ሰበር ዜና ከቂሊንጦ

ኮሚቴዎቻችን ዛሬም ድንቅ ታሪክ
ሰሩ ፡፡
በዛሬው ዕለት በቂሊንጦ ማረሚያ
ቤት በዞን አንድ ላይ ከፌዴራል
ጉዳዮች ሚኒስቴር በመጣ አንድ
ባለስልጣን አማካኝነት ኮሚቴዎቻችን
ጠዋት መደበኛ የመከላከያ ምስክር
ለማሰማት በወጡበት የዞን አንድ
ታሳሪዎችን በመሰብሰብ ስለ
ሽብርተኝነት ለመስጠት የፈለጉት
የተዛባ ትምህርት በድንቅ
ኮሚቴዎቻችን ሊከሽፍ ችሏል ፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደ
ተደረገው የመንግስት ባለ ስልጣናት
በዞን አንድ እና በሌሎች ዞኖች ላይ
ኮሚቴዎቻችን በሌሉበት ስለ ሽብር
እናስተምራለን በማለት
ኮሚቴዎቻችንን ለመወንጀል
ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው
መቅረቱ የሚታወስ ነው ፡፡
ዛሬም ሀምሌ አንድ መደበኛ
የመከላከያ ምስክራቸውን
ለማስደመጥ የታደሙት
ኮሚቴዎቻችን የድምፅ መቅረጫው
ተበላሽቷል በሚል ተልካሻ ምክኒያት
ከችሎት ቶሎ በተመለሱበት ጊዜ
ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
የመጣው ባለስልጣን ተሳሪዎቹን
በመሰብሰብ ላይ የነበረ ሲሆን
ኮሚቴዎቻችን ለመሰብሰብ
ፍቃደኛነታቸውን ባለመግለፃቸው
በፖሊስ ሀይል በግዳጅ እንዲሰበሰቡ
መደረጉን ምንጮቻችን ዘግበዋል ፡፡
በስብሰባው ላይ ከፌዴራል ጉዳዮች
የመጣው ባለ ስልጣን ስለ ሽብር
የተዛበ ገለፃ ካደረገ በኃላ ጋዜጠኛ
አቡበከር አለሙ እጁን በማውጣት
<> በማለት ድንቅ ንግግር
አሰምቷል ፡፡
የህግ ባለሙያ የሆነው ዑስታዝ ካሚል
ሸምሱም ሰለ ፀረ-ሽብር ህጉ ሰፊ
ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን ከሶስት አስከ
አራት ጥያቄዎችን ለባለ ስልጣኑ
አንስቷል ፡፡
ባለስልጣኑ ሽብርን ከአንድ ሀይማኖት
ጋር የተያያዘ በማስመሰለ ሲያስተምሩ
የነበሩ ሲሆን ካሚል ሸምሱም እኛ
የታሰርነው ባዕድ ሀይማኖት በግድ
ሲጫንብን አንቀበልም በማለታችን
ነው ፡፡እንደውም ዶ/ር ሺፈራው
የማያውቁትን እና የራሳቸው ያለሆነን
ሀይማኖት በግድ ሲጭኑብን ነበሩና
መታሰር ያለባቸው እሳቸውና
መሰሎቻቸው ናቸው ፡፡
ሀይማኖት በግድ አይጫንብን
፣መጅሊስ ከካድሬዎች ይፅዳ ስላልን
እንዴት እንታሰራለን ? እስካሁን
ሽብር ፈፅሞ የታሰረ አንድም እሰረኛ
የለም ከናንተ አስተሳሰብ የተለየ
አስተሳሰብ ስላለን ብቻ ነው
የታሰርነው ብሏል ፡፡
በስተመጨረሻም ስለ ሀይማኖት
መቻቻል ዛሬ እንዴት ትነግሩናላችሁ ?
በሀገራችን እስላም ክርስቲያኑ ተዋዶ፣
ተከባብሮና ተዋልዶ ለረጅም አመታት
ኖረዋል፡፡መንግስት የሚሰራቸው
ይህንን የሚያፈርሱ በኢቲቪ
የሚቀርቡ ዶክመንታዎች አሳዛኝ
መሆናቸውን ሲገልፁ በስብሰባው
የታደመው እስረኛ ድጋፉን ገልፃል ፡፡
ዑስታዝ አህመድ ሙስጠፋም እኛ
ሽብር ነው የተፈፀመብን ይህን
መንግስት የምንከስበት ቦታ ካለ
እባካችሁ ጠቁሙን ፡፡ይህ መንግስት
22 ዐመት በህዝብ ላይ ሽብር
ሲፈፅም ነው የቆየው በማለት
አስደናቂ ንግግር ማድረጉን
ምንጮቻችን ዘግበዋል ፡፡
አላሁ አክበር !
አላሁ አክበር !
አላሁ አክበር !

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s