መንግስታዊ ሽብር በአንዋር መስጅድ ከጠዋት ጀምሮ ህዝበ-ሙስሊሙ ከተለያዬ አቅጣጫ ወደ አንዋር መስጅድ ይጎርፍ ነበር ከ5፡30 በፊት የኢቲቪ ካሜራ ማኖችና አጃቢ ሲቪል የለበሱ ፖሊሶችና ደህንነቶች መዲና ህንፃ ላይ ቦታቸውን መያዝ ጀመሩ 6፡30 የአንዋር መስጂድ ኢማም ኹጥባ ማሰማት ጀመሩ 6፡40 የጁምዓ ሶላት ከመሰገዱ በፊት ኢማሙ ኹጥባ እያሰሙ እያለ ከመስጅዱ ፊት ለፊት እየተሰራ ካለው የባቡር መንገድ ትላልቅ ድንጋዮች ቁጭ ብሎ ኹጥባ እያዳመጠ ወደነበረው ህዝብ መወርወር ተጀመረ። ከሙስሊሙ መሃል ተሰግስገው የነበሩት የመንግስት ሰዎችም መልሰው ድንጋይ መወርወር ሲጀምሩ ሰው ሊያስቆማቸው እየሞከረ እያለ ዱላ የያዙ ፖሊሶች ከፊት ለፊት ያገኙትን ሰው እየደበደቡ ለሶላት የመጣውን ሰው ማባረር ጀመሩ በዚህ ጊዜ ብዙ ሰዎች በፖሊስ ዱላና በተወረወረው ድንጋይ የተጎዱ ሲሆን የኢቲቪ ካሜራ ማኖች ሂደቱን ከመዲና ህንፃ ላይ ሁነው ይቀርፁ ነበር። በዚህ ግርግር በጣም አስደንጋጭና አሳዛኝ ከነበሩት ክስተቶች አንዱ ፖሊሶች ከመስጊዱ ወደ ተ/ ኋይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሚወስደውን መንገድ ለመስገድ ከመጡ ሰዎች ካፀዱት በኋላ ሲቪል የለበሱና ሙስሊም የማይመስሉ ሰዎች ሁለት ፖሊሶችን በአሰቃቂ ሁኔት በድንጋይና በዱል ሲጨፈጭፏቸው ማዬቴ ነው። ያአላህ! መንግስታችን ይህን ድራማ አስታኮ የሚወስደው እርምጃ ምን ያህል ወገኖቻችን ይታሰሩ፣ ይደበደቡ፣ ይገደሉም ይሆን?!

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s