ተሀጁድ ሊቀር ነው ?
ወላሂ አሁን ዝሁር ላይ በኢማሙ
በኩል
የተላለፈው መልእክት
በትክክል መሞታችንን ያመለክታለወ
ኮካ
መስጂድ ነው ኢማሙ ተገደው
እንደሆነ ያስታውቃል ሳቅ እያሉ ነው
የሚያወሩት እናም እንዲህ አሉ
የተሃጁድ ሰላት እንዳይሰገድ
ተረሃዊም ባጭሩ
እንዲሰገድ ከበላይ ትዛዝ
ተላልፉዋል አሉ
ከዚህ በፊት የመሰጂድ ኮሚቴና
ጀመአው
መሹራ በማድረግ ነበረ የምንወስነው
አሁን
የሚተደደረው በመጅሊስ ስለሆነ
ተዛዙም
ከዛው ነው የመጣው አሉ
ኢናሊላሂ ተዲያ በትክክል
አልሞትንም?
ወላሂ ምን እንደምንጠብቅ
አላቅም !
እስኪ ወንድሜ # malcolm king
ግድግዳውላይ ከለጠፋት ፁፍ ጥቂቷን
ተውሼ
ላስነብባቹ !
ኣህባሽ የሚባል ከኢስልምና ያፈነገጠ
በኣይሁዳ የሚረዳ ሃይማኖት
ከሊባኖን ኣምጥቶ በግድ ቀይሩ ኣለን
ተደናግጠን እያለን ይግረም
ብሎ ደሃ ሲሞት ታጥቦ
የሚቀበርበትን ኮሌጅ
ኣወሊያን ኣስተማሪወቹን
ኣባሮ ወሰደው እንዴ ከዛስ? ከዛማ
ተማሪወች
ተሰባሰቡና
ኣስተማሪዎቻችን ይመለሱ ብለው
ተቃውሞ
ጀመሩ ከዛ ሌላውም
ኢትዮጲያዊ ተከትሎ ኮሚቴ ተመርጦ
መንግስትን የሚሰራው ነገር
ትክክል ስላልሆነ ወደ ራሱ
እንዲመለስ እሱ
ያዋቀረውንም መጅሊስ
ኣፍርሶ ሙስሊሙ እራሱ
የሚፈልገውን
በመስጊዱ እንዲመርጥ
እንዲፈቅድልን መልከተኛ ላክን
ከዛስ?
ወዲያው ደነገጡና ፈቀዱ
ኣይደል?ኣይደለም መጀመሪያ ጥሩ
መልስ
እንደሚሰጡንና
የኮሚቴውም ኣወቃቀር ህጋዊ
እንደሆነ
ነገሩንና መልሱን ከኣንድ ወር
ቡሃላ እንደሚሰጡ ነገሩን ሲገርም
ለመብታቹህ እንዴት ኣንድ ወር
ይቀጥራሉ ወዲያው
ኣይመልሱም፧ወር
ኣስጠብቀው ሁሉንም መለሱ
ኣይደል? ኣይደለም ጸባያቸው ሁሉ
ተቀያይሮ
ኣሸባሪ ምናምን ኣገር
ሚበጠብጡ ብለው ኣንድ ምሽት ላይ
ህጻን
ሴት ኣዋቂ ሳይመርጡ
መስጊድ ሰብረው በመግባት
ደብድበው ለሰደቃ
የተዘጋጀ ከበሬ ጀምሮ
ሁሉንም ነገር ወሰዱ እንዴ? ክዛ
ኢሄንን
ያደረጉ ለፍርድ ይቅረቡ
ብላቹህ ኣገር በጠበጣቹህ ኣይደል?
ኣይደለም
ጭቆናው ይቁም
ብለን ኣንዋር መስጊድ ላይ
ኣስጠነቀቅናቸው
ከዛስ? ከዛማ በበነጋታው
ጥያቄያችንን እንዲያቀርቡ
የላክናቸውን
ኮሚቴዎች ኣሰሯቸው ለኣንድ
ወርም ማንም እንዳይጠይቃቸው
ኣደረጉ
እንዴ ከዛስ? ከዛ ቡሃላማ
በየመስጊዱ ኣህባሽ ኢማሞችን
እየቀየሩ
መስጊድ የተባለን ሁሉ
ነጠቁን እንዴ ከዛስ? ከዛማ በኣህባሽ
ኣንሰግድም ብለን በራሳችን
ኢማም ሁለተኛ ጀማአ መስገድ
ስንጀምር
እስሩ እና ዱላው ተጧጧፈ
እንዴ ከዛስ? ከዛማ ምንድነው ነገሩ
እያልን
ስንገረም በተለያዩ
ክልሎች ሆነ ብለው ብጥብጥ እያስነሱ
የብዙ
ሙስሊሞችን ህይወት
ቀጠፉ ኣሃ ከዛ ኣገሪቷን
ድብልቅልቋን
ኣወጣቹሃት ኣይደል? ኣይ
ይግረም ብለው በየቤቱ ፍተሻ ብለው
ሙስሊሙን መዝረፍ እንደውም
ኣንድ ቤት ኣንዲት የኣስራ ሰባት
ኣመት ልጅ
ደፈሩ ገባኝ ከዛ እቤት
ኣንመልስም ብላቹህ ወደ
ቤተመንግስት
ሄዳቹህ ኣይደል? ኣይ
እንደውም ኮሚቴው ኣሸባሪ ነው
ብለው
የሃሰት ፍልም ሰርተው
በስህተት ይሁን ወይም ምን ያመጣሉ
ብለው
እኛም እንድንፈራ
ሲያሰቃዯቸው የሚያሳይ ፊልም
ኣሳዩን ኣሃ
ከዛ ቡሃላ ነው ቤት
ኣንመለስም ያላቹህት? ኣይደለም
ከዛማ
የኢድ በኣላችን ላይ
መንግስት ፕላን ኣውጥቶ ህጻን
ወጣት ሴት
ኣዛውንት ሳይል በርካታ
ሙስሊሞችን ገድሎ ቁጥር ስፍር
የሌለውን
ህዝብ ኣቆሰለ በሺወች
የሚቆጠሩትንም ኣሰረ ገባኝ ያኔ
ትግስታቹህ
ኣለቀ ምን ኣደርርጋቹህ?
ምን እናደርጋለን ሙስሊሙን ሁለት
ሶስት
ሳምንት እያሰሩ ደጎም ባለ
ዋስ ሰበብ በቁሙ ዘረፉ እንዴ ባክህ
እኔ ቀልድ
ኣልፈልግም እውነቱን
ንገረኝ ከዛስ? ከዛማ በማሃል የሆኑ
ሰውዬን
ገድለው በሃሰት
ሙስሊም ወንድሞቻችንን
በማሰቃየት እኛ
ነን የገደልነው ኣስባሏቸው
ወይ ጉድ ከዛስ ከዛማ ከሁለት ቀን
በፊት
መንግስት ኣይዟቹህ
የሚላቸው ኣህባሾች ሃረር ወስጥ
ተሰበሰቡና
ኣህባሽ ያልሆነውን
ሙኣዚን ፈነካክተው ለቀቁት ኣሃ
ኣገሪቷ
በኣንድ እግሯ ቆመች በለኛ?
ኣይ ዛሬ ደግሞ ኣንድ የዩኒቨርሲቲ
ተማሪ
የነበረች እህታችን ከኣመት
በላይ መታሰሯ ሲገርመን መከላከያ
ኣቅርቢ
ተብላ ፍርድቤት ስትናገር
ኣራት ፖሊሶች ልብሷን ኣስወልቀው
እንደገረፏት ለፍርድ ቤት
መናገሯን ሰማን ኣሃ በቃ ተወው
ኣሁን ገባኝ
ለካ ኣንተም ሁሉንም
ታሪክ ስትነግረኝ በህይወት ያለህ
መስሎኝ
ነበር ኣውፍ በለኝ ለሙሉ
ኢትዮጲኣዊ ሙስሊም ኣለም ላይ
ባሉ
መስጊዶች ሁሉ ሰላተል ጀናዛ
እንዲሰገድልን ኣደርጋለሁ በል ኣሁን
ኢሄ
ዱንያን ማፍቀር ከኣንተ
እንዳይጋባብኝ ዞር በልልኝ ኣላህ
ሁላችንንም
ይቅር ይበለን።

Advertisements

About Weraba times

I am journalist Journalisten
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s