ስማቸው ማሊክ ኢብኑ አነስ ኢብኑ
ማሊክ ኢብኑ አቢ አምር ሲሆን
ቅጥያ መጠሪያቸው አቡ አብዱላህ
(የአብዱላህ አባት) ነው። የዘር
ሀረጋቸው ሲተነተን ማሊክ ኢብኑ
አነስ፣ ኢብኑ ማሊክ፣ ኢብኑ አቢ
አምር፣ ኢብኑ ሃሪስ፣ ኢብኑ
አይመን (ዑስማን)፣ ኢብኑ ኹዘይል
(አል-አስባሂይ በየመን የነበረው
ሂምያር የተባለው ገዥ ነገድ
ቅርንጫፍ)። ኢማሙ ሱዩጢ
(ረሂመሁላህ) ሲናገሩ የኢማሙ
ማሊክ የዘር ሐረግ ወደ ያዕረብ
ኢብኑ ያሽጃብ፣ ኢብኑ ቀህጧን
ይመዘዛል።
በሌላ በኩል እንደተዘገበው ደግሞ፡-
ዝሁ አስባህ፣ አል-ሃሪስ፣ ኢብኑ
ማሊክ፣ ኢብኑ ዘይድ፣ ኢብኑ ገውስ፣
ኢብኑ ሰዕድ፣ ኢብኑ አውፍ፣ ኢብኑ
አዲ፣ ኢብኑ ማሊክ፣ ኢብኑ ዘይድ፤
ኢብኑ ሳህል፣ ኢብኑ አምር፣ ኢብኑ
ቀይስ፣ ኢብኑ ሙአዊያ፣ ኢብኑ
ጃሻም፣ ኢብኑ ዐብድሻምስ፤ ኢብኑ
ዲዒል፣ ኢብኑ አልገውስ፣ ኢብኑ
ቁጥን፣ ኢብኑ አረብ፣ ኢብኑ ዘሂር፣
ኢብኑ አይመን፣ ኢብኑ ሁምስ፣
ኢብኑ ሂምያር፣ ኢብኑ ሰባዕ፣ ኢብኑ
ያሽጃብ፣ ኢብኑ የዕረብ፣ ኢብኑ
ቀህጧን ተብሎ ተዘግቧል።
የኢማሙ ማሊክ የእናታቸው ስም
አሊያህ ቢንት ሻረክ ኢብኑ
አብዱረህማን አል-አዝዲያህ
ያባላል።
ሌላው ከእርሳቸው ጋር ተያያዥነት
ያለው ስያሜ “ኢማሙ ዳሩል
ሂጅራ” እና “አል-
መደንይ” (አብዛኛውን ጊዜያቸውን
መዲና ስላሳለፉ ነው ይህን ስያሜ
ያገኙት) ተጠቃሽ ናቸው።
ልደት
ሀፊዝ ኢማሙ አዝ-ዘሃቢ፣ ሰምዓን
ኢብኑ ፈርሑንና ሌሎች
እንዳስቀመጡት በዕድሜ ትልቅ
በሆነው ደረሳቸው በየህያ ኢብኑ
ቡኸይሪ ዘገባ መሰረት ኢማሙ
ማሊክ የተወለዱት በ93 ዓ.ሂ ነው።
ሌሎች በ90 ዓ.ሂ፤ አንዳንዶች
ደግሞ በ95 ዓ.ሂ የሚል ዘገባ
አስተላልፈዋል። ያፊዕ “ጦበቃቱል
ፉቀሃእ” በሚባለው ኪታባቸው
በ94 ዓ.ሂ የሚል ፅፈዋል። በተለየ
ሁኔታ በእናታቸው ማህፀን ውስጥ
ከተለመደው ዘጠኝ ወር በላይ
ተቀምጠዋል። መዲና ውስጥ
ከመወለዳቸው በፊት የተወሰኑት
ሁለት ዓመት ሌሎች ሶስት ዓመት
በናታቸው ማህፀን ቆይተዋል
ይላሉ።
አካላዊ ሁኔታ
ሙጠረፍ ኢብኑ አብዱላህ አል-የሳሪ
እንደተናገሩት ኢማሙ
በቁመታቸው ረጂም፣ ደልደል ያለ
ሰውነት ያላቸው፣ ብሎንድ ፀጉር፣
ትልልቅ አይንና አፍንጫ ያላቸው፣
ግንባራቸውም ሰፋ ያለ ነበር።
ኸሊፋዎቹ ዑመርና ዐሊም
(ረዲየላሁ ዐንሁም) እንደዚህ
እንደነበሩ ይነገራል። እጅግ ብዙና
ወፍራም እሰከ ደረታቸው የሚደርስ
ፂም ነበራቸው። የቀድሞ ቀመስ
ፀጉራቸውን ወደ ከንፈራቸው
ጠርዝ ያሉትን በመከርከም ሙሉ
ለሙሉ ማስወገዱ ተገቢ እንዳልሆነ
ይናገሩ ነበር። የኸሊፋው ዑመር
ኢብኑል ኸጧብን (ረ.ዐ) ሱና ይከተሉ
ነበር፤ ዑመር በሆነ ጉዳይ ላይ
ጥልቅ ሀሳብ ሲይዛቸው የቀድሞ
ቀመስ ፀጉራቸውን ወደ
ከንፈራቸው አቅጣጫ እየጎተቱ
ያሰላስሉ ነበር። ከዚህ ተነስቶ
ዑመር በሁለቱም ከንፈራቸው ላይ
ፀጉር እንደነበራቸው ይነገራል።
በጣም የተዋቡና ውድ ነጫጭ
ልብሶችን መልበስ ያዘወትራሉ፤
ቶሎ ቶሎ ይቀይሯቸዋል፤
በልብሶቻቸው ላይ ሚስክና ሌሎች
ሽቶዎችን መቀባት ይወዳሉ።
ጥምጣማቸውን ግማሹ ተርፎ
በአገጫቸው ስር የሚደርስ ሲሆን
ጫፎቹ (ጎፍላው) በሁለቱ
ትከሳቸው መሃል ላይ ያርፋል።
በተጨማሪም ፎጣ መሰል ልብስ
የሚለብሱ ሲሆን ከራሳቸው እስከ
ትከሻቸው ያለውን አካል ይሸፍናል።
ትምህርትና ዕውቀት
የኢማሙ ማሊክ ቤተሰብ በራሱ
የዕውቀት ማእድ ነበር።
ህፃንነታቸውን በአትክልት
በተዋበችው መዲና ነው ያሳለፉት።
ቁርአንን የተማሩትና በቃላቸው
ያጠኑት (የሀፈዙት) ገና
በህፃንነታቸው ነበር። ቁርአኑን
የቃሪኦች መሪ በሚባሉትና
ለዘመናችን አነባበብ መሰረት
ለጣሉት በ169 ዓ.ሂ ከዚህ ዓለም
በሞት በተለዩት ናፊዕ ኢብኑ
ዐብዱረህማን ላይ ቀርተዋል።
የመቅራትና የማስተማር ፍቃድ
ሰነድ (ኢጃዛ) ከርሳቸው ተቀበሉ።
መጀመሪያ ዕውቀትን ፍለጋ በወጡ
ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ዕጥረት
ገጥሟቸው ነበር። ይህንንም
ለማሟላት የቤታቸውን የጣሪያ
ማገዶች በመሸጥ መፅሀፍቶችና
ወረቀቶች ገዙ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ
ግን ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ
(ሱ.ወ) በርካታ ሐብትና ገንዘብ
ለገሳቸው። የኢማሙ በቃል
የማጥናት (ሽምደዳ ችሎታ) እጅግ
የሚገርም ነበር። በሽምደዳ፣
በሐዲስና በፊቂህ ከሂጃዝ ሰዎች
የሚደርስባቸው እንዳልነበረ
ተዘግቧል። ኢማሙ ሻፊዒይ
(ረሂመሁላህ) ሲናገሩ ማሊክና
ኢብኑ ዑወይናህ ባይኖሩ ኖሮ
የሂጃዝ ዒልም ተኖ ይጠፋ ነበር
ብለዋል። ኢማሙ ዘሃቢ ሲናገሩ
ከታቢዒዮች በኋላ ከኢማሙ ማሊክ
ጋር በዕውቀት፣ በፊቂህ፣ በዝናና
በሽምደዳ ሊወዳደር የሚችል
ፈፅሞ አልነበረም ይላሉ።

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s