መታሰቢያነቱ በጓንታናሞ አብሮኝ ለነበረው ጓደኛዪ።

Anwar Temame
የልብ ወዳጄ
ከዚህ ጓደኛዪ ጋር እንዴት እና መቼ
እንደተግባባን አላስ
ታውስም።ብቻግን ለብዙ አመታት
እኔ ያለሱ እሱ ያለኔ የማንታይ የልብ
ወዳጆች ሆነን አሳልፈናል።ከዚህ
ጓደኛዪ ጋር የሚያራርቀን ነገር ቢኖር
ቁመት ነው።እሱ ለፀሀይ ቅርብ
ሲሆን እኔ ደግሞ ለመሬት ቅርብ
ነኝ።ይህ ወዳጄ ረጅም ከመሆኑ
የተነሳ አብረን ጎን ለጎን እየሄድን
እኔን ማየት ስለሚቸግረው እና
የምናገረውን ለማድመጥ ወደታች
ጎንበስ ማለት ረጃጅም ቅልጥሞቹ
ስለማይሰጡት አብሬው
እየተራመድኩኝ እንኳን
ይደውልልኛል።አንዳንዴ ሲያበሽቀኝ
ረጅም ወይ ሞኝ ነው ወይ በረኛ ነው
እለዋለሁ፣እሱም የዋዛ አይደለም
ስማ አጭር ሰዉ እንቅፋት ነው ወይ
ተንኮለኛ ነው ይለኛል (እንደቁመቱ
ምላሱም ረጅም ሳይሆን
አይቀርም)።ሰዎች ስለመለሎ ቁመቱ
ስለደንዳናው ሰውነቱ ሲያወሩ
አልገረምም ከዚያ ይልቅ ከብዙ
ረጃጅሞች እና ፈርጣማ ጡንቻ
ያላቸው ሰዎች ላይ የማይስተዋል
አክብሮት እና አስተዋይ አምሮ ን
የተቸረበመሆኑ ያነገሩ ይበልጥ
ይማርከኛል።አሁን ይሄን ሰው እንደ
ዳይኖሰር አመፀኛ ቢያረገው ማን
ነበር የሚመልሰው?፣በጡንቻው አስቦ
ቢሆን ኖሮስ ስንት ደካሞችን
በጨፈለቀ፣ነበር።ሁሉን ቻይ አላህ
እንደግመል አገራው እንጂ••••••
°
እናንተዪ ጊዜ ግን እንዴት ነው
ባካችሁ እንደ፣አቦ ሸማኔ ወደፊት
የሚወረወረው።ከዚህ የነብስ ወዳጄ
ጋር ውል በሌለው የሂወት ጥልፍልፎሽ
ተተብትበን የየራሳችንን የኑሮ ጥጥ
መፍተል ከጀመርን 10አመታት
አለፈን።
አቤት ያን ጊዜ እሮጦ በማይደክመው
አፋላው ጉልበታችን ኳስ ተጫውተን
እንመጣ እና በእንጀራ ብቻ
የማይመለሰው ሆዳችንን በመረቅ
ለመሙላት በየ፣ልኳንዳ ቤቱ የበግ እና
የበሬ ቅልጥም ፍለጋ
ተሽከርክረናል።ይህን በማድረጋችነ
ስንት ውሾች በክፉ አይን አይተውናል
።እኛ ቀለባችሁን ነው የበላንባችሁ
ቻይናዎች ቢያገኝዋችሁ ግን እናንተን
ነው የሚበልዋችሁ ብለን በውሾቹ
አሹፈናል።ስንት ጊዜ የበሬውን እና
የበጎቹን እግር እንደጫማ ጥንድ
ጥንድ አርገን እየለየን ሸሆናቸው ላይ
ቁጥር ፅፈናል።ቻርሊ ቻፖሊን
ጫማውን ቀቅሎ የሚበላበትን
ፊልም እያየን እኛ የእንስሶቹን
ጫማ ቀቅለን መረቁን
ጠጥተናል።ስንት ስጋ ነጋዴዎች
ቢላቸውን ከሞረድ ጋር እያፋጩ
ስንት ኪሎ ይሀየንላችሁ ሲሉን
የበሬውን እግር ፈልገን ነው
ስንላቸው በመገረም ስቀዋል።
እናንተዪ፣ዘመኑ፣እንዴት፣
ነው፣ባካችሁ፣እንደ፣ሁሴን
፣ቦልት፣የሚቀደው፣
ከዚህ የልብ ወዳጄ ጋር አሁን እጅጉን
ተራርቀናል በችግሩና በችግሬ ግዜ
በንፁህ ወዳጅነት የተገነባው ፍቅር
የሆነየተለከርቭ፣ሰርቶ፣በ
ተለያየ፣አቅጣጫ፣ታጠፈ፣እ ሱ
በብርቱ እጆቹ መቀመጫውን
ሊያበጅ መዶሻ አንስቶ እጀ፣ጥበበኛ
ሆነ።እኔም በቀጫጭን ጣቶቼ
እጀ፣ብእረኛ ሆንኩኝ።
ከዚህ የልብ ወዳጄ ጋር ዛሬ በብዙ
ምክንያቶች፣ተራርቀናል፣አ
ልፎ፣አልፎ፣ስንገናኝ፣በደ
ስታ፣እየተያየን፣ስለብዙ፣
ነገሮች፣እናወራለን፣አንዳ ንድ ግዜ
ሳስበው ከብዙ መራራቅ በሃላ
ስንተያይ የምንሰጣጠው
የጋለ፣ሰላምታ በፊት ካደረጀነው ንፁህ
ፋቅር ላይ ተቀንሶ ወደዚ ዘመን
የተሸጋገረ፣ይመስለኛል።
በመጨረሻም ስንለያይ የማትሰማኝ
ጓደኛዪ ሆይ ካንተጋር ከተራራኩኝ
ወዲህ ብዙ የልብ ወዳጆችን
አፍርቻለው በወዳጆቼ ተከብቤ ዛሬም
ግን ማንም የማይደርስበትን
ወዳጅነትህን እንደምናፍቅ ማን
በነገረህ ብዬ በዝምታዪ ውስጥ
አውርቻለው።
መታሰቢያነቱ በጓንታናሞ አብሮኝ
ለነበረው ጓደኛዪ።

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s