በድንገት ሙሉ በሙሉ የፈረሰውን ታሪካዊው የጡሪሲና መስጊድን በወፍ በረር ላስቃኛችሁ ነው ተከተሉኝማ

ከከሚሴ ከተማ ወደ ኮምቦልቻና
ደሴ በሚወስደው የአስባልት
መንገድ ላይ 11
ኪ.ሜ ከተጓዙ በኋላ 5 ኪ.ሜ ወደ
ምስራቅ ጥርጊያ መንገድ ተከትለው
ወደ ውስጥ ሲገቡ የሚገኝ ታሪካዊ
መስጊድ ነው። ይህ በርካታ
ዓመታትን ያስቆጠረው የጡሩሲና
መስጊድ አሰራሩ እጅግ በጣም
የሚደንቅ የአባቶቻችንን የቤት
አሰራር ብቃት ያስመሰከሩበት
ነበር። በተለይ የጣራው አሰራር
ጥበብ በተለያዩ የእንጨት ጌጦች
(ዲዛይኖች) ያሸበረቀ በመሆኑ ያዩት
ሁሉ የሚደመሙበት ነበር።
.
ሌላው አጃኢብ የሚያሰኘው ነገር
የሙሶሶዎቹ ብዛት እና ውፍረት
ነበር በሰአቱ መስጊዱ ያለበት
መንደር ምንም እንኳን መኪና
የማይገባበት ቢሆንም አባቶች
ለቤቱ ይሆናል ያሉትን ዛፍ ከያለበት
በጥንቃቄ በመምረጥ ቆርጠውና
አስተካክለው ዳገት ቁልቁለቱን
በትካሻቸው ተሸክመው በመምጣት
ያቆሙት መሆኑ ጉድ የሚያሰኝ
ነው። የእያንዳንዱ ቋሚ እንጨት
ውፍረት በሁለት ሰዎች የማይታቀፍ
ከመሆኑም በላይ በጣም ረዥም
መሆኑ
እውነት በሰው ልጅ ሃይል
መተከላቸው ያጠራጥራል ።
.
ታዲያ በዚህ ውብ መስጊድ ዙሪያ
በርካታ የኸልዋ ቤቶችን ስለተሰሩለት
የኢልም
መንደር ሆኖ አያሌ መሻኢኮች
ማፍራት ተችሏል ። መስጊዱን ልዩ
የሚያደርገው
ሌላው ነገር በቅጥር ጊቢው ውስጥ
የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ
ማለትም
የቡና ማፍሊያ ቦታ፣ የማር(ብርዝ)
ማዘጋጃ ቤት በውስጡ ማካተቱ
ነበር። በመስጊዱ የግምዣ ቤት
ውስጥ የተለያዩ እድሜ ጠገብ
የሆኑና የአሰራር ጥበባቸው በእጅጉ
ውበትን የተላበሱ የባህል እቃዎች
ማለትም ከእንስራ ያልተናነሱ
ጀበናዎች ፣ የቡና መውቀጫዎች
ከአንድ እንጨት ተፈልፍለው
የተሰሩ በጣም ጉዙፍና በርካታ
ባርሚሎች ፣ ቁጥራቸው ከ 500
በላይ የሆኑ ሲኒዎች፣ በጣም
ትላልቅ በእንጨት ተፈልፍለው
የተሰሩ የሲኒ መደርደሪያ
(ረከቦቶች ) እና ሌሎችም እድሜ
ጠገብ ውብ የባህል ቅርሶች
ይገኙበት ነበር ። በጡሪሲና መስጊድ
የተለያዩ መንፈሳዊ ከንውኖች
ቂርአቶች ደርሶች የሚሰጡበት
ቢሆንም በዋናነት ግን የነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል ( መውሊድ)
በሰፊው ይከናወንበት ነበር።
ለበዓሉም ድምቀት ከ 20 በላይ
ግመሎች እና በርካታ በሬዎች
ይታረዳሉ ስጋውም ለበዓሉ
ታዳሚዎች መስተንግዶ የሚውል
ነበር ። ኘሮግራሙን የታደመው
ሁሉ የማይረሳው ልዩ ነገር ደግሞ
ሌሊት ላይ ለጋ የማር ብርዝ
ተዘጋጅቶ በክቡር ዘበኛ(መጠጫ)
በሰልፍ በሰልፍ በሚመጡ
ካዳሚዎች በስነ-ስርዓት ይታደላል ፣
በአንድ ትርጎ ላይ ከ 80 እስከ 100
ሰንደሎች ተሰክተው ህዝቡን
በመልካም መአዛ ያውዱታል ።
.
እንግዲህ ወገኖች ይህ ታሪካዊ
መስጊዳችን እነዚህን ሁሉ ትዝታ
ይዞ በነበር እንድናወራ ሰሞኑን
በ2010 መባቻ በ ጳጉሜ 3 ላይ
በአሳዛኝ ሁኔታ ያጣነው ። አንድን
ህዝብ ህዝብ የሚያሰኘው ታሪኩ
ነው ታሪክ የሌለው ህዝብ ሙሉ
አይደለም ታሪካዊ መሳጂዶቻችን
በተለያዩ ምክንያት ፈርሰዎል
የቀሩትም እድሳትና ጥበቃ
ስለማይደረግላቸው በመፍረስ ላይ
ይገኛሉ። ሙስሊሙ ታሪክ አለኝ
ሲል ከቅድመ አያቶቹ የተረከበውን
በማስረጃ እያሳየ ሊሆን ይገባል ።
በክብር የተረከበውን ታሪኩን ጠብቆ
ለትውልድ ማሳለፍ ደግሞ አሁን
ላይ ያለነው የእኛ ኃላፊነት ነበር።
በተለይ ደግሞ እንደነዚህ አይነት
ታሪካዊ ቦታዎችን ማጣት ጉዳቱን
እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ምክንያት
ከተባለ አንደኛ አባቶቻችን
አስከፊውን የፊውዳል (የአፄዎች)
የጭቆና አገዛዝ ለመቋቋም እና
ሃይማኖቱ ላይ ይደርስ የነበረውን
ዘመቻ ለመመከት የተጠቀሙበትን
ስልት እንዴት እንደነበር ለትውልድ
ሳይተላለፍ መቅረቱ ሲሆን ሌላው
ደግሞ በዚህ አስከፊ ዘመን
የኢልም ቦታዎች ሲፈራርሱ
በዙሪያው የነበሩ መሻኢኮችና
ተማሪዎች ያለ መስጊድ መኖር
ባለመቻላቸው መበተናቸው ችግሩን
አስከፊ ያደርገዋል ።
.
የኦሮሚያ ዞን አለኝ ከሚላቸው
ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦቹ መካከል
የሾንኬ መስጊድ ፣ የዶዶታ መስጊድ ፣
የሙፍቲ መስጊድ፣ የፈቂህ አባስ
መስጊድ፣ እና ይህ እንደዋዛ
የፈረሰው የጡሩሲና መስጊድ አንዱ
ነበር። የከሚሴ ዞኑ በዚህ የህዝብ
ሃብት በነበረው ታሪካዊ መስጊድ
ዙሪያ ምን ማድረግ እንዳሰበ
ለጊዜው ባይታወቅም እኛ ግን
እንደ ህዝብ የከሚሴ ባህልና
ቱሪዝም መምሪያ የሆነ መፍትሄ
እንዲያመጣ እንጠይቃለን ።
አንድም ከአደጋው የተረፉ የቤቱ
ቅሪቶች አልያም የባህል ቁሳቁሶች
ካሉ ህዝቡን በሙሉ አስተባብሮ
መልሶ የሚተካበት ሁኔታ ቢፈጠር
መልካም ነው ካልሆነ ግን
የአከባቢው ማህበረሰብ ይህንን
ታሪካዊ ስፍራ ወደ ነበረበት ቦታ
ለመመለስ ሊረባረብ ይገባል ።
.
ይህ የሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን
የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪክ ነውና ።

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a comment