እባክህ አትቸኩል ባል ከስራ ሲመለስ ከሚስት ጋር ትንሽ አለመግባባት ይፈጠርና መቆጣት ይጀምራል። ሚስትም የዋዛ አልነበረችም እሱ አንድ ሲል እሷ ሁለት እያደረገች አጸፋዊ ምላሽ መስጠት ቀጠለች። ትንሿ ክፍላቸው በአንድ ጊዜ ከሁለቱም አፍ በሚወረወሩ የቃላት ጥይቶች ወደ ጦር አውድማነት ተቀየረች። ሚስት በተደጋጋሚ ፍታኝ፤ በቃ ፍታኝ፤ ፍታኝ አልኩህ እኮ ከአንተ ጋር መቀጠል አልፈልግም የሚሉ ቃላትን መሰንዘር ጀመረች። እሺ እንግዲህ በቃ ፍቺ ከፈለግሽ ቀላል ነው ብሎ ከኪሱ ወረቀት በማውጣት የሆነ ነገር ከጻፈ በኋላ ከመሳቢያው ውስጥ ፖስታ አውጥቶ በማሸግ ይኸው የፍቺ ወረቀትሽን ያዢ ብሏት ከቤቱ ወጥቶ ሄደ። በንዴት ሀይለቃል ስትናገር የነበረችው ሚስት ከባሏ ቤቱን ለቆ መውጣት በኋላ ነገሮችን በጥሞና ማየት ስትጀምር ስህተት የሰራች መሆኗ ታወቃት፤ ያ ብዙ መስዋእትነት የከፈለችለት ትዳሯ እንደ ቀልድ ሲፈርስ ተሰማት፤ የኔ በሆነ ብላ ስትመኘውና በመጨረሻም ያሰበችው ተሳክቶ የግሏ ያደረገችውን ገና ከተጋቡ አመት እንኳን ያልሆነውን ምርጥ የትዳር አጋሯን አሳልፋ ለሌላ ሰው መስጠቷ ሲታወቃት የሰራችው ስህተት አብከነከናት። በፍጹም አይሆንም እያለች ማልቀስ ጀመረች። በዚህ መሀል ባል ተመልሶ መጣ። አንዲት ቃል ሳይተነፍስ ወደ መኝታ ክፍሉ በማምራት አልጋው ላይ ተቀመጠ። ሚስት እየተንደረደረች መጥታ ውዴ ስህተት ሰርቻለሁ፤ በሰራሁት ነገር በጣም ተጸጽቻለሁ፤ እባክህ ፍቺው እንዳይጸድቅ ቶሎ ብለህ ከሼኾች ፈትዋ ጠይቅልን አለች። ባልም የምርሽን ነው ከልብሽ ተጸጽተሻል? አላት። አዎ እባክህ ፍጠን ጊዜ አታባክን አለችው። እስቲ ፖስታውን ክፈቺና ጮክ ብለሽ አንብቢልኝ አላት። ፖስታውን ከፍታ ማንበብ ጀመረች፦ “ ያቺን ስወዳት፤ ሳፈቅራት፤ ለይል ሰግጄ ውዴን ለምኜ በስንት መከራ ያገኘኋትን ምርጥ ሚስቴን ለትንሽዬ አለመግባባት ብዬ የምፈታ ሞኝ አይደለሁም። እዚህ ዱንያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአኺራም የጀነት ውስጥ ሚስቴ እንድትሆኚ ነበር አላህን የለመንኩት። ስለዚህ ውዴ ወላሂ አልፈታሽም!!!” የሚል ነበር። ቀና ብላ የባሏን ፊት የምታይበትን አቅም በማጣት እንዳቀረቀረች ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። አይዞሽ ተረጋጊ የችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ ፍቺ ሳይሆን ፍቅርና ፍቅር ብቻ ነው አላት። ወንድ ልጅ ሆይ አላህ ፍቺን በአንተ እጅ ላይ ያደረገው እንደ “ትርፍ” ብር የትም እንድትመነዝረው ሳይሆን ነገሮችን አመዛዝነህ በብልሀት እንድትይዘው ነውና ለሁሉም ነገር ፍቺን ብቸኛ አማራጭ አድርገህ አትውሰድ። ዛሬ ዘለህ ፈትቼሻለሁ የምትላትን ሴት ለማግኘት ትላንት የተጓዝክባቸውን መንገዶች አስብ።

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s