የዒድ ሶላትን በኢሕአዴግ አሥተባባሪነት በአዲስ አበባ ስታዲየም አልሰግድም! ኃፍረት የለሹ የኢሕአዴግ መንግሥት ባለፉት ጥቂት ቀናት ቅሌታም ካድሬዎቹን በማሰማራት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላትን ‹‹ለዒድ ሰላት ውጡ፣ ትራንስፖርት ተዘጋጅቶላችኋል›› የሚል የቤት ለቤት ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚሰገደው የዒድ ሶላት ላይ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሙስሊም ሲወጣ እንደኖረ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የዘንድሮው ዒድ በ‹‹ጥቁሩ ሽብር›› ማግሥት የሚካሄድ ከመሆኑ ባሻገር፣ ሌላ ኢሕአዴጋዊ የሁከት ዕቅድ የተነደፈለት እንደመሆኑ፣ ህዝበ ሙስሊሙ የግፈኞች የሁከት ድራማ ሰለባ መሆን ያለበት አይመስለኝም፡፡ የዘንድሮውን የዒድ ሰላት በአዲስ አበባ ስታዲየም መስገድ፣ ‹‹ጥቂት አክራሪዎች ሁከት ለመቀስቀስ ቢሞክሩም፣ የፀጥታ ኃይሎች ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት የዒድ ስግደት በሰላም ተከናውኗል›› ለሚል የኢቴቪ ማላገጫ ግብዓት መሆን ነው፡፡ አምና ከስግደት በመመለስ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ያን ለመሰል አሰቃቂ ጭፍጨፋ እየተዳረጉ በነበሩበት ቅጽበት፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹‹ህዝበ ሙስሊሙ ስግደቱን አከናውኖ በሰላም ወደየቤቱ ገብቷል›› ብሎ ማላገጡ አይረሳም፡፡ በግሌ የዒድ ሶላትን በኢሕአዴግ አሥተባባሪነት በአዲስ አበባ ስታዲየም አልሰግድም!

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s