመረው ዘግይቶ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን ተገቢውን ጥረትsisi አለማድረጋችንን ማመን አለብን፤ በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ለመተባበርና መፍትሔ ለማግኘት ድርድርና የጋራ መግባባት ቁልፍ ናቸው” በማለት አል-ሲሲ የግብጽን ፍላጎት አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ የአባይ ግድብ ዙሪያ…

View original post 288 more words

በቅርቡ የታሰሩት ጋዜጠኞች እና ዞን 9 ብሎገሮች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

Freedom4Ethiopian

ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ከጠዋቱ 4፡00ሰዓት የነበረው ቀጠሮ ባልታወቀ ምክንያት ወደ 8፡00 ሰዓት ተዛውሮ ነበር፡፡ በ8፡00 ሰዓት በነ በረው ቀጠሮም አጥናፍ ብርሃን፣ ኤዶም ካሳዬ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያው ዙር ወደ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ በ9፡00 ሰዓት ደግሞ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ዘለዓለም ክብረት ቀርበዋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ ፖሊስ) ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመጠየቁ ለቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ጉዳዩ በዝግ ችሎት ነው በሚል ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ ጓደኛ እንዲሁም በስፍራው የነበሩ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ፣የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች፣ ዲፕሎማቶች ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ችሎቱን መታደምም ሆነ መግባት በመከልከሉ ጉዳዩ በዝግ ችሎት ተከናውኗል፡፡
ቀሪዎቹ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህት ፋንታሁን ነገ ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ የዛሬ ፍርድ ቤት ሌላ ለየት ያለው ክስተት የህግ ባለሙያ የሆነው ወጣት ኪያ ፀጋዬ ችሎቱን ለመታደም አራዳ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ ፎቶ…

View original post 35 more words