ባዶ ንፁኃን እጆች VS የታጠቀ ነፍሰ-ገዳይ የ’ስከዛሬዎቹ ሠላማዊ ሠልፎች ዋነኛ መንስኤ ጭቆና የወለደው የብሶት ጥርቅም ሲሆን እንዲሁም ጥያቄው የጥቂት ሰዎች ሳይሆን ሕዝባዊ አብዮት መሆኑን በግልፅ ለማሳየትም ጭምር ነበር፡፡ ይህም ሆኗል፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ግልጽ ነው፡፡ የወያኔን ግፍ ያልተረዳ ኢትዮጵያዊ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህም ነበር መላው ኢትዮጵያዊ ከሙስሊሙ ሠላማዊ ተቃውሞ አንስቶ እስከዛሬም ድረስ ለ5 አመታት ያህል ባዶ እጁን እስካ’ፍንጫው ድረስ ከታጠቀ ኃይል ጋር ሲተናነቅ የኖረው፡፡ ወያኔ መቼም ቢሆን ስልጣኑን መቆናጠጥ እንጂ ለሕዝብ ደም መፍሰስ ደንታ የሌለው በመሆኑ አሁንም ያላ’ንዳች ከልካይ መግደሉን መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ በባዶ እጅ ከጥይት ጋር የሚደረገው ልፊያ በዚሁ ሊገታ ይገባል፡፡ ሕዝቡ በአሁኑ ወቅት የሚፈልገው 2 ነገር ብቻ ነው፡- 1. ከወያኔ የሚከላከለው የታጠቀ ሚሊሺያ ((ትጥቅ)) እና 2. መረጃ የሚለዋወጥበት የመገናኛ መንገድ ብቻ እነዚህን ሁለቱን ወሳኝ ነገሮች ማድረግ ከተቻለ ወያኔ ለአንድ ሰሞን እንኳ ፀንቶ መቆየት ሚችል አይመስለኝም፡፡ ከጅምሩ እሱን ማፍረክረክ ይቻላል፡፡ የወያኔ ኃይላትም ቢሆኑ በታጠቀ ሕዝብ ላይ ከመተኮሳቸው በፊት የሚያስከፍለውን ዋጋ ቆም ብለው ሁለት ጊዜ እንዲያስቡ ይገደዳሉ፡፡ የኃይል ሚዛኑ ለሕዝቡ ማጋደሉ እርግጥ ሲሆን የመከላከያ ወታደሩ ሳይቀር አምፆ ወያኔን በመክዳት በሂደት ከሕዝቡ ጎን መሰለፉ አይቀሬ ነው፡፡ ካ’ሁን በኋላ እራሱን ከወያኔ ነፍሰ-ገዳዮች የሚከላከልበት መሳሪያ የሌለውን ሕዝብ ባዶ እጁን ወደ አደባባዮች ማስወጣቱ መቆም ይኖርበታል፡፡ ቀጣዩ ቅድሚያ የሚሰጠው ሥራ ሕዝቡ እራሱን የሚከላከልበትን መንገድ ማመቻቸት ሊሆን ይገባል፡፡ የዚያኔ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ማናገር ይቻለዋል፡፡ ወያኔም እንደ በረዶ ክምር ቁልቁል ይምዘገዘጋል፤ ኢንሻአላህ፡

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s