ረመዷን ውስጥ ፆመኞችን
በማስፈጠር ወደ አላህ (ሱ.ወ)
ለመወደድ ጥረት እናደርጋለን።
ይህን የምናደርገው ሰው
ስላደረገ አሊያም ከሰው እይታ
ለመግባት አስበን ሊሆን
ይችላል። በዚህ ረመዷን ግን
ስናስፈጥር የሰውን ሙገሣ
ከመፈለግም ሆነ ከትችቱ
ለመራቅ እንዳይሆን
እንጠንቀቅ። ለይዩልኝ
መሥራት ከአላህ ዘንድ ምንም
ምንዳ አያስገኝምና።
ጾመኛን ማስፈጠርና የተራበን
ሆድ ማጥገብ የሚወደድ እና
ነቢያዊ ሱና ነው። ነገርግን
ከዚህ በላይ የተራበን የሰው
ልጅ ቀልብ ማጥገብ የሚፈለግ
ግዴታ ነው። በዚህ በኩል
ከፍተኛ ጥረት ማድረግ
ይኖርብናል። እኛ ልብ ያላልነው
ስንት ምክር የተጠማ ሰው አለ!
እኛ ያላስተዋልነው ስንት
በስሜት ውስጥ የሚዋኝ አዳኝ
የሚፈልግ ፍጡር አለ!
ከሰጋጆች ጋር ጎን ለጎን ስንቆም
ከሁሉም ጋር የምንተዋወቅ
ሆነን አይደለንም። ነገርግን
ቀልባችንን እንዲተዋወቅና
አንድነታችን እንዲጠናከር አንድ
ነገር ማወቅ ይገባናል።
ከኢማሙ በኋላ ለሰላት
ስንሠለፍ ሰልፍን ማስተካከል
የአማኞችን ልብ ያስተሣስራል፤
አንድነታቸውንም ያጠናክራል።
ለኛም ሆነ ለዲናችን አደገኛ
ጠላቶች አሉ። ከሃዲያን ከሆኑ
ዱዓእ በማብዛት በነርሱ ላይ
ድልን እንቀዳጅ። ሙስሊሞች
ከሆኑ አላህ ሀቁን
እንዲያሣያቸው። ዱዓእ ጠላትን
ወደ ወዳጅ ይለውጣል። አላህ
መልካም አገልጋዮቹን ያግዛል።
በረመዷን ውስጥ የሙስሊሞች
እጅ እንደሚፍታታ ያውቃሉና
በየጎዳናዎችም ሆነ በመስጅድ
በር ላይ ችግረኞች
ያጋጥሙናል። ነገርግን እኛ
የማናያቸውና የማናውቃቸው
ብዙ ችግረኞች አሉ። የሰው
ዓይን የማየት እፍረት፣ በሽታ፣
አካለ ስንኩልነትም ሆነ ሌላ
ነገር ወጥተው ከመጠየቅ
ያገዳቸው። እነሱን
እናስታውሣቸው። ባሉበትም
ሄደን እንርዳቸው።
በየዓመቱ የረመዷን ወር
ደረጃና ትሩፋት ይዘከራል።
እኛም የሚባለውን ሁሉ
በተደጋጋሚ ስለሠማን
ተላምደን መለወጥ አቅቶናል።
በዘንድሮ ረመዷንን ግን
የታላቁን ወር ደረጃ ከልብ
እናጢን። የግምቱንም ያህል
ዋጋ እንስጠው።
ለይለቱልቀድር የረመዷን ዋጋ
ከፍ ከሚያረጉ ነገሮች አንዷ
ናት። እኛም ብዙ ረመዷንን
ፆመናል። ለይለቱልቀድርን
ስለማግኘታችን ግን አላህ ብቻ
ያውቃል። ዘንድሮን ግን ሆነ
ብለን ይህችን ታላቅ ለሊት
ተግተን እንፈልጋት። እስከዛሬ
አላገኘናት ይሆናልና።
ረመዷንን ስንሠናበት አሊያም
ሲሠናበተን አላህ ለሚቀጥለው
ያደርሰን ዘንድ ለጌታችን አደራ
እንበለው። ሥራችንንም
ይቀበለን ዘንድ እንዲሁ።
የምንሰናበት ነገር ካጣን ያ
በርግጥም ትልቅ ጥፋት ነው፤
ለእድሜያችንም ትልቅ ኪሣራ
ነው። የተከለከለ ማለት አላህ
የከለከለው ነው።
ይህ በጥቂቱ ከላይ
የጠቃቀስነው በታላቁ ወርሀ
ረመዷን በር ላይ ሆነን
ውስጣችን የሚመላለስ ስሜት
ነው። ይህ ወር የኛ
እንዲሆንልን በርግጥ ቆርጠን
ተነስተን ይሆን! የወንጀላችንን
ቆሻሻ የምናጥብበት
ከምክሮቹም ቀልባችንን ህያው
የምናረግበት ወር ይሆንልን
ይሆን! ወይስ እሱም
እንደቀደሙት ረመዷኖች ሁሉ
ሣንጠቀምበት ያልፋል..…
ረመዷንን ለአዲስ ህይወት
ውጥን እናርገው። ወደ ጌታችን
ለመመለስ እውነተኛ
መንደርደሪያ ይሁነን።
ተሸቀዳድመን ከገበታው
መቋደሱ ለሁላችንም ግድ
ይላል።
ሙስሊሞችን ያዘናጋሽ ስንፍና
ሆይ ከቀልቦቻቸው ላይ ተነሺ..
የሙስሊሞች ሀሳብ ሆይ
ለመልካም ነገር ሁሉ ፍጠኚ
እሩጪ። ለመልካም ጥሪ
ፈጣን ምላሽ የሠጠ ሰው ምንኛ
ታደለ! ከበሩ የተባረረና
የተመለሠ ምንኛ ከሠረ! አላህ
ሆይ! ወደ ስኬት መንገድ
ምራን። ወዳንተ ለመመለስና
እጅ ለመስጠት አግዘን።
ለፀሎታችንም ምላሽ
አትንፈገን።
አላህ ሆይ! ረመዷንን
ባርክልን። ለፆሙና ለተራዊሁ
በተደጋጋሚ ከሚታደሉት
አድርገን። ከጀሀነም እሣት ነፃ
ከሚሆኑትም አድርገን።

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s