የኢህአዴግ መንግስት በዜጎች ላይ
የከፈተው የተስፋ ማስቆረጥና
የማሸማቀቅ ጦርነት በጋራ ሆነን
እንከላከል ።
•••••••••••••••
••••••••••••••• ••
————— ———
ኢህአዴግ የስልጣን ጥማቱን ገና
አለቀቀውም
ከአሁን በኃላም ቢሆን ለ100
አመት ያክል ለመግዛት ያስባል
እቅዱም ነድፎ በሰፊው
እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ለስልጣኑ አስጊ ወይም ተቀናቃኝ
የሆኑ የትኛውንም አካል ወይም
ፍጡር ከማጥፋት እንደማይመለሰ
በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ
አሳይቷል።
በእርግጥ ይህንን አላማውን
የሚያሳኩለት የሀገሪቷና የህዝቦቿ
የሆኑትን ታላላቅ ተቋሞችን በእጁ
ስር አድርጓቸወል ።
የመከላከያው ሀይል
የፖሊስ ሀይልና
የደህንነት ተቋሞችን ለአላማው
መሳከት ከፍተኛ አስተዋፅኦ
አድርገዋል።
አላማቸው የኢትዮጵያን ህዝብ
ከጨቋኙ ስርአት ለማላቀቅ ነበር
ብለው ነበር። ዛሬ ግን የኢትዮጵያ
ህዝብ የናፈቀው ነፃነትን
ሳይስገኙም በእራሳቸው የስልጣን
መያዣና የሀብት ማግበስበሻ ትራክ
ውስጥ ገብተው ያንን ያክል
መስእዋት የሆነላቸው ህዝብ
ረስተውታል ።
በየ 5 አመቱ የሚደረገው
የይስሙላ ምርጫም የምእራቡ
ሀገራት እርዳታ ማግኛ ከመሆን
ውጪ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዘየደው
ነገር እንደሌለ ታይቷል።
ምርጫ በመጣ ቁጥር ዜጎች
የሚታሰሩባትና የሚገደሉባት
ምድር ሆናለች ኢትዮጵያ
እነሆ ኢህአዴግም አሁን አጠናክሮ
ቀጥሎበታል ።
አምባገነኖች በባህርያቸው ምርጫ
አለርጅካቸው በመሆኑ ገና በሩቅ
ሆነው ነው የሚፈሩት።
ለዚህም ነው ኢህአዴግ
ተቃዋሚዎችን ማዋከብና ማሰር
የግል ሚዲያው መዝጋት እና
ጋዜጠኞችን ማሰር ወይም ከሀገር
እንዲሰደዱ ማድረግም
ይገኝበታል።
በሌላ በኩል ህገ መንግስታዊ
መብቱን እየጠየቀ ያለው
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ቀላልና
ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ
በማን አለብኝነት የማዋከብ
የማሰር እና የመግደል ስራው
አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
ከዚህም በላይ የሚተገብረው ነገር
እንዳለ ለመረዳት ብዙም
አያዳግትም።

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s