ኢሀድግ አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ 4ኛው አጼ

BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ
የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ የ1966
የሙስሊሞች መብታችን ይከበር
ብሔራዊ ጭቆና ይብቃ ጥያቄ
ከተነሳ ከ22ዓመት በኋዋላ የ1987
የሙስሊሞች ተቁዋማዊ ጥያቄ
የተቀሰቀሰው።
ዛሬ ከ 22 ዓመት በኋዋላ ደግም
እየተገፋን እህህ ስንል ጥቂት
የማይባሉት በእለት አስቢዛ
እየተሸነገሉ፣ በሥልጣን እየናወዙ፣
በንግድ ሥርዓቱ በፍርሃት እየራዱ ፣
በአፈሙዝ ጫና እየሰጉ፣ በየጉያችን
ያለመተማመን የተደበቀ ቦንብ
ተሸጉጦ ፣ መገፋቱን በዝምታ ውጦ
ባለበት ሁኔታ የአወልያ ብላቴናዎች
በለኮሱት አብዮት ውስጥ
“የዱምፃችን ይሰማ ንቅናቄ” ነፍስ
ዘራን።
3 ጥያቄዎች ተይዞ ማኅበረሰባዊ
ንቅናቄ ተፈጠረ።ሙስሊሞቹ
በሰለጠነና በሠላማዊ መንገድ
መንግሥትን ሞግቱዋል።
ጠይቁዋል።ከአራት ዓመት በላይ
የትግል ውጥረት ውስጥ
ቆይቱዋል። ዛሬም ጥያቄው
አልተመለሰም።መጠየቅ እንጂ
መልስ መንጠቅን ያልታደልንበት
ታሪካዊ ድግግሞሽ ግን ያሳምማል።
ለሕዝብ ጥያቄ መልስ የማይሰጥ
..የሕዝብ ድምፅ የማይሰማ
ሥርዓት…አንባገነናዊ ጉዞ እድሜው
ስንት ይሆን? ይህን የእንጨት
ሽበት ሥርዓተ ዕድሜ የሕዝባዊ
ንቅናቄ አብዮት ያከስመው ይሆን?
የሚል ሙግት ውስጥ አንገባም።
በዚህ ጥያቄ መነቃቃት አሁን
በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት
በወቅቱ በወሰደው የጅምላ
እርምጃ እስር፣ እንግልት፣ ስደት እና
ሞት የብዙ ሙስሊሞችን አንገት
አሰብሩዋል።በፍርሃት
አርዱዋ።በርካታ ተቁዋሞች
አክስሙዋል።ዳግም ከ22 ዓመት
በኋላ የድምፃችን ይሰማ ሠላማዊ
ንቅናቄ ብቅ አለ።
አሁን የተጠራቀመ ጥያቄያችንን
ለማስመለስ 22 ወራት ወይስ 22
ዓመት?ጥያቄ ነው።
ህዝባዊ ብሶት በገነፈለባት ሀገር
ሙስሊሞች የትግል ትከሻ ብቻ
ሳይሆን የሚና ባለቤት የማይሆኑት
ለምን ይሆን?በሥልጣን ላይ ባለው
መንግስት መገዛት ከጀመርን ጊዜ
ጀምሮ ሃይማኖታችን መሰረት
ባደረጉ ግጭቶች የረከሱብን
የሃይማኖት ተቁዋሞች፣ “ዋ!
ኢስላማ “በሚያስቡል ሁኔታ ክብር
ያጡ ሒጃቦች ፣ የተሰበሩ ህሊናዎች
፣የፍርሀት ጊዜዎች ፣የስጋት ወቅቶች
፣የህሊና ጠባሳዎች ፣የአካል ጉድለቶች
የተቀጠፉ ሕይወቶች የሥርዓቱ
የግፍ ኒሻን ናቸው።
ይህ በሃይማኖት ክብረ በዓል ዙሪያ
የሚዳቀኑት ታንኮች አማኙን ከበው
የሚወሩት አፈሙዞች በቅርቡ
በኦሮምያ የሬቻ ክብረ በአል ላይ
የተፈጠረው ዘግናኝ እልቂት የሰው
የማምለክ ነፃነት የት ሀገር ይገኛል?
እንድንል ያደርጋል።
የሃይማኖት ሥርዓት ከወታደራዊ
አጀብ እና ከአፈሙዝ ጥላ ነፃ
አድርጉልን።
ጥያቄያችን ዛሬም መልስ ይሻል

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
Aside | This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s