ልንገርሽ ባገሬ ተፈteሮ ተዛብቷል ፈራሀ፣እግዜር ወጥቶ ፈራ መንግስት መጥቷል ሼህ ጥምጣም ጠምጥሞ በሀሰት ይፈርዳል ቄስ መስቀሉን ይዞ ለመንግስት ይሰግዳል ልንገርሽ ባገሬ ሁሉም ተቀይርዋል ሽፍታ ምንሽሩን በሬ ቀንዱን ጥልዋል የኔ ብሎ የለም ሁሉም የአንድ ነው እንኩአን መሬት ቀርቶ ህዝብ የመንግስት ነው ልንገርሽ በኔ ሀገር ሰዋሰው ተረስቷል ሰሙን ንጉስ ጦና ወርቁን አጤ ዩሀንስ ተቀራምተውታል ንብ ቀፎ ጠልታለች ኮሮጆ ነው ቤትዋ ማንም አይቀርባትም እሾህ አለ፣ፊትዋ ልንገርሽ ሀገሬ ሰው የሚጮህባት እንግዳ ተቀባይ ማእከላዊናት እስቲ ልጠይቅሽ ብርቅ ነው ባንቺ ሀገር ንጉስ ሰው ሰብስቦ ተረት ተረት መንገር ልንገርሽ ባገሬ አርብ አርብ ይዘመራል ሳር ቅጠሉ ሁሉ ፍትህ ፍትህ ይላል። ልንገርሽ ባገሬ ዘመነ፣ለውጥ ነው የማይለወጠው መንግስት ብቻ ነው። ልንገርሽ••••ልንገርሽ• ••ልንገርሽ

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s